St.Paul's Hospital Millennium Medical College
19K subscribers
2.08K photos
24 videos
12 files
469 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
Hungary pledges to boost Surgical Campaigns in St Paul's Hospital Millennium Medical College, AaBET hospital
A medical team named 'Hungary helps’ has provided St. Paul's Hospital Millennium Medical College and its affiliated hospital AaBET with medical support via Surgical Campaigns. The Surgical Campaign is highly presumed to be instrumental in addressing the surgical needs of some selected patients.
The campaign took place from May 27 until June 7, 2024. The surgical campaign in this round was focused in Neurosurgery and ENT specialties.
Two experienced male neurosurgeons and two female otolaryngologists with a member from anaesthesia were involved in the clinical service. There were also members involved in coordination and assessing the social impact.

There were 11 neurosurgical cases in skull base surgery operated within these periods. Surgery carries its own risk of complications and these cases of skull base neurosurgery were deemed as challenging cases with high risk of complications.
There were 53 cases operated by the ENT team in collaboration with the local ENT surgeons.Ensured quality education and promote lifelong learning opportunities for all is another mission to be hit. Surgical skills are better transferred in a hands-on approach. Such surgical campaigns offer great opportunities for training numerous professionals in different specialties. The knowledge and experience of these surgeons would be passed to local surgeons, nurses and residents. There is also the experience gained by the Hungarian surgeons in practice in Ethiopian setting, where resources are limited. This is a bilateral exchange of knowledge and expertise. Endoscopic ear surgery and Trans nasal orbital surgery were important lessons learnt.

The Hungary Ambassador to Ethiopia, his excellence Mr Attila Koppány, , does have a great role in initiating Hungary medical professionals and is highly attributable to the coming of Hungary physicians to Ethiopia thereby providing the people with voluntary service.

 
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ ኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እንኳን አደረሳችሁ!
የኮሌጁ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ሪፖርት ወይይት ተደረገ፡፡
በኮሌጁ ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች የቀረበው ይኸው የዘጠኝ ወር ሪፖርት የተቋሙን የስራ አፈጻጸም የተመለከተ ነው፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ አበይት የጤናው ዘርፍ የስራ ክንውንም ቀርቧል፡፡

በሪፖርቱ መሰረት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ስኬት የተመዘገበበት እንደሆነ ተገልጻል፡፡ ለአብነትም በሕክምና አገልግሎት ዘርፉ በዘጠኝ ወራት አራት መቶ ሀምሳ ሺህ ሕሙማን ተስተናግደዋል፡፡ በእናቶች ጤና አገልግሎት በየወሩ በአማካይ በቁጥር ለአንድ ሺህ እናቶች የወሊድ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይም 12 ሺህ ቀዶ ሕክምና ተሰርቷል፡፡ ይህም አፈጻፀሙ 85 በመቶ ለመድረስ ተችሏል፡፡ የኤሌክትሮኒክ ሜዲካል ሪኮርዲኒግ ሽፋኑ 95 በ በመቶ መድረሱም እንደ ስኬት ከተመዘገቡ ስራዎች መካከል ይገኝበታል፡፡ በሪፖርቱ የዓይን ሕክምና እና የተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ብዙ ሕሙማንን እንዳተስተናገዱ ተገልጻል፡፡ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያዊያን ሐኪሞች ሳይቆራረጥ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በተጨማሪም በሪፖርቱ እንደተገለፀው በሪፈር ተብለው ከሌሎች የጤና ተቋማት የሚመጡ ሕሙማን ምልልስ እንዲያጥር ተደርጓል፡፡ቀዶ ሕክምና የሚፈልጉ ሕሙማን በረጅም ቀጠሮ ማስተናገድ ቀርቷል፡፡ ሕሙማን በመጡበት ሰዓት በስፔሻሊስት ሐኪም ይታያሉ፡፡እነዚህን ሌሎች ጉዳዮች በሕክምና ክፍሉ ከታዩ ዋና ዋና ስኬቶች መካከል እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
በሕክምና አገልግሎቱ አሰጣጥ ላይም ዋና ተግዳሮት ተብለው ሁለት ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡ የጤና ኢንሹራንስ የሌላቸው እና ለሕክምና አገልግሎቱ ገንዘብ የመክፈል አቅም የሌላቸው ሕሙማን ቁጥር ጨምሯል፡፡ ይህም ተቋሙ የሚያገኘውን ገቢ አሳጥቶታታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቱን የሚሰጥበት ክፍል በቂ አለመሆን ተጠቅሰዋል፡፡
ኮሌጁ በስድስት የቅድመ ምረቃ የትምህርት ዘርፎች፡በ27 ሰብ ስፔሻሊቲ ሕክምና፣በ11 የማስተር እና የኤም. ፒ.ኤች እና 1 የፒ.ኤች .ዲ መርሀግብር በአጠቃላይ 2031 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ በዕለቱ ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡
የሕብረተሰብ ጤና ትምህርትቤት በመደበኛ መርሀግብሩ በሁለተኛ ዲግሪ በአምስት የትምህርት ዘርፎች በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡በዚህ ዓመት በጤና ተግባቦትና ፕሮሞሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡ ትምህርቱ ቤቱ በየዓመቱ ለሴቶች ብቻ በሚሰጠውʺFemale Scholarshipʺ ስምንት ሴቶች የነጻ ትምህርት ዕድል አግኝተዋል፡፡መምህራኑ በበጀት ዓመቱ በቁጥር 45 የሚደርሱ የምርምር ስራዎቻቸው በዐለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ታትመውላቸዋል፡፡
የነርሲንግ ትምህርት ቤት በበኩሉ በስድስት የሁለተኛ ዲግሪ መርሀግብር ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ ከትምህርት ፕሮግራማቸው መካከል ሶስቱ ሪዚደንሲ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በመጪው ዐመት ሁለት አዲስ የነርሲንግ ሪዝደንሲ መርሀግብር ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው፡፡ መምህራኑ በዚህ ዓመት በቁጥር 40 የሚደርሱ የጥናት ጽሁፋቸው በዐለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ታትመውላቸዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ በቅድመ ምረቃ በአምስት ፕሮግራሞችም በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
የሕክምና ትምህርት ቤቱ ሁለት አዳዲስ የስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች የከፈተ ሲሆን ተጨማሪ አንድ ፕራግራም በሚቀጥለው ዓመት ለማስጀመር ዝግጅቱን ጨርሷል፡፡
በአጠቃላይ በኮሌጁ የሰው ሐይል እጥረትና የመማሪያ ክፍሎች በበቂ ሁኔታ አለመገኘት ዋንኛ ችግር ነው ተብሏል፡፡
የኮሌጁን ምድረ ግቢ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እና ጽዱ ተቋም ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑ ይህ እንደስኬትተቆጥሯል፡፡በሌላ በኩል ኮሌጁ ነጸ ሕክምናን ሕብረተሰቡ በሚገኝበት አካባቢ በመሄድ ነጻ የጤና ምርመራ ሰጥቷል፡ የተጀመሩ የሕንጻ ግንባታዎች በተገቢው ጊዜ እንዲያልቁ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተብራርቷል፡፡
የኮሌጁከፍተኛ የስራ ሀለፊዎች ባቀረቡት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ ኃላፊዎቹ ለተገኙት ስኬቶች በሙሉ የመላው የኮሌጁ ማህበረሰብ ጥረት ነው ብለዋል፡፡ በሪፖርቱ የታዩ ችግሮችንም በቀጣይ ለመፍታት ጥረት ይደረጋልም ብለዋል፡፡
Exciting News!

We are thrilled to announce that the Center for Professional and Institutional Development (CPID) has been granted the annual model CPD award!
This outstanding achievement is a testament to the hard work, dedication, and collective efforts of the CPID team. We would like to extend our warmest congratulations to each and every individual who contributed to this success.
We are proud to share this achievement with the college community and celebrate the well-deserved recognition of our team's excellence!