ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
መጻጉ ዮሐ.፭፡፩-፳፭ ድውያንን እንዴት አርጎ ፈወሳቸዉ;
በዚህ የአራተኛ የአብይ ጾም ሳምንት አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ በሽታዎች ያሏቸውን ሰዎች ፈውስ እንደሰጣቸው ይሰበክበታል። በተለይም ለእነዚህ በሽተኞች ጌታችን ፈውስን ያደረገላቸው በሰንበት በመሆኑ በሰንበት መልካም ሥራን መሥራትን፤ የታመመ መጠየቅን፤ ያዘነ ማጽናናትን፤ የደከመ መርዳትን፤ የነፍስ ረሐብ ያለበትን በቃለ እግዚአብሔር ማበርታትን እና ተመሳሳይ ሥራዎችን መሥራት ተገቢ እንደሆነም ይሰበክበታል። የሰንበት ቀን የተቀደሰች ዕለት ናትና በሰንበት ክርስቲያኖችን ማበርታት፣ መጠየቅ እና ለሕይወታቸው ተገቢውን መንገድ የምናሳይበት እንጂ የግል ሥራ የምንሠራበት አለመሆኑም ይሰበክበታል። አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት መልካም በማድረጉ ከአይሁድ እና ከፈሪሳውያን ፈተና ቢገጥመውም በሰንበት መልካም ከማድረግ ግን ወደ ኋላ አላለም። እኛም በሰንበት የቤተ ክርስቲያንን ነገር ብቻ እንድናደርግ በማሰብ በሰንበት ያልተፈቀደውን ትተን የተፈቀደውን ብቻ ለማድረግ የተዘጋጀን መሆን ይገባናል። ጌታችን የፈወሰበትን እና በሰንበትም ፈውስን ካገኙ ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት፦
ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም፥ ለምጻም ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት። እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወዳለሁ፥ ንጻ አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ። ኢየሱስም። ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ አለው። ወደ ቅፍርናሆምም በገባ ጊዜ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል ብሎ ለመነው። ኢየሱስም። እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ አለው። የመቶ አለቃውም መልሶ። ጌታ ሆይ፥ በቤቴ ጣራ ከታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል። እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፥ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም። ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም። ና ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም። ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል አለው። ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም። እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤ የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። ኢየሱስም ለመቶ አለቃ። ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ። ኢየሱስም ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤ እጅዋንም ዳሰሰ፥ ንዳዱም ለቀቃት፤ ተነሥታም አገለገለቻቸው። ማቴ.፰፡፩-፲፭
ከኢያሪኮም ሲወጡ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን ብለው ጮኹ። ማቴ.፳፡፳፱-፴
ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ። ደቀ መዛሙርቱም። መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ። የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም። ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች። በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ። ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና። ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ። ዮሐ.፱፡፩-፯
አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት። ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፥ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን። አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።ከጻፎችም አንዳንዶቹ በዚያ ተቀምጠው ነበር በልባቸውም። ይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው አሰቡ። ወዲያውም ኢየሱስ በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ በመንፈስ አውቆ እንዲህ አላቸው። በልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ? ሽባውን። ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ። ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል? ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤ ሽባውን። አንተን እልሃለሁ፥ ተነሣ፥ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው። ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፥ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።ማር.፪፡፫-፲፪
በዚህ በአራተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦ እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ ሠይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣህለኒ
በአማርኛ፦ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል። እኔስ። አቤቱ ማረኝ፤ እልሃለሁ። መዝ.፵፡፫-፬
በዚህ ቀን እሚነበበዉ ወንጌል
ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው። ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ኢየሱስ። ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት። እርሱ ግን። ያዳነኝ ያ ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። እነርሱም። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰው ማን ነው? ብለው ጠየቁት። ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ሰለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና። እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው። ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ። ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር። ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው
ይፈልጉት ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል። አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል። ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ። ዮሐ.፭፡፩-፳፭
እንኳን አደረሰን መልካም በዓል ፡፡
#መጻጉዕ

❖ እግዚኦ ተሣሃለኒ
❖ አቤቱ ማረኝ
❖ Yaa Waaqayyo anaaf oo'i

መዝ. 41:4 / Far 41:4

JOIN US @daregot
ኮረና ቫይረስ
ከውሃን ተነስቶ ዓለምን በሁለት ወር ውስጥ ያዳረሰው ኮረና ቫይረስ ዛሬ የሁሉም ሰው ራስ
ምታት የሆነ ይመስላል፡፡ እኔ ያለውበት ዩኒቨርስቲ እና ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ቢያንስ ለአንድ
ወር የክፍል ውስጥ ትምህርት መቋረጡን አውጀዋል፡፡ ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ መግባት
ከአርብ ጀምሮ ታግዷል፡፡ ትላንት የኮንግረስ የጤና ባለሙያ ለኮንግረሱ ባደረጉት ገለጻ
በአሜሪካ ውስጥ ብቻ እስከ 150 ሚሊዮን ሕዝብ በቫይረሱ ሊጠቃ እንደሚችል
ተናግረዋል፡፡ ይሄ ማለት የአሜሪካ ግማሽ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በቀጣይ ቀናት
ከተጠቂዎች ውስጥ አንዱ የመሆን ዕድሌ ከ100% ግማሹ (50%) ነው ማለት ነው፡፡
የተወረረ ከተማ ይመስል ሁሉ ነገር ዝም ብሏል፡፡
የሰው ልጅን የሥልጣኔ ደረጃ ወይስ የሥልጣኔ ገደብ የሚያሳይ ነው የሚለው የምር
የሚያከራክር ነው፡፡ በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ዓለማችን በአንዴ ጸጥ ድርግም
ማለት እንደምትችል የታየበት ወቅት ነው፡፡ የማይክሮ ሶፍት ባለቤት ቢል ጌት እንደተናገረው
በአፍሪካ ውስጥ በብዙ ሚሊዮኖች የሚጠጋ ሕዝብ ቫይረሱ ሊጨርስ ይችላል፡፡ ያደጉ
አገሮች በዚህ ሰዓት አይደለም ለአፍሪካ ሊደርሱ ለራሳቸውም ማጠፊያው አጥሯቸዋል፡፡
ቫይረሱ ሙቀት ባለበት ሥፍራ አይቆይም የሚለውም ከትላንት በስቲያ የአሜሪካ
ሳይንቲስቶች ቫይረሱ በአየር ላይ እስከ 7 ቀን የመቆየት አቅም እንዳለው ከገለጹ በኋላ እና
የመካከለኛው ምስራቅ አገራት በስፋት መጠቃት ከጀመሩ በኋላ ብዙ ተቀባይነት ያለው መላ
ምት አልሆነም፡፡ ቫይረሱ በእድሜ የገፉ ሰዎችን ብቻ ነው ለሞት አደጋ የሚያጋልጠው
የሚለውም ሁልጊዜ እውነት አይደለም፡፡ በሚኒሶታ ግዛት ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የጤና
እንከን የሌለበት የ30 ዓመት ጎልማሳ ከሸመገሉት ሰዎች በላይ በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ
(critical condition) ውስጥ መገኘቱ አስገራሚ አድርጎታል፡፡
የጤና አጠባበቅ ሁኔታው በጣም ዝቅተኛ በሆነው እና የሰውነት ንክኪ ከፍተኛ በሆነበት
ኢትዮጵያ ቫይረሱ በእጅግ ፈጣን ሁኔታ ሊዛመት እንደሚችል ግምቴ ነው፡፡ ለ15 ቀን ምንም
ዓይነት ምልክት ሳያሳይ እና ከምርመራ ውጤት ተሰውሮ መቆየት የሚችለው ቫይረሱ
በኢትዮጵያ ዓይር መንገድ ጣቢያ ላይ ተኮልኩለው በተሰለፉ የጤና ባለሙያዎች ብርታት
ኢትዮጵያ ድርሽ አላለም ማለት እጅግ ሲበዛ ሞኝነት ይመስለኛል፡፡ ማህበረሰቡ በከፍተኛ
ደረጃ በጉዳዩ ላይ መወያየት መጀመር መቻል አለበት፡፡ በድኅነት አቅማችን ይሄን ጉድ
እንዴት መወጣት እንዳለብን በፍጥነት ካልታሰበበት ብዙ ሕዝብ ሊያልቅ እና አገሪቷንም
ክፉኛ ሊጎዳት ይችላል፡፡ (ከታች ያለው ምስል ዛሬ በታርጌት ሱፐር ማርኬት ውስጥ የተነሳ
እና የሳሙና እና የንጽህና መጠበቂያ ስፍራው እንዴት ባዶ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡
ከሙሉአለም ጌታቸው
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያድርጉ

1.እጆችዎን አዘውትረው በሳሙና እና በውኃ ይታጠቡ፣

2. ሳይታጠቡ አይንዎትን፣ አፍንጫዎትንና ፊትዎትን ከመንካት ይቆጠቡ፣

3. ሕዝብ በሚጨናነቅበት ቦታዎች አይገኙ፣

4. በሚያስነጥሱበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎትን በክርንዎ ወይም በመሀረብ ይሸፍኑ፣

5. ጥሩ ያልሆነ ስሜት ከተሰማዎ ከቤት አይውጡ፣

6. ትኩሳት፣ሳልና ለመተንፈስ መቸገር ካለ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሕክምና ማዕከል ይሂዱ፣

7. ስለ በሽታው ከጤና ባለሞያዎች እና ከመንግስት ኃላፊዎች የታመነ መረጃ ይውሰዱ፡፡

ሁላችንንም እግዚአብሔር ይጠብቀን

Join Us @Daregot
ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!
በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ
ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን
ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት
እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!< ከሮና ቫይረስ
የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ
የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡
< ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ
ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ
ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ
አይደለም፡፡
< በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ! <
የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡
1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ
ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን
የለበትም። ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡
< በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን
የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡
< አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ
ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡
2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት
ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣
የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ
በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡
3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡
ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች
ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ
ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች
#ምን ምንድን ናቸው?
1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ
ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::
2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ
በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡
ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ
በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?
1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን
ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም
ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላበተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን
ያስገነዝበናል፡፡
ሁሉን የሚይዝ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን
እንለምነው ወይም እንማልደው፤ ስለታመሙ ወንድሞቻችን፤ በሽታን ሁሉ ህማምንም ሁሉ
ከእነርሱ ያርቅ ዘንድ የበሽታን መንፈስ ሁሉ ሽሮ አጥፍቶ በፈውስና በጤና ሁሉ ሥልጣን
ያለው እግዚአብሔር አምላካችን ጤንነትና ሂወትን ይሰጣቸው
ስለታመሙት ጸልዩ
ሁሉን እግዚአብሔር ስለታመሙ ወንደወሞቻችንና እቶቻችን እለምህንሃለን እንማልድሃለን
በሽታ ሁሉ ደዌን ሁሉ ከእነርሱ አርቅ የደዌን መንፈስና ኀይል ሻር ደዌን ሁሉ በሽታን ሁሉ
ከእነርሱ አሳልፍ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን
አቤቱ ይቀር በለን
የነፍስና የሥጋ መድኀኒት የምትሆን ፍጥረትን ሁሉ በምህረት የምትጎበኝ አንተ፤ በክፉ በሽታ
የተቸከረሽውንና የተጨነቀሽውን ነፍስ፤ በኩፉ መናፍስት ለሚጨነቁት ሁሉ እረፍትን ስጥ፡፡
ደዌና በሽታን ከዚህ ቤትና ከሀገሪቱ አርቅ ቅዱስንና ብሩክ ስምህን ከሚያመልኩና
ከሚጠሩ ሁሉ አርቅ፡፡ በአንድ ልጀህ በኢየሱስ አርስቶስ ፤ ከልጅህና ከመንፈስ ቅድስ ጋራ
አንድ ሥልጣን ያለህ፡ ክብር ሥልጣን ለዘለአለሙ የአንተ ብቻ ነው አሜን
ምሁር ኢየሱስ ገዳም ክፍል አንድ
አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ተዘዋውረው ሲያስተምሩ በወቅቱ ማዕከል አድርገው የሚነሱበት እና የሚደርሱበት ስፍራ ይህ ታላቅ ገዳም ምሁር ኢየሱስ ገዳም ነበር ፡፡

አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ በመላው ምሁር ለተከሏቸው መቶ ሃምሳ ስድስት አብያተ ክርስቲያኖች የበላይ ጠባቂና አስተዳዳሪ አንድ ንቡረዕድ በምሁር ኢየሱስ ሾመው እና አስቀምጠው እሳቸው ግን ዛሬ አሬብ ተብሎ ወደሚጠራው ዋሻ በመሄድ በፍፁም ብህትውና በፆም በፀሎት እና በስግደት ተወስነው እንደኖሩ የአባታችን ገድል በምሁር እና በጎጎት አርባ ዘመን ተሰውረው ቆዩ ሲል ይነግረናል፡፡

አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ የአራዊት ድምፅ የአጋንንት ትንኮሳና የለሊቱን ጨለማና ግርማ ታግሰው በፍፁም ብህትውና ለ አርባ አመታት የተጋደሉበት ዋሻ ከምሁር ኢየሱስ አጠገብ በስተ ሰሜን ዛሬ ድረስ ይታያል፡፡ የአባታችንን ፈለግ የተከተሉ እግዚአብሔር በድንቅ አጠራሩ የጠራቸው ብዙ የበቁ ቅዱሳን ከሰው ተሰውረው በዚህ አካባቢ ይኖራሉ፡፡
በአባታችን ስም እና በሌሎች ቅዱሳን ስም በፀሎታቸው ሀይል በእግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃድ ከመሬት ውስጥ የፈለቀው ጸበል ለብዙ ህሙማን ፈውስን እየሰጠ በዋሻ ውስጥ ዛሬ ድረስ ይገኛል፡፡

ከአስራ አምስት ዓመት በፊት በ፲፱፻፺፯ ዓ.ም በብፁዕ አቡነ መልከፄዴቅ ከፍተኛ ድካም እና ጥረት በአባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ስም ይህ ዋሻ በሚገኝበት አካባቢ ቤተክርስቲያን ተሰርቷል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው እና ብቸኛው የንቡረዕድ መቀመጫ ሆኖ እስከ አስራ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የዘለቀው የምሁር ኢየሱስ ገዳም ብዙ ድንቅ ታሪክ የተመዘገበበት ስፍራ ነው፡፡
፭ኛ ሳምንት ደብረ ዘይት/
የአብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት /ደብረ ዘይት/፦
በዚህ የአምስተኛ የአብይ ጾም ሳምንት አምላካችን ጌታችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዳግም ምጽአቱ የተናገረበት፤ ስለ መጨረሻው ዘመን
አስቀድሞ የገለጸበት ታሪክ ይነገርበታል። በዚህ ሳምንት የሚሰጠው የትምህርቱ ሙሉ ስብከት
በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፤ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፫፤ እንዲሁም በሉቃስ ወንጌል
ምዕራፍ ፳፩ ላይ ተጽፎ ይገኛል። ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ክርስቶስን የመምጣትህና የዓለም
መጨረሻ ምልክት ምንድር ነው? ብለው በጠየቁበት ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦
ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥
ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ
ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም
በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ
ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።...ወንድምም ወንድሙን አባትም
ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ።
ይገድሉአቸውማል፤ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ
መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።... በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው
ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ
ዓይነት ይሆናልና። ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን
ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ። ማር.፲፫፡፭-፳
ስለዚያች ቀን አስፈሪነትና ታላቅ መታወክ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ
ሲናገር ስለመረጣቸው ምርጦች ሲል ወራቶቹን ባያሳጥር እነዚያ ጊዜያቶች እጅግ አስፈሪ
ነበሩ። በምድር ላይ በቅድስና ስለኖሩት ቅዱሳን ሰዎች ሲባል እግዚአብሔር ቁጣውን በምሕረት
እንደሚመልስ ሰፋ ያለ ትምህርት ይሰጥበታል።
በዚህ በአምስተኛው ሳምንት በቅዳሴ ላይ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሙሉው ምንባብ
ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦
9ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን። ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ
ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።
በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር
ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ
በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው
ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል
ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ። ፩ተሰ ፬፡፲፫-፲፰
አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት
እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል። እናንተ ግን ወዳጆች
ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን
እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ። ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ
ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም
እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤
በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት
ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል። ይህ ሁሉ እንዲህ
የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥
በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን
ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤ ነገር ግን
ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።
ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም
በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥ የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ።
እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን
ጻፈላችሁ፥ በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ።
፪ኛ ጴጥ፫፡፯-፲፭
ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት። በተጠራም ጊዜ
ጠርጠሉስ ይከሰው ዘንድ ጀመረ እንዲህ እያለ። ክቡር ፊልክስ ሆይ፥ በአንተ በኩል
ብዙ ሰላም ስለምናገኝ ለዚህም ሕዝብ በአሳብህ በየነገሩ በየስፍራውም መልካም
መሻሻል ስለሚሆንለት፥ በፍጹም ምስጋና እንቀበለዋለን። ነገር ግን እጅግ እንዳላቆይህ
በቸርነትህ በአጭሩ ትሰማን ዘንድ እለምንሃለሁ። ይህ ሰው በሽታ ሆኖ በዓለም ባሉት
አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሣ፥ የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ
አግኝተነዋልና፤ መቅደስንም ደግሞ ሊያረክስ ሲሞክር ያዝነው፥ እንደ ሕጋችንም
እንፈርድበት ዘንድ ወደድን። ነገር ግን የሻለቃው ሉስዮስ መጥቶ በብዙ ኃይል
ከእጃችን ወሰደው፥ ከሳሾቹንም ወደ አንተ ይመጡ ዘንድ አዘዘ፤ አንተም ራስህ
እርሱን መርምረህ እኛ ስለምንከስበት ነገር ሁሉ ልታውቅ ትችላለህ። አይሁድም
ደግሞ። ይህ ነገር እንዲሁ ነው እያሉ ተስማሙ። ገዡም በጠቀሰው ጊዜ ጳውሎስ
መለሰ እንዲህ ሲል። ከብዙ ዘመን ጀምረህ ለዚህ ሕዝብ አንተ ፈራጅ እንደ ሆንህ
አውቃለሁና ደስ እያለኝ ስለ እኔ ነገር እመልሳለሁ፤ እሰግድ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም
ከወጣሁ ከአሥራ ሁለት ቀን እንዳይበልጥ ልታውቀው ትችላለህ። ከአንድም ስንኳ
ስነጋገር ወይም ሕዝብን ስሰበስብ በመቅደስ ቢሆን በምኵራብም ቢሆን በከተማም
ቢሆን አላገኙኝም። አሁንም ስለሚከሱኝ ያስረዱህ ዘንድ አይችሉም።
ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ
የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤
እነዚህም ራሳቸው ደግሞ የሚጠብቁት፥ ጻድቃንም ዓመፀኞችም ከሙታን ይነሡ ዘንድ
እንዳላቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ። ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና
በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ። ከብዙ ዓመትም
በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤ ይህንም ሳደርግ ሳለሁ
ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።ነገር ግን በእኔ ላይ ነገር
ያላቸው እንደ ሆነ፥ በፊትህ መጥተው ይከሱኝ ዘንድ የሚገባቸው ከእስያ የመጡ
አንዳንድ አይሁድ አሉ። ወይም በመካከላቸው ቆሜ። ዛሬ ስለ ሙታን መነሣት
በፊታችሁ በእኔ ይፈርዱብኛል ብዬ ከጮኽሁት ከዚህ ከአንድ ነገር በቀር፥ በሸንጎ ፊትቆሜ ሳለሁ በእኔ አንድ ዓመፃ ያገኙ እንደ ሆን እነዚህ ራሳቸው ይናገሩ። ፊልክስ ግን
የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና። የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን
እቆርጣለሁ ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው። ሐዋ.፳፬፡፩-፳
በዚህ በአምስተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦ እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
በአማርኛ፦ እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።
አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤
እሳት በፊት ይቃጠላል፥ መዝ. ፵፱(፶)፡፫
በዚህ በአምስተኛው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦
ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት
ቀረቡ
። እርሱ ግን መልሶ። ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ
በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ
ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል?
የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት። ኢየሱስም መልሶ
እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ
እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ
አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና
ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም
የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ
ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም
በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ
በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች
ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር
ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ለአሕዛብም ሁሉ ምስክርእንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው
ይመጣል። እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ
ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች
ይሽሹ፥ በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥ በእርሻም ያለ ልብሱን
ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ። በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ
ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤ በዚያን
ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን
ታላቅ መከራ ይሆናልና። እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤
ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ። በዚያን ጊዜ ማንም። እነሆ፥
ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም። ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና
ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ
ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ። እንግዲህ። እነሆ፥
በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤
መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ
ይሆናልና፤ በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ። ከዚያች ወራትም መከራ
በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም
ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ
ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥
የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም
ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ
ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ። ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ
ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁ
እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ
ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን
አያልፍም። ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ
መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። ማቴ.፳፬፡፩-፴
Forwarded from Daregot Media
#ደብረዘይት

ሰላም እብል ለምጽአትከ ከዋላ በደመና ሰማይ ልዕልት እንተ ይብልዋ ጌልጌላ አመ ትመጽእ ክርስቶስ ርዕሰ መሐላ ጸውአነ ለአግብርቲከ ውስተ ዐፀደ ፍግዕ ወተድላ ናንሶሱ ምስሌከ በሐዳስ በቀፀላ
❖❖❖

ጌልጌላ ብለው በሚጠሯት በሰማይ ደመና ላይ ለሚሆነው ለኃለኛው ምጽአትህ ሰላም እላለው። ፍፁም ደስታ ባለበት ሥፍራ አዲስ የሆነውን ዘውድ ለብሰን ካንተ ጋራ እንመላለስ ዘንድ የቃል ኪዳን ፍጻሜ የሆንክ ክርስቶስ ሆይ በጌትነትህ በመጣህ ጊዜ እኛ ባሮችህን ጥራን።
❖❖❖

Gelgelaa jedhanii kan waamanif dhufatii ke boodaa duumessa samiirraa olitti ta'uuf nagaan jedha.Gammachuun gonkummaa iddoo jirutti;gonfoo haaraa uuffannee siwaliin akka deddebinuuf yaa Kiristoos dandama waadaa kan taate yeroo mootummaa keetin dhufte nu garboota kee waami.

[ ማቴ 24፥64 ፣ ዕብ 7፣1-28፣ ራዕ2፥10፣ሥራ 1፥11 / Maat.24÷64, Ebro.7÷1-28,Mul.2÷10,Duu 1÷11 ]
መልክዓ ኢየሱስ

JOIN US @daregot
ራሳቸውን እብድ ያደረጉ ቅዱሳት መነኮሳይያት!
ቅዱስ ጳኩሚስ ከመሠረታቸው ገዳማት መካከል ከወንዶች ገዳማት ራቅ ብሎ የተመሠረተ
የሴቶች ገዳም ነበር። በዚያም ውስጥ አራት መቶ ሴቶች መነኮሳይያት ይኖሩ ነበር። በዚያ
ገዳም ውስጥ ራሷን እንዳበደችና ርኲስ መንፈስ እንደያዛት የምታስመስል ድንግል ነበረች።
ሌሎቹ እርሷን ከመጸየፋቸው የተነሣ አብረዋት እንኳን አይበሉም ነበር፤ እርሷ ግን ይህን
ወደደችው። በምግብ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ወዲያ እና ወዲህ ትንከራተታለች፣ ሌሎች
የተዉትንና የተናቀውን ማንኛውም ሥራ ትሠራለች፣ እነርሱ እንደሚሉት "የገዳሙ ቆሻሻ
አስወጋጅ" ነበረች። በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ከእህቶች መነኮሳይያት መካከል ማንም በአፏ
ስታላምጥ አይተዋት አያውቁም፣ በማዕድም ተቀምጣ አታውቅም ነበር። ከማዕድ
የሚወድቀውን ፍርፋሪና የማዕድ ቤት እቃዎችን ስታጥብ ከዚያ በሚገኘው ነገር ብቻ ትኖር
ነበር። ማንንም ተሳድባ ወይም ትንሽም ሆነ ብዙ አውርታ አታውቅም፤ ምንም እንኳ ብዙ
ትሰደብ፣ ትነቀፍና ትረገም የነበረች ብትሆንም።
የእግዚአብሔር መልአክ ፒተሮአም ለሚባል ታላቅና ታዋቂ ለነበረ ታላቅ ባሕታዊ
ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦ "እንዲህ ባለ ቦታ ስለመኖርህና ስለ ሃይማኖተኛነትህ ለምን
በራስህ ትመካለህ? ከአንተ የበለጠ ሃይማኖተኛና ፍጹም የሆነችን ሴት ማየት ትፈልጋለህ?
ወደ ታቤኔሲዮት ገዳም ሴቶች ሂድ በዚያም በራሷ ዘውድ የደፋች ሴት ታገኛለህ። እርሷ
ከአንተ የበለጠች ናት፤ በብዙዎች መካከል ብትሆንም ልቧ ከፈጣሪዋ ከእግዚአብሔር
ውጪ እንዲሄድ ፈጽሞ ፈቅዳለት አታውቅምና፣ አንተ ግን እዚህ ተቀምጠህ በሃሳብ
በተለያዩ ቦታዎች ትዞራለህና" አለው።
ይህን ሲሰማ ከበኣቱ ወጥቶ የማያውቅ የነበረው ባሕታዊ ወደዚያ ገዳም ሄደና ወደ ገዳሙ
ለመግባት ጠየቀ። የታወቀና በዕድሜው የገፋ አረጋዊ ባሕታዊ ስለነበር ወደ ሴቶቹ ገዳም
እንዲገባ ፈቀዱለት። በዚያም ሁሉንም መነኮሳይያት ያያቸው ዘንድ ጠየቀ። ሆኖም እርሷ
አልመጣችም። በመጨረሻም፦ "የቀረች አንዲት አለችና ሁሉንም አምጡልኝ" አላቸው።
እነርሱም፦ "በማዕድ ማዘጋጃ ቤት ያለች አንዲት እብድ ብቻ ናት የቀረችው" አሉት።
እርሱም፦ "እርሷንም ጭምር አምጡልኝና ልያት" አላቸው። ሊጠሯት ሄዱ እርሷ ግን ነገሩን
አውቃው ይሁን ወይም ጉዳዩ ተገልጦላት መልስ አልሰጠቻቸውም። በግድ ጎተቷትና፦
"ታላቁ ፒተሮአም ሊያይሽ ይፈልጋል" አሏት። በመጣች ጊዜ ከራሷ ላይ ያለውን ብጣሽ
ጨርቅ አሰበና ከእግሯ ላይ ወድቆ "ባርኪኝ" አላት። እርሷም እንዲሁ ከእግሩ ላይ ወድቃ
"አባቴ ሆይ አንተ ባርከኝ" አለችው። ሁሉም መነኮሳይያት ተገረሙና፦ "አባ እንዳትሰድብህ
ተጠንቀቅ እብድ ናት" አሉት። አባ ፒተሮአምም ሁሉንም፦ "እብዶችስ እናንተ ናችሁ እርሷ
ግን የእኔም የእናንተም እናት ናት። በፍርድ ቀንም እንደርሷ የተዘጋጀሁና የተገባሁ ሆኜ እገኝ
ዘንድ ምኞቴ ነው" አላቸው።
እነዚህን ነገሮች ከዚህ አባት ሲሰሙ ሁሉም ያደረጉባትን ነገር እየተናዘዙ ከእግሩ ላይ
ወደቁ። አንዲቱ የውኃ እጣቢ አፍስሼባታለሁ ትላለች፣ ሌላዋ ደግሞ መትቻታለሁ ትላለች፣
ብቻ ብዙዎች አንዷ አንድ ሌላዋ ደግሞ ሌላ ነገር እንደፈጸሙባት በመናገር ይናዘዙ ጀመር።
እርሱም ከጸለየላቸው በኋላ ሄደ። ከጥቂት ቀናት በኋላ በእህቶቿ መነኮሳይያት
የሚደረግላትን ክብር መሸከም ስለከበዳት እንዲሁም ፊት በበደሏት ነገር ሁሉ ይቅርታ
አድርጊልን የሚሉት ነገራቸው ስለበዛባት ገዳሙን ጥላ ጠፋች። ወዴት እንደሄደችም ሆነ
የት እንደተሰወረች ወይም እንዴት እንደሞተች ግን ማንም ያወቀ የለም።
+ + +
ዳግመኛም ቅድስት መነኩሴ ሆና ሳለ እርሷ ግን ራሷን እብድ አስመስላ ስለኖረችው
ቅድስት አናሲማ እንነግራችኋለን፦ ይኽችም ቅድስት አናሲማ በደናግል ገዳም መንኩሳ
በታላቅ ተጋድሎ የምትኖር ስትሆን እርሷ ግን ራሷን እብድ አስመስላ ኖረች፡፡ በሌሊትም
በጾምና በጸሎት ሥጋዋን በመቅጣት ራሷን ታሠቃያለች፡፡ ሰዎችም በሚያዩዋት ጊዜ
አእምሮዋን ያጣች እንደሆነች ታስመስላለች፡፡ መበለቶችም ይሰድቧታል፡፡ እጅግ ገድላኛው
የሆነው ጻድቁ አባ ዳንኤል በአንዲት ዕለት ከደናል ገዳም ደርሶ ደጁን አንኳኳ፡፡ እነርሱም
የከበረ አባ ዳንኤል መሆኑን ዐውቀው ከፈቱለት፡፡ ይኽችም ቅድስት አናሲማ በዚያ ራሷን
እብድ አስመስላ በደጅ የምትተኛ ሴት ነበረች፡፡ የከበረ አባ ዳንኤልም እብድ መስላ በደጅ
ስለተቀመጠችው ቅድስት አናሲማ እመ ምኔቷን ሲጠይቃት እብድ መሆኗን ነገረችው፡፡ አባ
ዳንኤል ግን እብድ የመሰለቻቸው አናሲማ እብድ ሳትሆን በድብቅ በታላቅ ተጋድሎ
የምትኖር የከበረች ቅድስት መሆኗን ነገራት፡፡
እብድ መስላ ትኖር ነበረችውና በሁሉም ዘንድ እብድ የተባለችው ቅድስት አናሲማም አባ
ዳንኤል ምሥጢሯን እንደገለጠባት በጸጋ አውቃ ወዲያው ደብዳቤ ጽፋ ይኸውም
‹‹የተከበራችሁ እኅቶቼ ስላስቀየምኳችሁና ስላሳዘንኳችሁ ይቅር በሉኝ›› ብላ ጽፋ
ደብዳቤውን አስቀምጣ ከንቱ ውዳሴን በመሸሽ ጥላቸው ጠፋች፡፡ እነርሱም ከዚያ በኋላ
ዳግመኛ አላዩአትም፡፡ ቅድስት አናሲማም በዚያው በበረሃ ሳለች በሰላም ዐረፈች፡፡
የቅድስት አናሲማ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን!
እኛስ የቅዱሳን አባቶቻችንን አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን እያገለገልነው ይሆን?
Forwarded from Daregot Media
#ገብር_ኄር

" ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።"

"Gooftaan isaa immoo, 'Ba'eessa goote, hojjetaa gaarii dhaa fi amanamaa nana, ati waan xinnoo irratti amanamte, ani immoo waan guddaa irra sin dhaaba; gammachuu gooftaan kee itti jiraatutti gali!' jedheen."

(ማቴ 25: 21 / Matt 25:21 )

#በቤትመሆንመልካምነው
#stayathome
#Manaturuungaaridha!

Join us @daregot
አ ብ ይ ጾ ም
/፮ኛ ሳምንት ገብርኄር/
የአብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት /ገብርኄር/፦
በዚህ የስድስተኛ የአብይ ጾም ሳምንት አምላካችን ጌታችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መክሊት ተሰጥቷቸው ለነበሩት አገልጋዮች
ያስተማረው ትምህርት፤ ታማኝነት ምን ያህል ጥቅም እንዳለው፤ የሃይማኖትን ነገር ገንዘብ
አድርጎ በመንፈስ ፍሬዎች በመታገዝ ጠቃሚ የሆኑ ሥራዎችን በመሥራት መክሊትን ማትረፍ
እንደሚገባ ይሰበክበታል። እያንዳንዳችን በተሰጠን እና በምናውቀው የአገልግሎት መንገድ
እንድንሰማራ፤ ፀጋችንን አውቀን የእግዚአብሔርን ፍጥረት በሚያስፈልገው ሁሉ እንድንረዳ
ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን አደራ መወጣት ይኖርብናል። የተሰጠንን መክሊት ደብቀን
ሳናተርፍበት ካስቀመጥነው በመጨረሻው ሰዓት በተሰጠን ፀጋ ምን እንዳደረግን ስንጠየቅ
በታማኝነት መክሊታችንን አስቀምጠናል ብንል መልሱ እጅግ አስከፊ ነው። እያንዳንዱ
የሰውነታችን ብልት የየራሱ ሥራ እንዳለው ሁሉ ከእግዚአብሔርም ለእያንዳንዳችን እንደ
ፀጋችን የምናገለግልበት ልዩ ልዩ ዓይነት ስጦታ አለን። እንደ ሥራ ሊከፍል ወልደ
እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን ሲመጣ አትርፈን እንጂ ያለንን ጥለንና የተሰጠንን ቀብረን
የምንጠብቅ መሆን የለብንም።
ቸር አገልጋይ ተብሎ የሚጠራ፤ በተሰጠው ሥራ ሁሉ ተሰልፎ መልካም
የሚያደርግ ማን ነው? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ የተሰጠው አደራ እጅግ ከፍተኛ
መሆኑን ስለተረዳ እና የተጠራበትም ጉዳይ የወንጌልን ነገር በዓለም ማሰራጨት መሆኑን
ስላመነበት ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ በማለት ታማኝ እና ቸር አገልጋይ መሆኑን ተናግሯል።
ነብዩ ሙሴ ሕዝብ እንዲያስተዳድር የተሰጠው አደራ ከእግዚአብሔር በመሆኑ ታማኝነቱን እና
ቸር እረኛ መሆኑን ሲያስተምር ለሕዝበ እስራኤል ደጋግሞ በምልጃ ሲቆምላቸው ተሰምቷል፤
ተስተውሏል። በሙሴ እግር ተተክቶ የገባው ነብዩ ኢያሱም የእረኝነት ኃላፊነቱን እና ቸር
አገልጋይነቱን በፈቃደ እግዚአብሔር ሲወጣና ከሕዝበ እስራኤል ጋር ቃል ሲገባባ ተሰምቷል።
በመጽሐፈ ኢያሱም የአገልጋይነት አደራውን እንዴት መወጣት እንዳለበት እና ሕዝቡም
እንዴት ቃል እንደገባለት እንዲህ ሲል ተጽፏል፦ ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች። በሰፈሩ መካከል እለፉ፥ ሕዝቡንም።አምላካችሁ
እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ምድር እስከ ሦስት ቀን ይህን ዮርዳኖስን
ተሻግራችሁ ልትወርሱአት ትገቡባታላችሁና ስንቃችሁን አዘጋጁ ብላችሁ እዘዙአቸው
ብሎ አዘዘ። ኢያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ
እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። የእግዚአብሔር ባርያ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛችሁን ቃል
አስቡ። አምላካችሁ እግዚአብሔር ያሳርፋችኋል፥ ይህችንም ምድር ይሰጣችኋል።
ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ ከብቶቻችሁም ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር
ይቀመጡ፤ ነገር ግን እናንተ፥ ጽኑዓን ኃያላን ሁሉ፥ ተሰልፋችሁ በወንድሞቻችሁ
ፊት ተሻገሩ፥ እርዱአቸውም፥ እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን
እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር
እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ
ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱአትማላችሁ። እነርሱም ለኢያሱ
እንዲህ ብለው መለሱለት። ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ
እንሄዳለን። በሁሉም ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፤ ብቻ
አምላክህ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን። ኢያ.፩፡፲-፲፯
በዚህ በስድስተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦ ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ
ወሕግከኒ በማእከለ ከርስየ
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ
በአማርኛ፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ፤ መዝ. ፴፱፡፰
በዚህ በስድስተኛው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦
ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ
ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት
ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው
ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት
አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። ከብዙ
ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው። አምስት መክሊት
የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት
ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም።
መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ
ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥
ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ
እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ
ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው
መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥
መክሊትህ አለህ አለ። ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥
ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን
ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር
እወስደው ነበር። ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤
ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ
ማፋጨት ይሆናል። የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን
መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ ማቴ.፳፭፡፲፬-፴፩
ታማኝ ባሪያ ሆነን ለመንግስቱ እንድንበቃ አምላከ ቅዱሳን ያብቃን ።
አዘጋጅ ዲያቆን አብሊ ሮቤ
የድርሻችንን ሳንወጣ እምታችን ይጠብቀናል ማለት ወጋችንም አይደለም፡፡
እንኳን በሥጋ ከኮሮና ህመም ለመትረፍ በነፍስ ከዘላለም ቅጣት ለመትረፍ ራሱ ሰው የራሱ
ድርሻ አለው፡፡ የበዛውን የአምላክን ቸርነት ከምታንሰዋ የሰው ልጅ ተሳትፎ ጋር ስናስማማ
እንድናለን፡፡ ከአምላክ ቸርነት ጋር ሲነጻጸር የኛ ድርሻ በመዳናችን ውስጥ የቱን ያህል ትንሽ
ብትሆንም የግድ ግን አስፈላጊ ናት፡፡ በጸጋው ብቻ መዳን የለም፣ ይህም ማለት በአርባ ቀን
እድል( በእጣ ፈንታ) መዳን የለም፡፡ የሰው ነጻ ፈቃድና ኃላፊነት በሞቱም ሆነ በመዳኑ
ውስጥ የማይተካ አለው፡፡ ያ የበዛው የአምላክ ቸርነት አናሳውን የሰውን ድርሻ
አያጠፋውም፣ አይተካውም፡፡
ለክርስትና እምነት መሠረቱ የእግዚአብሔር ወልድ በሥጋ መገለጥ መሆኑ እሙን ነው፡፡
ይኸውም በተዋህዶ የከበረው፣ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ፣ ከሁለት አካል አንድ አካል
የሆነው ስግው ቃል ነው፡፡ በተዋህዶ ሁለቱ ቅድመ ተዋህዶ የነበሩ ፈቃዳት (ፈቃደ አምላክ
እና ፈቃደ ሰብእ) ለሰው ሰው ልጅ ድኅነት በተደረገው ተዋህዶ ውስጥ ሚና አላቸው፡፡
ለሰው ልጅ መዳን የቱን ያህል የአምላክ ምህረቱና ቸርነቱ ለንጽጽር የማይቀርብ ቦታ
ቢኖረውም፣ የሰውም ልጅ ፈቃድ ደግሞ አስፈላጊና አስፈላጊነቱ የግድ ነበር፡፡ በአምላክ
ሰው መሆን ውስጥ ሰው ልጅ ድርሻውን በድንግል ማርያም አንደበት “እንደ ቃልህ
ይደረግልኝ” በማለት ገለጸ፡፡ ይህም በመሆኑ ድኅነት በግድ የተጫነብን ሳይሆን በፈቃዳችን
የተቀበልነው ብሎም እኛ ራሳችን የተሳተፍንበት መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ እንኳንስ በግል
ድኅነታችን ውስጥ ይቅርና በአምላክ ሰው መሆን ውስጥ ራሱ ድርሻ አለው የሰው ልጅ፡፡
ምናልባት ምሳሌው እጅጉን የራቀና በአንድ ገጽ የማይጣጣም ሊመስል ይችላል፡፡ ሆኖም
ከዚህ ማንሳት የምፈልገው ቁምነገር ሰው ሁሌም የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለውና ያንን የቤት
ሥራውን መወጣት አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የአምላክን ድርሻ በፍጹም እምነት
መቀበል ደግሞ የላቀ ልዕልና የሚጠይቅ ጉዳይ ይሆናል፡፡
ለብዙ የኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ አለማድረግ እምታችን መከራከሪያ ስናደርግ እንሰማለን፡፡
ከምንም በፊት ይከላከልልናል ብለን በምንናገረለት እምነታችን ልክ ብንገኝ ኖሮ ምንኛ
በታደልን!! በእውነት ያለ ሐሰት እምነታችን ይታደገን ነበር፡፡ እውነቱን ስንናር ግን አሁን
ባለው ሁኔታ እምነታችንን የስንፍናችን መደበቂያ እያደረግን ነው፡፡ የገዛ ወንድሙን
ለመውደድ ያልበቃ እምነታችን እንዴት የዓለሙን ቁጣ ለመታደግ ይችላል ብለን
እንመጻደቃለን?! ለመሆኑ የሚያሰፍለገውን ነገር ማድረግ ከግል እምነታችንም ሆነ
ከሃይማታዊ አስተምህሮአችን ጋር እንደማይጣጣም በምን አስልተን ነው አስቀድመን
የስንፍና ሐሞታችንን የምንዘረግፈው?! እስቲ መጀመሪያ የድርሻችንን እናድርግና ከኛ አቅም
በላይ የሆነውን ለእግዚአብሔር እንስጥ፡፡ ግን የልብ ጠማማነታችንን፣ የበዛ ስንፍናችንንም
ጭምር እግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ነውር ነው፡፡
እጃችንን እንታጠብ
ተራርቀን እንገኝ
የተመከርነውን ሁሉ እናድርግ፡፡ እምነት በዚህ መንገድም ውስጥ እግዚአብሔር ቸርነቱን
ያደርግልናል ብሎ ማለትን ይጨምራል፡፡
"ነስሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት"
"መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንሰሃ ግብ"
ብልህ መንገደኛ ለመንገድ ስንቅ ይቋጥራል፡፡ የእኛ ስንቃችን ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡
ወንድሜ/እህቴ ፈጣሪን እንስማው ንሰሃም እንግባ እየራበን ለምን በረሃብ እንሙት ካህናት አሉልን የሚያጥብን ሥጋና ነፍሳችንን
ለምን እንርቃለን መቁረብ ሲሆን ተስፋችን ፡
ብልህ ችግሮችን ለመልካም ይጠቀመዋል እኛም ንሰሃ ብንገባ ብንቆርብ አሰባችሁት በመንግስቱ ቅድስት ሥላሴን፡ እመ አምላክ ድንግል ማርያምን ፡ ቅዱሳን መላዕክትን ፡ ቅዱሳን ነብያት ወሐዋርያትን ፡ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታትን ፡ ደናግላን መነካሳትን ፡ መናኝ ባህታዊያን ሁሉን ቅዱሳን እናያለን አብረን እኖራለን ከዚ የሚበልጥ ምን አለ እና ነው በፈጣሪ ያመፅን ሲዖልን የመረጥን፡፡
ዛሬ እንጸጸት ንሰሃ እንግበባ
ዛሬ እንወስን ሲዖል እንዳንገባ
ካህናት ይጠቡን በንሰሃ ሳሙና
የቆሸሽን እኛን ያፀዳናልና

መልካም ንሰሃ
የአባት ምክር
አየህ! አሉ ሲቃ በተሞላበት ድምፀት። የንግግራቸውን የአጀማመር ሁኔታ ስሰማ የተኛን አንበሳ የመቀስቀስ ያክል ቀይ መስመር እንዳለፍኩ ተሰማኝ። ቢሆንም ምርጫ አልነበረኝም ።
"ሰማህ!" አሉ:
"በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተውታላችሁ። ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፤ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፤ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፤ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፤ ምኞታችሁ ልክ የለውም፤ አምሮታችሁ ብዙ ነው። ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል። ተዉ የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፤ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፤ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ። ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተ መቅደሱን በመስታወት ሰርታችሁ መቅደስ ባትገቡ እንኳን ሁሉን ከውጭ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ። ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ፤ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም። ሁሉ አላችሁ፤ ግን ባዷችሁን ናችሁ። ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም!" ቀጠሉ አባ። ሰውነታቸው እንደ ቅኔ ዘራፊ በስሜት ይናጣል።
"መድኃኒት ነው ያልከው?! መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ትተኸኝ ትሄዳለህ። ጥበብን "ሀ ግእዝ" ብዬ ላስተምርህ ብሞክር፤ "ሆ ሳብዕ" ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ። የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተልከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል። ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፤ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ፤ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ፤ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከስር ትጀምራላችሁ። ትቀጥላላችሁ፤ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ። ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ። በጽኑ ታማችኋል"።
ከታሪክ ፍቅርን እና ልማትን ሳይሆን ጥላቻን እና ጥፋትን ትቆፍራላችሁ። ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፤ እናም ወደኋላ ስለታሪካችሁ እና ስለቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃት እና ሃፍረት ይሰማችኋል። ስለሆነም ከኋላ ታሪካችሁ እና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትን እና የተሸናፊነትን ትርጉም በአንድ ለይ የያዙ ሃውልቶችን ታቆማላችሁ። ለግልጽነት እና ለነጻነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ እርቃን ወደመሆን ወረዳችሁ።
ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ። በዚህ ዓለም ጥድፊያ ታማችኋል። ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፤ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፤ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ ሀገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ። በቁማችሁ የናቃችሁትን የሀገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ። ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ተሰብራላችሁ። ግብዝነታችሁ መጠን የለውም። ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፤ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቅያ ታስባላችሁ። ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖሩም። ዘመናችሁም በምልልስ እና በመዋተት ያልቃል። ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም!"
ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር) እመጓ 2008 ዓ.ም ከገፅ 161-163
እውነት ነው ዛሬ ሁላችን ታመናል ከዚህ አስከፊ ህመም ደግሞ መዳን እና ማገገም የምንችለው እግዚአብሔር ለኛ የሰጣቸውን አባቶቻችንን ስንሰማ እና የሚሉንን ስንተገብር ነው። እነርሱ ደግሞ በቃልም በፅሁፍም ይነግሩናል ይመክሩናል ለዚህ ነው 2ኛ ጢሞ 3፥16-17 "የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መፅሐፍ ሁሉ ለምክር እና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት ይሁንህ" የተባለው ስለሆነም የአባቶቻችንን ምክር እና ተግሳጽ አድምጠን ከዘመኑ የውስጥ ህመም እና በሽታ በንስሐና በእምነት በመመለስ ልንነፃ ይገባል። በብዙ ደግሞ አስተዋዮች ልንሆን ያስፈልጋል። የልቦናችን እግር መንገዱ ከዋዘኞች ጋር ሊተባበር አይገባም። "ልጄ ሆይ አስተውል" ይላልና ጠቢቡ ሰሎሞን።
የምህረት አምላክ እግዚአብሔር መካሪ አባት አያሳጣን። መፅሀፋን በሙሉ እንድታነቡት እንጋብዛችኋለን። ሀገራችንን እና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይጠብቅልን አሜን።
''ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥
ከመተቃቀፍም ለመራቅ
ጊዜ አለው፤''
(መጽሐፈ መክብብ 3፥5)እና
''እግርህን ወደ ባልንጀራህ ቤት አታዘውትር።''
(መጽሐፈ ምሳሌ 25፥17) ተብሎ ተፅፏል እና ፈጣሪን መፈታተን እዳይሆንብን ራሳችንን እንጠብቅ ።