ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ሕይወቴን ውሰድና
ሞትህን አቀብለኝ!
___________

ቢቢሲ እንደዘገበው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በጣልያን ብቻ ከ50 በላይ ቀሳውስት ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአንደኛው ካህን ህልፈተ ሕይወት ግን ልብ ይነካል።

አባ ጁሴፔ ቤራርዴሊ ይባላሉ። በጣልያኗ ካስኒጎ ከተማ ሊቀ ካህን ሲሆኑ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ሎቬሬ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነበር። በቫይረሱ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት መተንፈስ በመቸገራቸው የሚያገለግሉባት ቤተክርስቲያን አጥቢያ ምእመናን በማዋጣት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያ (respirator) ገዝተው ሆስፒታል ያመጡላቸዋል።

ሐኪሞቹ እስትንፋስ በመስጠት ሕይወት የሚቀጥለውን የመተንፈሻ መሣሪያ አባ ቤራርዴሊ ሊቀጥሉላቸው ሲሉ ካህኑ "አሻፈረኝ" ይላሉ። ምክንያታቸውን ሲጠየቁ "ከእኔ ይልቅ ወጣት ለሆነው ታካሚ ስጡት" በማለት እምቢ ይላሉ። የሚገርመው ነገር አባ ቤራርዴሊ ከዚህ ቀደም ዐይተውት ለማያውቁት፣ ዘሩንም ሆነ ሃይማኖቱን ለማይለዩት ታማሚ ነው "ሕይወቴን ውሰድ እና ሞትህን አቀብለኝ" ያሉት።

በትእዛዛቸውም መሠረት ከምእመናን ተገዝቶላቸው የመጣላቸውን ብቸኛውን የመተንፈሻ መሣሪያ ሐኪሞቹ ለወጣቱ ታካሚ ይሰጡታል። አባ ጁሴፔ ቤራርዴሊም በዚሁ ሆስፒታል በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።

ብዙዎቻችን ኖረን እንሞታለን። ጥቂቶች ደግሞ ሞተው ይኖራሉ። የአባ ቤራርዴሊን የመሠሉ ታሪኮች በብዙ መቶ አመታት መካከል አንዴ የሚተረኩ እንጂ የአዘቦት ወጎች አይደሉም። በርካቶች የፈጣሪን ቃል ያነባሉ። አንዳንዶች ደግሞ ቃሉን ይሰብኩታል። እጅግ ጥቂቶች ግን ቃሉን ይኖሩታል።

"እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል"
(1 ዮሐንስ 3 ፥16)

________
"የቤተ ክርስትያን መመሪያ ከእምነት መጉደል ቆጥሮ የሚተች ሰው ካለ በጠንካራ እምነቱ ኮሮናን በማስወገድ እንዲገላግለን በትሕትና እንማፀናለን"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የምንጠነቀቀው በኖቬል ኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ቁጥር ስለጨመረ ሳይሆን እንዳይጨምር ነው። አሁን መዘናጋት ይብቃን በየደጃችን እያንኳኳ ነው። ብዙ ሰዎች ምርመራ ስላልተደረገላቸው እና በመገናኛ ብዙሃን ስላልተነገረን ከሆነ ተሳስተናል የትኛውም ሀገር በቸልተኝነት የቁጥር ጨዋታ ሲንቅ የሆነውን ሰምተናል አይተናል። አሁን ከየመሀላችን ጤነኛ የመሠለን ሰው በሽታ ይዞ እያከፋፈልን ላለመሆኑ ምን እርግጠኛ ነን?! አድኀን ጌታ ሆይ ። የነነዌን ህዝብ እንዳዳነ ያድነን።
ኮሮና ሆይ ቅዳሴ አስታጉለሀልና እግዚያብሔር ያስታጉልህ
.ነሐሴን እግዚአብሔር ይቅሠፈው!
ወሩ ከላይ ዝናም ከታች ምንጭ እየገነፈለ ምድራችን በውኀ የምትሸፈንበት ወርኀ ነሐሴ ነው። ተረኛው ቀዳሽ ካህን ከቤቱ ወደቤተ ክርስቲያን ለመኼድ አንድ ትንሽ ወንዝ ተሻግሮ ነበር የሚኼድ፤ ከዕለታት በአንድ ቀን በነሐሴ ወር ግን ካህኑ ቀን ጎደለበት ወንዙ ሞላበት፤
ወንዙን ለመሻገር የቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሞገስ
ወይም የክሪስ ኤንጅል plexiglass ያስፈልጋል
ግን ኹለቱም አልነበረውምና ወደቤቱ ተመለሰ። ቅዳሴው ታጎለ።
ይኽን ነገር የሰማ የቅኔ ተማሪ እንዲኽ ሲል ቅኔ ቆጠረበት።
“እግዚአብሔር ይቅሥፎ ለዘኀለፈ ነሐሴ፤
እንተ ዘነሐሴ ክረምት እስመ አኅጎለ ቅዳሴ፤
ያለፈው ነሐሴን እግዚአብሔር ይቅሠፈው
የነሐሴ ክረምት ቅዳሴ አስታጉሏልና”
አይ የካህኑ አበሳ!
ቅዳሴ አላስታጉልም እንደምንም ልሻገር ብሎ ሰጥሞ ቢሞት፣ ተዳድፎ ሊቀድስ አስቦ ይኾናል የተቀሰፈ የሚለው ይኖራል፤
(( ዳንኤልን ያከበረ አንበሳ አግናጥዮስን መብላቱ፣ አግናጥዮስ ሀይማኖት ስላልነበረው ነው እንዴ? አግናጥዮስን ሳትኾን 'አንበሳውን' አትዳፈር!))
ወንዙን ፈርቶ ሲቀር ይኸ ፈሪ ቄስ ፈጣሪውን አምኖ ዋኝቶ መሻገር ሲገባው ቅዳሴያችንን አስታጎለ ተብሎ አምኖ ባለመሻገሩ ይወቀሳል።
እንደ ተሜ ያሉት ባለቅኔዎች ደግሞ የቀረውን ካህን ያይደለ ያስቀረውን ክረምት ይወቅሳሉ።
ይኽ የኛ ጊዜም በሽታ እንደ ሰርዶ በየምድሩ የበቀለበት በመኾኑ ቅዳሴያችን እንደ ሱራፌል ኾኗል፤ ቀዳሹም አስቀዳሹም ካህን። አልተለመደምና ይጨንቃል ለኛ፤
ቢኾንም ማዕበሉ ጸጥ እስኪል ወንዙ እስኪጎድል በቤት መቆየት በጎ ነው፤ ከፍጹምነት ላልደረስን ወጣንያን ክርስቲያኖች።
የአንዳድ መምህራን ወንድሞቻችን ሐሳብም ቢኾን ወንዙ እስኪ ጎድል ሕዝብ በቤት አይቆይ የሚል አይደለም፤
የሐሳቡ ልዩነት ያለ በግቡ ሳይኾን በሂደቱ ላይ ነው፤ በሂደቱ እኔም ችግር ብየ የማስበው ጉዳይ ነበረ፤ ኾኖም እርስ በእርስ እንደ ድንጋይ ከሚወራወሩት ሮኬት ለመዳን
Iron Dome( የብረት ጣርያ) ውስጥ ሀገራቸውን አስጠልለው የሚኖሩት እስራኤልና ፍልስጥኤም እንኳ በጋራ ገዳያቸው ኮሮና ምክንያት በጋራ መሥራት ሲጀምሩ እኛ መድረሻችን አንድ ኾኖ መንገዳችን የተለያየ ሰዎች
አንድ ኾነን
ኮቪድ ያኅጉልከ እግዚአብሔር ሥላሴ፤
ኮሮና ሕማም እስመ አኅጎልከ ቅዳሴ፤
ቅዳሴ አስታጉለኻልና ኮሮና ኾይ እግዚአብሔር ያስታጉልኽ። እንበል።
አስታጉለኻል ማለታችንም ምእመናንን ስላሰቀረ ብቻ ነው።
<< ጊዜ ስጥ - ልብ ስበር >>
...
ጌታ ሆይ !
ዳግመኛ መምጣትህ፣ እንደማይቀር ባውቅም፤
የመምጣትህን ቀን፣ አሁን አልናፍቅም።
...
ከዕርገትህ በኋላ፣ ዳግም ስትመጣ፤
ጻድቅ መንግሥት ሊወርስ፣ ኃጥዕ ግን ሊቀጣ፤
እንደሆነ አውቃለሁ፣ ዘላለም ለመፍረድ፤
እና አሁን መጥተህ፣ እኔ ሲኦል ልውረድ?
ትንሽ ቆይ ፈጣሪ...
የቁጣ መዓትህ፣ በፍቅርህ ትጋረድ።
...
"ቶሎ ና" ሚሉህን፣ ፈጽሞ እንዳትሰማ፤
እነርሱ ስለእኔ፣ ምንም አያውቁማ።
የአንተን ቶሎ መምጣት፣ ሚናፍቁ ሁሉ፤
ባክህ ልብ ስጣቸው፣ ትንሽ ያስተውሉ፤
ስለእነርሱ እንጅ፣ ስለሰው ያውቃሉ?
በፍጹም አያውቁም ! ሚያቁማ ቢሆኑ፤
ለእኔ ቢጤ ነፍሳት፣ ራርተው ባዘኑ፤
"ጊዜ ለንሰሐ" ፣ ብለው በለመኑ...
...
የአንተ ዳግም መምጣት...
ልክ እንደ ልደትህ፣ ኃጢአትን ለማጥፋት፤
አይደለም ለመስቀል፣ አይደለም ለመሞት፤
ለመፍረድ ነው እንጅ፣ ይግባኝ በሌለው ቃል፤
.......የእኔ ሥራ ደግሞ... ባንተ ይታወቃል።
.
እናም ካላስቸገርሁ...
ለሠራሁት ኃጢአት፣ ዘንድሮና አምና፤
ንሰሐ ለመግባት.... አስቤአለሁና፤
የሆኑ ዓመታት... ትንሽ ዘግይተህ ና !
...
ግን አደራ አምላኬ !
ዕድሜን በቸርነት፣ ከመስጠት ባሻገር፤
ይህን ክፉ ልቤን....... ለ ን ሰ ሐ ስበር።
...
ልቡ ተጸጽቶ፣ ያልተሰበረ ሰው፤
ምንም ለንሰሐ፣ ሺህ ዓመት ቢሰጠው፤
ያው ያባክነዋል... ፊት እንዳመለጠው።
...
.
አሁን ብትመጣ...
የሚጋደሉ እጆች፣
የሚሳደቡ አፎች፣
የሚጠላሉ ዓይኖች፣
ቂም፣ ብሽሽቅ፣ በቀል... የተሸከመ ጉድ፤
መሆኑን እያወቅህ፣ ሚጠብቅህ ትውልድ፤
ሲኦልን ለመሙላት፣ ገነትን አራቁቶ፤
ትመጣለህ ብዬ፣ አልገምትም ከቶ።
...
.
ይሄ ብኩን ትውልድ፣ ይህ ባለጌ ዓለም፤
ስትይዘው ጨነቀው፣ ጊዜ ስጥ ግድየለም።
ግና ግና ግ ና ...
ሰውን እንዳየኸው፣ በሕይወት ጎዳና፤
በሚሰጠው ጊዜ፣ የሚለማመደው፣ ክፋትን ነውና፤
ከመምጣትህ በፊት...
ልኩን እንዲረዳ፣ መዓት በቤቱ አዙረህ፤
ብዙ ሳትጨክን...
በትንሽ ቁንጥጫ፣ ትዕቢቱን አባረህ፤
በሚኖረው ዘመን፣ ልቡን መልስ ሰብረህ።
አ ብ ይ ጾ ም
/፯ኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ/
የአብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት /ኒቆዲሞስ/፦
በዚህ የሰባተኛ የአብይ ጾም ሳምንት አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ቀንና ሌሊት ወንጌልን ያስተምር እንደነበረና በዘመኑ የነበረው የሕግ ሰው
ኒቆዲሞስ በጌታ ትምህርት እጅግ ተማርኮ ሳለ ቀን ቀን ወደ ጌታ ዘንድ እየመጣ እንዳይማር
አይሁድ ይቃወሙኛል የሚል ፍራቻ ስላደረበት ሌሊት ሌሊት እየመጣ ከጌታ ዘንድ
እንደተማረ ይነገርበታል። በተለይም ታላቅ የሕግ መምህር የተባለው ኒቆዲሞስ ሰው ከውኃና
ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ አይችልም ብሎ ጌታ
ያስተማረው ትምህርት እጅግ እንደከበደውና በጥያቄ ውስጥ እንደከተተው እንረዳበታለን።
ከዚህ ትምህርት እያንዳንዳችን የምንረዳው የመንፈስን ነገር ለማወቅ መንፈሳዊ መሆን
እንደሚገባ እንጂ የዓለም ዕውቀት ያለው እና በምርምር ብቻ የእግዚአብሔርን ነገር
አውቃለሁ ማለት አለመቻሉን ነው። ይህንን በተመለከተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ
ሲል ያስተምረናል፦
እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም
ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል
አልነበረም። በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም
ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤ ነገር ግን
እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን
የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን። ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ
ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤ ነገር
ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር
ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን። መንፈስም
የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር
በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን
የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀርለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው
የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ
አልተቀበልንም። መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ
በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል
አይደለም። ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና
አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። መንፈሳዊ
ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። እንዲያስተምረው
የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን። ፩ኛ ቆሮ.፪፡፭-፲፮
የዚህ ሳምንት ትምህርት የሚያስረዳን አብይ ነገር ዘላለማዊ ሕይወት
ለማግኘት ሁለተኛ ከክርስቶስ መወለድ አስፈላጊ መሆኑን ነው። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ፤
ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነውና በማለት ለኒቆዲሞስ የተናገረ ጌታ ዛሬም ሁለተኛ መወለድን
ሞኝነት አድርገው ለሚያዩ ዳግም መወለድ እንዳለባቸው ሐዋርያትን ተክተው በእግራቸው
በገቡ ካህናት ያስተምራል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ስለ ዳግም መወለድ እንዲህ ይለናል፦
ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደደ ነፍሳችሁን
አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ። ዳግመኛ የተወለዳችሁት
ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ
ዘር ነው እንጂ። ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ
ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም
የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው። ፩ኛ ጴጥ.፩፡፳፪-፳፭
በዚህ በሰባተኛው ሳምንት በቅዳሴ ላይ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሙሉው ምንባብ
ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦
ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ
እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ
ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች። ስለዚህ ባልዋ
በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ
አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም። እንዲሁ፥ ወንድሞቼ
ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ
እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ። በሥጋ
ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ
ነበርና፤ አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም
በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም። እንግዲህ
ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን
ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ። አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና። ኃጢአት ግን
ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና።
እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ
እኔም ሞትሁ፤ ለሕይወትም የተሰጠችውን ትእዛዝ እርስዋን ለሞት ሆና አገኘኋት፤
ኃጢአት ምክንያት አግኝቶ በትእዛዝ አታሎኛልና በእርስዋም ገድሎኛል። ስለዚህ ሕጉ
ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት። እንግዲህ በጎ የሆነው ነገር
ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም፥ ነገር ግን ኃጢአት ሆነ፤ ኃጢአትም በትእዛዝ
ምክንያት ያለ ልክ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ ኃጢአትም እንዲሆን ይገለጥ ዘንድ በጎ
በሆነው ነገር ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር። ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና፤ እኔ
ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጥሁ የሥጋ ነኝ። የማደርገውን አላውቅምና፤
የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱን አላደርገውም።
የማልወደውን ግን የማደርግ ከሆንሁ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ። እንደዚህ
ከሆነ ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም፥ በእኔ የሚያድር ኃጢአት ነው እንጂ።
በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና፤ ፈቃድ አለኝና፥ መልካሙን
ግን ማድረግ የለኝም። የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን
በጎውን ነገር አላደርገውም። ሮሜ. ፯፡፩-፲፱
ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት
አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ
እንወደዋለን። ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ
ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት
ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ
ከእርሱ አለችን። ፩ኛ ዮሐ.፬፡፲፰-፳፩
ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ
በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፥ እንዲህም
አላቸው። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ
ተጠንቀቁ። ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥
አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ
ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ። ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ
ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከ
ተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።
አሁንም እላችኋለሁ። ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ
ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ
አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።
ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም
እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው። እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው
ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤ ዕለት ዕለትም በመቅደስና
በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም
ነበር። ሐዋ.፭፡፴፬-፵፪
በዚህ በሰባተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦ ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ
አመከንከኒ ወኢተረክበ አመጻ በላዕሌየ
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓሏኢመሕያው
በአማርኛ፦ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤
ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤ መዝ. ፲፮፡፫
በዚህ በሰባተኛው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦
ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤
እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር
ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና
መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው። ኢየሱስም
መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን
መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም። ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት
ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን?
አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና
ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ
የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዳግመኛ ልትወለዱ
ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ። ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም
ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ
የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው። ኒቆዲሞስ መልሶ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው።
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን
አታውቅምን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም
እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም። ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ
ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደ
በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም
ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። በእርሱ
የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ
ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው
እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ
በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ
አሁን ተፈርዶበታል። ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና
ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን
ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ ዮሐ.፫፡፩-፳ይቆየን ።
Forwarded from Daregot Media
የኒቆዲሞስ ታላቅነት

በዚያ “አልቦ ዘመድ በጊዜ ተዋርዶ” በተባለበት ፣ ሐዋርያቱ እንኳ ጥለው በሸሹበት ዕለተ ዓርብ የልጇን መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ከአርማትያሱ ሰው ከዮሴፍ ጋር ከመስቀል አውርዶ በቀበረ ጊዜ እመቤታችን ለኒቆዲሞስ የመረቀችው ምርቃት “ታላቅ ያድርግህ!”(1) የሚል ነበር።

ይኸውም ሲደርስ ሲፈጸም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የታላቁ አቢይ ጾም ፯ተኛ ሳምንት መጠሪያ አድርጎት ፤ በጾመ ድጓውም “ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ ፣ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ፣ ወይቤሎ ለኢየሱስ እጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ ፣ አንሥአኒ በትንሣኤከ” (2) እያለ ዘምሮለት በዓመቱ ታሪኩ ሲነገር ታላቅነቱ ሲወሳ ይኖራል።

ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡት https://telegra.ph/ዲረጎት-04-05

Join us @daregot
አንድ ጣሊያናዊ ሐኪም በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ላይ ዶክተሮች እያደረጉ ያሉትን የመርዳት ጥረት እና ችግሩን ለመፍታት ያለባቸውን የአቅም ውስንነት ሲገልጽ የጀምስ ካሜሮንን ታይታኒክ ፊልም ለምሳሌነት ተጠቅሞአል::

ታይታኒክ የተሰኘችው መርከብ እየሰጠመች ባለችበት ወቅት መርከቡ ውስጥ የነበሩ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች ነበሩ:: በዚያ ውጥንቅጥ ውስጥ መርከብዋ እየሰጠመች እንኩዋን ሙዚቃ ማሰማታቸውን አላቆሙም ነበር:: ይህ ዶክተርም የሚለው ምንም ማድረግ ባንችል እንኩዋን እየሞቱ ላሉ ወገኖቻችን የቻልነውን ያህል እንታገላለን ነው::

የእኛ ሀገር ሐኪሞች ዕድሜያቸውን ሰውተው ተምረው : የእግር ኩዋስ ተጫዋችን ያህል እንኩዋን ሳይከፈላቸው በቂ መሣሪያ ሳይኖራቸው በብዙ ዋጋ አገልግለዋል:: የሚገባቸውን ክብር ልንሰጣቸው ቀርቶ ድራማ ቢሠራ በእነሱ ላይ : ፊልሙ ቢቀልድ በእነርሱ ላይ ነበር:: ብዙ ስታድየሞችን በፉክክር በየክልሉ የገነባች ሀገራችን ጥቂት ሆስፒታሎችን እንኩዋን ሳትገነባ : ብዙ ጉድለትና ብሶት በተጫነው የጤና ሥርዓት ከባድ ፈተና ተጋርጦብናል::

በየዓለማቱ ሐኪሞች በገፍ የሞቱበትን ይህን ወረርሽኝ ለመጋፈጥ መሣሪያ ሳይኖራቸው ሊዘምቱ የታጠቁ ሐኪሞቻችን ከመቼውም ጊዜ በላይ እገዛ ይሻሉ:: የሕክምና ቁሳቁስ ማበርከት : ለሐኪሞች ምግብ ማቀበል : የሚሉንን መስማትና ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታችን ነው::

ፈጣሪ በሕክምና ሙያ ለሚደክሙ ዋጋ ሊሠጣቸው የታመነ ነው::

"በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና፡— ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ፡ አለው" ሉቃ 10:35

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Forwarded from Daregot Media
ውድ የዳረጎት መጽሔት አንባቢዎች

እነሆ ዳረጎታችን በቁጥር 6 ዕትሟ ወደ እናንተ ልትደርስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቷታል፡፡ ዳረጎትን ለመቋደስና ከማዕዷ ለመካፈል የምትሹ ሁሉ እጃችሁን ታጥባችሁ፣ ማህበራዊ ርቀታችሁን ጠብቃችሁና እንደው ግድ ካላለ በቀር ከቤት ሳይወጡ በጸሎት ተግተው እንዲጠብቁን እያልን ከቀናት በኀላ ዳረጎታችንን ይዘን እንቀርባለን፡፡

ከጥንቱም ተካፍሎ መብላት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነውና በዚህ ሰዓት ሥጋዊ መብል ላጡት ካለን እያካፈልን ለመንፈሳዊው መብል ደግሞ ዳረጎት ይዛ የቀረበችውን መጽሔታችንን ለሚወዱት እንዲያጋሩና ከገበታችን እንዲሰየሙ ( ፔጃችንን እንዲወዱልን) ከወዲሁ በክርስቶስ ፍቅር እንለምናችኀለን፡፡

Join Us @daregot
ማታ በሚቀርበው የፀሎት መርኀግብር ይባላሉ እንለማመዳቸው
Forwarded from Daregot Media
ይህንን መጽሔት ብላ!

በአምስት ተከታታይ መጽሔቶቿ ለአንባብያን የቀረበችው ዳረጎት መጽሔታችን በስድስተኛ ዕትሟም ወቅታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችን አካታ ወደ አንባቢያን ልትደርስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል፡፡ ዳረጎት መጽሔትን በቴሌግራም፣ ፌስቡክ ገጻችንና በቅርቡም በአዲስ መልክ በምንጀምረው ዌብሳይታችን መከታተል ይችላሉ፡፡

ከሊቃውንት ራቱን በልተው ከዳረጎት ጭማሪውን ይቋደሱ!

Join us @daregot
ቤት ነኝ ካሉ ዳረጎት ይጨመርሎታል!

በዚህ ጊዜ በቤት መሆን መልካም ነው፡፡ አባቶቻችንም ይህንኑ አጽንዖት ሰጥተው እየነገሩን ይገኛሉ፡፡ ሐኪሙም ከቤት እንድንውል መድኃኒቱን አመላክቶናል፡፡ ታዲያ ዳረጎትም መጽሔቱን አንብቡ ብላ ጨምራ አዛለች!

ከ5ቱ ዕትሞችና ከኦሮምኛ ትርጉም መጽሔታችን ያመለጣችሁ ካላችሁ እነሆ በአንድ አሰናድተንላችኀል፡፡ መርጠው ያንብቡ ሌሎችም ይጋብዙ፡፡ ያለው ይጨመርለታል ነውና በቅርቡ ደግሞ 6ኛውንም ዕትም እናደርሳለን፡፡

መጽሔቶቹን ለማግኘት👉 https://drive.google.com/folderview?id=104jrUcQm7tOB-9rH43NydM9V_rOF8mzP

በቤት መሆን መልካም ነው!

በቴሌግራም 👉 @daregot

በድረገጻችን 👉 www.daregot.com
በዚህ ዓለም የሰው ልጅ ሊገጥመው የሚችለው ፈተና ሁሉ በሦስቱ አርዕስተ ኃጣውእ ውስጥ ተጠቃለው ይገኛሉ ይላሉ አበው፡፡ ስስት እና ፍቅረ ንዋይን ለጊዜው እንተወው፡፡ አሁን ኮረና ቫይረስ ጎትቶ ጫፍ ላይ አቁሞናል፡፡ እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁና ይታደጋችኋል የሚለው ጭወት የብዙዎቻችንን የጥንቃቄ ግንብ እንዳይደረምሰው ያሰጋኛል፡፡ መቼስ መድኃኒዓለም በተፈተነበት ሰዓት ነው ያለነው፡፡ ይሄ ፈተና ከእኩዮች እንደሆነ ሕዝበ ክርስቲያኑ መገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም መግቦቱ (ፀሐይን በማውጣት ዝናብን በመስጠት) በፍጥረቱ መኃል ልዩነት አያደረግም ያለው “እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ተጽፏል” የሚለው የዚህ ፈተና መውጫ ጋር ተመሳስሎ ታይቶኛል፡፡ በእኛ ቤተክርስቲያን የሚከበሩ አስተማሪዎች ሳይቀሩ ይሄን በሽታ ከመቅሰፍተ አምላክ ጋር በማያያዝ ሰውን ከቤተክርስቲያን ራስ ላይ ለመወርወር ሲጥሩ ይታያሉ፡፡ ይሄን በሽታ በተአምር አይደለም የምንሻገረው፡፡ የምንሻገረው ተአምርን መሻት በማቆም ነው፡፡ ከቻይኖቹ ይልቅ ስመ-እግዚአብሔር የተጠራባቸው አካባቢዎች በይበልጥ አልቀዋል፡፡ ይሄ በራሱ በቂ ትምህርት ነው፡፡ ትዕቢት ካልያዘን በቀር እኛ ከማንም የተሻል አይደለንም፡፡ ለእኛም በተለየ ሰይጣን እያለን እንዳለው የሚታዘዝልን መላዕክት አይኖርም፡፡ ትልቁ ተአምር እስካሁን የተደረገልን ነው፡፡ በሽታው ያደጉትን ዓለማት ካዳረሰ በኋላ ነው ወደ እኛ የመጣው፡፡ አንድም የመማሪያ ጊዜ ሰጥቶናል፡፡ ሌላም የመድኃኒቱ የመገኛው ጊዜ ቢያንስ እስካሁን በወሰደው ጊዜ አጥሯል፡፡ የሰው ልጅ ትልቁ ስጦታው የማሰብ አቅሙ ነው፡፡ የማሰብ አቅማችንን ሊያደነዝዝ የሚችለው ሰይጣን እና ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ከእውቀታችን የሚያጣላንን ስብከት ገሸሽ አድርገን የሕክምና ሰዎችን እንስማ፡፡ እሱን ስሙት የሚለው የድንግል ማርያም ጥሪ ዛሬ እግዚአብሔር ሃይማኖት ሳይለዩ ሰውን ሁሉ እንዲያገለግሉ የእሱን እውቀት ያካፈላቸውን የሕክምና ሰዎች እንድንሰማ ይዋል፡፡
መልካም ምሽት