‹‹ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ይድረስ ዓይኔም በፊቱ ዕንባ ታፍስስ›› ዕዮብ 16፡20
ሕዝቅያስ ሆይ ዕንባ ምህረት እንደሚያሰጥ እድሜም እንደሚያሰቀጥል አንተ ታውቃለህ እስቲ እንጠይቅህ ...ትሞታለህ ተብለህ መርዶህ ተነግሮህ ሳለ እንዴት 15 ዓመት ሙሉ ተጨመረልህ ?
የሕዝቅያስ መልስ፡-
‹‹ፊቴን ወደ ግድግዳ መልሼ ወደ እግዚአብሔር ጸለይኩኝ 'አቤቱ በፊትህ በእውነትና በፍፁም ልብ እንደ ሄድኹ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግኹ ታስብ ዘንድ እለምንሃለኹ' ብዬ እጅግ አድርጌ አለቀስኩ እግዚአብሔርም በኢሳይያስ በኩል እንደታረቀኝና የሞቱ ዜና ተቀይሮ ይኸው አስራ አምስት አመት እንደተጨመረልኝ አበሰረኝ›› (2ነገ 20፡5) የሚል ይሆናል፡፡
ዕንባ!
ፃድቅ የተባለ ዕዮብ በጸሎት ጊዜ ዕንባ አስፈላጊ እንደሆነ ሲናገር ‹‹ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ይድረስ ዓይኔም በፊቱ ዕንባ ታፍስስ›› (ዕዮብ 16፡20) ይላል፡፡ታዲያ ይህች ዕንባ ልባቸው ለተሰበረ ምልክት ናትና ወደ እግዚአብሔር ታቀርባለች፡፡ (መዝ 34፡18)
በፍፁም ጸፀት የምታለቅስን ዓይን አይቶ እግዚአብሔርም ዝም አይልም ‹‹አውከውኛልና ዓይኖችሽን ከእኔ መልሺ›› ይላል እንጂ! የአጋንንት ዋና ስራቸውም እንደ እሳት የምታቃጥላቸውን ይህቺን የንስሐ ዕንባ ከእኛ ማጥፋት ነው፡፡ ለእነርሱ አትመችምና!
የስንቶቻችን ዓይን ወደ ፈጣሪ ለማልቀስ ደርቆ ይሆን?
‹‹አቤቱ በደሌን እና ነውሬን የምታጥብ ዕንባ ሥጠኝ ፤ አቤቱ አንተን የሚያገለግል እንባ ስጠኝ ፤ አቤቱ የሚያቃጥል እንባ ሥጠኝ››
ከዳረጎት ዘተዋሕዶ ቁጥር 3 መጽሔት የተወሰደ!

ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን በዓላት ውስጥ አንዱ ለሆነው ለታላቁ የሆሳዕና በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!
"ሆሳዕና በአርያም" ማለት በአርያም /በሰማይ/ ያለ መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሆሻአና" የሚል ሲሆን ትርጉሙም "እባክህ አሁን አድን" ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡ መዝ.117፡25-26፡፡
የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም" በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡
በሌላ አነጋገር ይህ ዕለት የጸበርት እሑድ /Palm Sunday/ ይባላል፡፡ ታሪካዊ አመጣጡ የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት መገለጫ ሆኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ይኸውም ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ጨርሳ ልማደ እንስት ከተቋረጠባት በኋላ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ ድርብ ደስታ በገለጡ ጊዜ፣ እንዲሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ አደባባይ ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን መስቀሉ /ሉቃ.22፤18/ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አእሩግ ነጻ የሚወጡበት ቀን መድረሱን እነርሱ ሳያውቁ እግዚአብሔር ባወቀ ዘንባባ በመያዝ ዘምረዋል፡፡ እስራኤል ዘንባባ በመያዝ እንዳመሰገኑት እኛም አስራኤል ዘነፍስ ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን በየዓመቱ እያስታወስን እናከብራለን፡፡ በዚህ ዕለት ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝቡ ይታደላል፡፡
ሕፃናትና አእሩግ "ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል" እያሉ ዘምረዋል፡፡ ይህ ሁሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲሆን በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ ጸሐፍት ፈሪሳውያን "መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው" አሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ "እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ሲል መልሶላቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው ፈሪሳውያንም የዋህ የሆነው ሕዝብ ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው በዕለተ ሆሳዕና እሑድ ዘንባባ ይዘው የዘመሩለትን ጌታ ዓርብ ላይ "ይሰቀል ዘንድ ይገባል" ብለዋል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በዚህም በነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡ "እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡" ዘካ.9፡9፤ ማቴ.21፡4፤ ማር.11፡1-10፤ሉቃ.19፡28-40፤ ዮሐ.12፤15፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት ሲሆንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም እውነተኛ የኅሊና ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17
ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡
ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፤ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡
የተምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡
የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡
ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፤ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡
በጌታችን በዕለተ ልደቱ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል በምድር ሰላም ለሰው ሁሉ ይሁን" /ሉቃ.2፡13/ እያሉ የዘመሩለት የሰላም ባለቤት ነው፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" /ዮሐ.14፡27/ ብሎ እንዳስተማረ ያን ሰላም የሚሰጥበትን ዕለት መቅረቡን ለማመልከት ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፣ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡ በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ ቅርብ ሲሆን በእምነት ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ መሆኑን አስተምሯል፡፡ ስለዚ

ህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜያችን ሳትጠልቅ በእምነት እንፈልገው፡፡ አሞጽ4፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፣ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅም፡፡ ኢሳ.66፡2፤ መዝ.50፡17፡፡
ጌታችን በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ስለሆነ የክብረ በዓሉ ምስጋና በዋዜማው ይጀመራል፡፡ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ካህናቱ በእምርት ዕለት በዓልነ፣ በታወቀ የበዓላችን ዕለት ከበሮ ምቱ በማለት የዋዜማውን ምስጋና ይጀምራሉ፡፡ የዋዜማው የምስጋና ቀለም እጅግ ሰፊ ስለሆነ በዚህ መዘርዘር አይቻልምና ከዋዜማው ፍጻሜ በኋላ ያለውን ሥርዓት እንመልከት፡-
በሌሊተ የሆሳዕና ማኅሌት ከመቆሙ በፊት በካህኑ ተባርኮ በሰሙነ ሕማማት ሲነበብ ሲተረጎም የሚሰነብተው ግብረ ሕማማት የተባለው መጽሐፍ መነበብ ይጀምራል፡፡ ስቡሕ ወወዱስ ዘሣረር ኩሎ ዓለመ፣ ዓለምን ሁሉ ፈጠረ እግዚአብሔር ፍጹም የተመሰገነ ነው በሚለው የምስጋናዎች ሁል ርእስ የዕለቱ የማኅሌቱ ምስጋና በካህናትና በሊቃውንት ይጀመራል፡፡
ከዐቢይ ጾም መግቢያ ጀምሮ ማዕቀብ ተጥሎባቸው በዝምታ የሰነበቱት ከበሮና ጽናጽል የምስጋናው ባላድርሻዎች ይሆናሉ፡፡ በዚህ የተጀመረው ማኅሌት ሌሊቱን ሙሉ አድሮ መዝሙር በሚባለው . . . ምስጋና በኩል አድርጎ ሥርዓተ መወድስ ተደርጎ ሰላም በተባለ ምስጋና ይጠናቀቃል፡፡
ሥርዓተ ዑደት በሆሳዕና
ሥርዓተ ማኅሌቱ ተፈጽሞ ሥርዓተ ቅዳሴው ከመጀመሩ በፊት እሰካሁን ከነበረው ሥርዓት ለየት ያለ ሆኖ እንመለከታለን፡፡ ይኸውም ሊቃውንቱ የዕለቱን ድጓ እየቃኙ እየመሩና እየተመሩ፣ ዲያቆኑ ከመዝሙር ዳዊት የዕለቱን በዓል የተመለከተ ምስባክ በዜማ እየሳመረ፣ ካህናቱም በዓሉን የተመለከተ ወንጌል በዐራቱም መዓዘን እያነበቡ ቤተ መቅደሱን አንድ ጊዜ ይዞሩታል፡፡
ለምሳሌ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ባለው በር ፊት ለፊት በመቆም መምህሩ አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ፣ ወደቤቱ እንገባ ዘንድ መንገዱን አሳዩን፡፡ የሚለውን ድጓ ይቃኛሉ ካህናቱ እየተከተሉ ያዜማሉ ዲያቆኑ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘየሐድር ውስተ ጽዮን፣ በጽዮን የሚገለጥ እግዚአብሔርን አመስግኑ እያለ ያዜማል፡፡ ካህኑም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 21፡ 1-13 ያለውን ኀይለ ቃል ያነባል፡፡ በዚህ ዓይነት መልክ በዐራቱም መዓዘነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ዑደት ይፈጸማል፡፡
ይህን ሥርዓት ሊቃውንቱ ሲተረጉሙት አንደኛ ጌታችን በአህያ ውርንጫ ተጭኖ በሕፃናት አንደበት እየተመሰገነ ኢየሩሳሌም የገባበትን የምስጋና ጉዞ ለማመልክት ሲሆን ሁለተኛ ሕገ ወንጌል በዐራቱም ማዕዘነ ዓለም ለሕዝብና አሕዛብ መዳረሱን ለማመልከትና ሕዝብና አሕዛብ በሕገ ወንጌል አንድ አካል መሆናቸውን በገቢር ለማሳየት መሆኑን ያስተምራሉ፡፡
ሥርዓተ ቅዳሴ ዘሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና አሁንም የቅዳሴው አገባብ ሥርዓት ከሌሎች ዕለታት ለየት ያለ መሆኑን እንመለከታለን፡፡ ዲያቆናቱ ሕብስቱን በመሶበ ወርቅ ወይኑን በጽዋዕ ይዘው በምዕራብ በር በኩል ይቆማሉ፣ ሠራኢው ዲያቆን በዜማ አሰምቶ እርኅው ኆኅተ መኳንንት፣ አለቆች ደጆችን /በሮችን/ ክፈቱ ይላል፡፡ ካህኑም በመንጦላዕክት ውስጥ ሆኖ መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት ይህ የክብር ንጉሥ ማነውÃÂ ብሎ ይጠይቃል ዲያቆኑም ይህ የኃያላን አምላክ እግዚአብሔር ነው ብሎ ይመልሳል፡፡ ዲያቆኑ ሦስት ጊዜ የክፈቱልኝ ጥያቄያዊ ዜማውን ካዜመ በኋላ ካህኑ ይባዕ ንጉሠ ስብሐት፣ የክብር ንጉሥ ይግባ ብሎ ፈቅዶለት ይገባል፡፡ መዝ. 23፡7
ይህንንም አበው እንደሚከተለው ያመሰጥሩታል፡፡ አንደኛ ቅዱስ ገብርኤልና ወላዲተ አምላክ በምሥጢረ ብስራት ጊዜ የተነጋገሩት እንደሆነና በመጨረሻም ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ፣ እንደቃልህ ይደረግልኝÂ ብላ መቀበሏን ሲያሳይ ሁለተኛው ፈያታይ ዘየማንና መልአከ ኪሩብ በማእከለ ገነት የተነጋገሩትን በድርጊት ለማሳየት መሆኑን ያስተምራሉ፡፡ ዋናው ምስጢር ግን ክርሰቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሊገባ ሲል ብዙዎቹ እንዲገባ መፍቀዳቸውን ያሳያል፡፡
እንደተለመደው ሥርዓተ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ እግዚእ ሕያዋን /የሕያዋን ጌታ/ የተሰኘው ጸሎት በካህናት ተደርሶ ለምእመናን ሥርዓተ ፍትሐት ይደረግላቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ሥርዓተ ፍትሐት ስለማይደረግ፡፡ በሰሙነ ሕማማት የማይከናወኑ ምሥጢራት በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
ምእመናንም ተባርኮ የተሰጣቸውን የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ወደየቤታቸው ያመራሉ፡፡ የዘንባባው ምሥጢር የተጀመረው በታላቁ አባት በአብርሃም ነው፡፡ ኩፋ.13፡21 ይህን የአባታቸውን ሥርዓት አብነት አድርገው እስራኤል የኤርትራን ባሕር ሲሻገሩ፣ ዮዲት ድል ባደረገች ወቅት ዘንባባ እየያዙ እግዚአብሔርን አመስግነውታል፡፡ ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባም ሽማግሌዎችና ሕፃናት የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው እንደተቀበሉት እናነባለን፡፡ ሉቃ.12፡8
ኢትዮጵያውያን ምእመናንም ክርስቶስ የሰላም፣ የነጻነት፣ የድኅነት አምላክ መሆኑን ለመመስከር ዘንባባውን ይዘው ወደቤታቸው ይገባሉ፡፡ ዮሐ.14፡27 በእጃቸውም እንደቀለበት ያስሩታል፡፡
ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የሆነ ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደተቀመጠ ሁሉ ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት ዛሬም ያድራል፤ የኅሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ንስሐ ገብተን ጌታችንን ሆሳዕና በአርያም እያልን ልናመሰግነው ይገባል፡፡
(ምንጭ፡ ሐመር ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ መጋቢት/ሚያዝያ 1996 ዓ.ም፣ ስምዐ ጽድቅ ዘኦረቶዶክስ ተዋሕዶ ጋዜጣ፣ ከመጋቢት 20-24 ቀን 2002 ዓ.ም፤ ልዩ እትም፡፡)

Forwarded from Daregot Media
"ሆሳዕና .... እባክህ አሁን አድን"
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለሆሳዕና በዓል አደረሳችሁ አደረሰን! ዳረጎት ዘተዋሕዶ ቁጥር ➏ መጽሔታችን በዕለተ ሆሳዕና በዛሬው ቀን ወደ እናንተ የምናደርስ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን!
በዚህኛው መጽሔታችን፡-
- ለምን እንታመማለን? ሥነ መለኮታዊና ሳይንሳዊ አንድምታው/ The Theological And Scientific Perspectives Of Why We Get Sick/
- ተዋሕዶዋ - የዓደዋ ድልና ተዋሕዷዊ ገድል
- የቤተክርስቲያን ኅብረት ከትላንት እስከዛሬ
- "ይህንን መጽሐፍ ብላ.....ግን እንዴት?"
- ምግባረ ሠናይና ቤተክርስቲያን
- ማህበራዊ አስተምህሮ/ Social Teaching /
- ቤተክርስቲያንና ወጣትነት
- ዕድሜና የእንቁጣጣሽ ዶሮ የተሰኙ ጹሑፎች የተካተቱበት ነው፡፡
መቼም እንደ አባቶቻችን ብራና ዳምጠን፣ ብርዕ ቀርጸን፣ ቀለም በጥብጠን ራት የሆነ ጹሑፍ ለማቅረብ ባንበቃም ያለውን ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ዳረጎቱን ( ጭማሪ) ይዘን ቀርበናልና www.daregot.com ላይ ገብታችሁ ጎብኙን የጎደለውን ሙሉ፣ የተሳሳትነውንም አርሙን::
የመጽሔታችንን መግቢያ ቀድመው እንዲያነቡ ጋበዝን 👉 http://daregot.com/መልእክተ-ዳረጎት/
የቴሌግራም ገጻችንንም ይከታተሉ https://tttttt.me/daregot

ዳረጎት ዘተዋሕዶ መጽሔታችን በነጻ ለእናንተ ቀርባለች!
3ኛ ዓመት ቁጥር 6 Download 👇
http://daregot.com/3ኛ-ዓመት-ቁጥር-6-2/
በአምስት ዕትሞች ለንባብ የቀረበችው ዳረጎት ዘተዋሕዶ መጽሔት እነሆ በስድስተኛ ዕትሟም ወቅታዊ ጉዳዮችን፣ ማህበራዊ እይታዎችን፣ ታሪካዊ ኩነቶችን፣ የግል ተጋድሏችንን የሚያግዙ ምእዳናትንና ሌሎች ዘርዘር ብለው የቀረቡ ኃሳቦችን አካታ ቀርባለች፡፡ ታዲያ ዳረጎት መጽሔታችን ለሌሎችም ትደርስ ዘንድ በሚችሉት አቅም ለብዙዎች እንዲያጋሩ እንጠይቃለን፡፡
መልካም ንባብ!
የቴሌግራም ቻናላችንንም ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/daregot

Forwarded from Liya Fashion
Tselot zeSemuneHimamat (Bezema_Yemiders-1).pdf
66.5 KB
ከካህናት ጋር አብሮ ለማዜም የተዘጋጀ ነው መልካም የሰሙነ ህማማት ሳምንት
አምላክ፦የአዳም ዘር ይድን ዘንድ፣ በፍቅሩ ተገዶ፤
ከሰማይ ዝቅ አለ፣ ከአምላክነት ሳይጎድል፣ በሰውነት ወርዶ።አይሁድ፦
የእርሱ ፍቅር ሳይሆን፣ ክብራቸው ገዷቸው፤
እውነቱ... ተግሣጹ... ስላሳበዳቸው፤
ለክፉ ሥራቸው፣ ነፃነት ፈልገው፤
እጅና እግሮቹን፣ በችንካር ሰንገው፤
"በክፉ ዓለማቸው፣ ደጉን እንዳያዩት፤
ዝቅ ብሎ ቢመጣ፣ ከፍ አ’ርገው ሰቀሉት"።እኛ፦
ከሰማይ መውረዱ፤ከሰው መወለዱ፤መከራ ስቅለቱ፣ ሕማምና ሞቱ፣
ቢገባን ባይገባን፣ የበዓሉ ምሥጢራት፤
ፋ ሲ ካ - እንወዳለን፣ ደግሶ ለመብላት።እንዲያውም...
በጾም ሳያደክም፣ በሕማም ሳይነካ፤
ቢሆን ደስ ይለናል...ሁልጊዜ ትንሣኤ፣ ሁልጊዜ ፋ ሲ ካ።እንደዚህ ነን በቃ!
መከራን ረስተን፣ ደስታን አድማቂ፤ያለ ሕማማት ሞት፣ ትንሣኤን ናፋቂ።
ነገር ግን...
የድኅነት ምሥጢሯ፣ አይሻር እውነቱ፤
ትንሣኤን ይቀድማል፣ መከራ ስቅለቱ... ሕማሙ እና ሞቱ።
ከሕማማት ሸሽቶ፣ ከመከራ ርቆ፤
በቃል ተመፃድቆ፣ በስብከት ተራቆ፤
እንዲያው በማስመሰል፣በሚኖሩትዓለም፤
እንኳንስትንሣኤ..
.በጎ ሕልም ሚያዩበት፣ የእንቅልፍ ረፍት የለም።

ዘረቡዕ (ረቡዕ) - ሰሙነ ሕማማት
በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ አዘጋገብ መሠረት ሦስት ነገሮች በዕለተ ረቡዕ ተደርገዋል፤ እነርሱም
የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የካህናት አለቆች÷ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
2. ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
3. ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ 30 ብር
ተመዝኖለታል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምንት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ “ሲኒሃ
ድርየም” ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲሆኑ የተቀሩቱ ደግሞ ጸሐፍት
ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ 72 አባላት የነበሩት ሲሆን የሚመራው በሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ነበር፡፡
በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ይዘው እንደ ሚገድሉት መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ በጸሐፍት
ፈሪሳውያንና በካህናት አለቆች ዘንድ ይጉላላ የነበረውን ጥላቻ ያውቁ ስለነበር “ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም
አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተዋውሏል፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችን
ያስተምር በነበረበት ወቅት ከተለያዩ ሰዎች የሚገባውን ገንዘብ ሰብሳቢ /ዐቃቤ ንዋይ/ ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ
ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ
አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ
ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡ “ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር” በማለት ያቀረበው
ሐሳብ “አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓች” እንደ ሚባለው ነበር፡፡ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም አለ፤ ሽቶ ከፈሰሰ
የሚተርፈው የለም፡፡ ይህ በመሆኑ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው ሐሳብ ተቀባይነት ስላጣ ማኩረፊያ ያገኘ መስሎት
በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሄዶ ተዋዋለ፡፡ ብር 30 ተመዘነለት፡፡ ይህ አሳዛኝ ታሪክ በሦስቱ ወንጌላት ውስጥ
በሚከተሉት ጥቅሶች ቀጽፎ እናገኛለን፡፡ (ማቴ.26÷3-16፤ ማር.14÷1-11፤ ሉቃ.22÷1-6 ይመልከቱ፡፡)
የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን እግር ስር ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡
የተለያዩ ገቢረ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ሁሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎቹ ሁሉ ሳይለየው እግሩን
አጥቦታል፤ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታውን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡
“የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል÷ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት እንደ
ተባለ፡፡” ማቴ.26÷24፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ “ገንዘብ የኃጢአት ስር ነው” ተብሎ አንደ ተነገረ ይህ የኃጢአት ስር የክርስቲያኖችን ሕይወት ሊያደርቅ
ስለሚችል ለገንዘብ ያለን ፍቅር በልኩ ሊሆን ይገባል፡፡ ሰው ይህን ህልም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል
ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡
ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ
የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደሆነ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት
ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡
እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረሃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው
ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይሆን ለእምነታችንና
ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ
ሸንጐ ምቹ ሆነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን፡፡
ይቆየን ።

ምሴተ ሐሙስ
ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
ጴጥሮስም፦ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም፦ ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ
መለሰለት።
ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።
ኢየሱስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም
ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።
አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ፦ ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለው።
እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን
ታስተውላላችሁን?
እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።
እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ
ዘንድ ይገባችኋል።
እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።
ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።
ስለ ሁላችሁ አልናገርም፤ እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ። እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ
ተረከዙን አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
በሆነ ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ፥ ከአሁን ጀምሬ አስቀድሞ ሳይሆን እነግራችኋለሁ።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ማናቸውን የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን
ይቀበላል።
ኢየሱስ ይህን ብሎ በመንፈሱ ታወከ መስክሮም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል
አለ።
ደቀ መዛሙርቱ ስለ ማን እንደ ተናገረ አመንትተው እርስ በርሳቸው ተያዩ።
ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ እርሱን
ጠቅሶ። ስለማን እንደ ተናገረ ንገረን አለው።
እርሱም በኢየሱስ ደረት እንዲህ ተጠግቶ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነው? አለው።
ኢየሱስም፦ እኔ ቍራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው ብሎ መለሰለት። ቍራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን
ልጅ ለይሁዳ ሰጠው።
ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት። እንግዲህ ኢየሱስ፦ የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ
አለው።
ነገር ግን ከተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው ማንም አላወቀም፤ ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ፥ ኢየሱስ፦
ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፥ ወይም ለድሆች ምጽዋት እንዲሰጥ ያለው ለአንዳንዱ መስሎአቸው ነበርና።
እርሱም ቍራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ።ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ። አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚአብሔርም ስለ እርሱ ከበረ፤
እግዚአብሔር ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ፥ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱን ራሱን ያከብረዋል ወዲያውም ያከብረዋል።
ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድም። እኔ ወደምሄድበት እናንተ
ልትመጡ አይቻላችሁም እንዳልኋቸው፥ አሁን ለእናንተ ደግሞ እላችኋለሁ።
እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ
እሰጣችኋለሁ።
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።
ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄዳለህ? አለው። ኢየሱስም፦ ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ
አትችልም፥ ነገር ግን በኋላ ትከተለኛለህ ብሎ መለሰለት።
ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ አሁን ልከተልህ አለመቻሌ ስለ ምንድር ነው? ነፍሴን ስንኳ ስለ አንተ እሰጣለሁ አለው።
ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት። ነፍስህን ስለ እኔ ትሰጣለህን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሦስት ጊዜ
እስክትክደኝ ድረስ ዶሮ አይጮኽም።
ይቆየን ።
አዘጋጅ ዲያቆን ኃይለሚካኤል

ሐሙስ ምሽቱን
በዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ከስቅለት በፊት ያለው ሐሙስ ፣ ጸሎተ ሐሙስ ፣ ምሴተ ሐሙስ ፣ ትእዛዘ ሐሙስ ፣ አረንጓዴ ሐሙስ እየተባለ ይጠራል፡፡
ይህ ዕለት የጌታችን ትኅትና የተገለጠበት ፣ ምስጢረ ቁርባን የተመሠረተበት ፣ መከራ መስቀሉ (ሕማማተ መስቀሉ) የተጀመረበት በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ልዩ ልዩ ሥርዓቶችም ይከወኑበታል፡፡
በዚህ ጽሑፍ ግን ጌታችን በተያዘበት ሐሙስ ምሽት ከጅማሬ እስከ ፍጻሜው የተፈጸሙ አበይት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርጊቶችን በሰዓታት ቅደም ተከተል ከጥቂት ማብራሪያ ጋር መተረክ ወደናል፡፡
❖ከምሽቱ አንድ ሰዓት❖
ጌታችን የሐዋርያቱን እግር ያጠበበት ሰዓት ነው። ጥቂት ቀደም ብሎ ከአራት ቀን በኋላ ከሞት ባስነሣው በአልዓዛር ቤት የፋሲካ ራት በልተዋል። ከማዕድ እንደተነሡ ማበሻ ጨርቅና በመታጠቢያው ውሃ ወስዶ ዝቅ ብሎ ተንበርክኮ በትኅትና እግራቸውን አጠበ፡፡ በመጽሐፈ መነኮሳት በተለይም በፊልክስዩስ በስፋት እንደተገለጸው የዚህ ሕጽበተ ፋሲካ ንባቡም ምሥጢሩም ግብረ ትኅትናና የአብነት ሥራ ነው......
ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ 👉 http://daregot.com/ሐሙስ-ምሽቱን/
Join Us @daregot