ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ቅዱስ_ሩፋኤል_ሊቀ _መላዕክት
#ሢመት
ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከ7ቱ ሊቃነ
መላእክት በደረጃው 3ኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት
እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በ10 ከተማ
ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች::
በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ 10ሩ ነገድ አለቃ
(መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል::
በሁዋላም "#መጋብያን " በሚባሉ በ23ቱ ነገድ ላይ
ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት::
#ቅዱስ_ሩፋኤልና_ሐዋርያት
አንድ ቀን #ጌታችን_ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ
ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት::
ጌታም 3ቱን ሊቃናት ( #ሚካኤል: #ገብርኤል እና #ሩፋኤል
) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው::
ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው" አለው::
እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው::
በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ
የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ::
#ረዳትነት
በመጽሐፈ #ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ
መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ:
ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዐይን
አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን
ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል::
#ቅዳሴ ቤት
ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ
ቤቱም ናት:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ #ቴዎፍሎስ
ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ
የታነጸው በአሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ
አጋዥነትም ለ300 ዓመታት አገልግሏል::
#ቅዱስ_ሩፋኤል
¤መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
¤አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
¤መዝገበ ጸሎት (የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
¤ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት
መሪ)
¤ፈታሔ ማሕጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማሕጸን
የሚፈታ)
¤መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማሕጸኖሙ አንተ" እንዲል::
💚💛ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር💛❤️
በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት
ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ #አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም::
እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ
ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም::
በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም " #ዮሐንስ_ሐጺር -
አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል:: ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ
ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም
ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::

ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ
ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ
መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል::
ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ
ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::
ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር
በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ
ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው
ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ
"አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር:: ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::

#አባ_ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ
ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ
ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::

አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ
ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ
መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል:: ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና
ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው
አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ
አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ
ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ
ወስዶ ተከለው:: ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ:: በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው
በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ
ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም:: ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው:- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው::" ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::
መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ
ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው
ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ
ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ
አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::
#መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ
ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር::
ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን
ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::
አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ
(ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን
#ሊቃነ_መላእክት #ሚካኤል እና #ገብርኤል በግርማ በጌታ
ፊት ቆመው ተመለከተ::
"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ
እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ
ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን
ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ #ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ
ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ
#ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::
በ825 ዓ/ም ግን በአባ #ዮሐንስ_ፓትርያርክ ዘመን ክቡር
ሥጋው ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው
ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ
ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ #ቅዱስ_መቃርስ
ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ
ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል:: ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ::
ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ
ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን::
በበረከቱም ይባርከን::
Dn yordanos abebe
🌼መስከረም 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት🌼
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት
3.ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ
4.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት (ልደቱ)
5."14,730" ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማሕበር)
🌻ወርሐዊ በዓላት🌻
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ)
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
"የፋርስ መንግስት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቁዋቁዋመኝ:: እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ #ሚካኤል
ሊረዳኝ መጣ:: እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት::" (ዳን. 10:13)
👉 @senkesar join us!