ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( # GIYORGIS_OF_SEG
LA ) +
ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ
ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ
ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ
"ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው
"የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት::
መገፋቱን የተመለከተ #አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን
ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ::
ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም
ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል
እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ
መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም
ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን
አጠጥታው ተሠወረችው::
+ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ::
በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን
ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ::
የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን
ደረሰ:: (መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን:
ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች
ነበሩ)
ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው
የኢ/ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:-
1. #ሊቀ_ሊቃውንት
2.#በላዔ_መጻሕፍት
3.#ዓምደ_ሃይማኖት
4.#ዳግማዊ_ቄርሎስ
5.#ጠቢብ_ወማዕምር
+ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች
ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ
7 ቀን ነው::
የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ
ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
እንኳን ለቅዱስ ሊቀ ሊቃውንት ማኅሌታይ አምሳለ ሱራፌል ያሬድ ካህን ለተሰወረበት ልዩ ክብረ በዓል አደረሳችሁ።

#መዘምር_ዘበድርሣን
#ጥዑመ_ልሳን
#ካህነ_ስብሐት
#ማኅሌታይ
#ሊቀ_ሊቃውንት
#አምሳለ_ሱራፌል የኢትዮጵያ ዕንቊ የቤተ ክርቲያን እንዚራ ምድራዊው መልአክ ቅዱስ ያሬድ ሊቅ ማኅሌታይ በረከቱ በእጅጉ በዝታ ትደርብን።

ያሬድ ማኅሌታይ ለእግዚአብሔር ካህኑ
ስብሐተ ትንሣኤ ዘይዜኑ
ኦሪት ቶታኑ ወወንጌል አሣዕኑ
ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ
ከመ ጸበል ግሁሣን ፀርነ ይኩኑ።