የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የዲንኬ-ሣውላ-ሸፊቴ እና የቱርጋ-ያላ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ስራን የተረከበው ተቋራጭ በሙሉ አቅም ወደ ስራ እንዲገባ ጠየቁ
➖➖➖➖➖➖➖➖
ሣውላ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2016 ዓ.ም የዲንኬ-ሣውላ-ሸፊቴ እና የቱርጋ-ያላ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ በአድስ መልክ የቻይናው ዊይ ኮንትራክተር ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተረክቦ በከፊል ስራ የጀመረ ቢሆንም በሙሉ አቅም ወደ ተግባር ባለመግባቱ ከተቋራጩ እና አማካሪዎች ጋር የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ምክክር አካሂደዋል።
በመድረኩ የ china Wu Yi co ተቋራጭ የሳይት መሐንዲስ አስተባባሪዎችና ተወካዮች ፣ የማማከር ስራውን የሚያከናውነው የ K&j ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተወካዮች ፣ የጎፋ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጃኬተ ዛይሴ እና የሣውላ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ንጋቱ ተፈሪን ጨምሮ የገማች ኮሚቴ አባል ተገኝተዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በመድረኩ እንደገለጹት መንገዱ ለጎፋና አከባቢው ህዝብ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውና እንደ የአይኑ ብሌን የሚጠብቀው በመሆኑ በጥንቃቄ ሊመራ ይገባል ብለዋል።
አስተዳዳሪው መንገዱ በአድስ መልክ በጠንካራ ኮንትራክተር እና አማካሪ በከፊል ቢጀመርም ተቋራጩ በሙሉ የሰው ሃይል እንዲሁም የግንባታ ቁሳቁሶችና ተሽከርካሪዎች ስራውን እንዲያስጀምር ጠይቀዋል።
ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ
አማካሪው work schedule መነሻ በማድረግ በጥብቅ እንዲከታተሉ አስተዳዳሪው አሳስበዋል፡፡
ኢንጂነር ዳግማዊ አክለውም አንድ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ሲገባ ችግሮች እንደሚያጋጥሙ በመረዳት ችግሩን ፈትቶ ተግባርን ለማሳለጥ መስራት እንደሚገባው በማሳሰብ ህብረተሰቡ በመንገድ ሥራው ለአደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን በሚገባው ቋንቋ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት የመንገድ ደህንነት ስራዎች እንድሰሩ ጠይቀዋል።
የተቋራጩ የሳይት ማሃንድሶች እና የተቋራጩ ተወካዮች በበኩላቸው ለጅምር በ4 ዶዜር ፣ በ 4 ኤክስካቫተር ፣ በ 1 ሎደር እና በ 20 የጭነት መኪናዎች በከፊል ስራ መጀመሩን ገልጸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በመሉ አቅም ወደ ስራ ለመግባት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
አክለውም በአሁኑ ሰዓት የዋና እና መካከለኛ ካምፖችን በመገንባት ላይ እንደሚገኙ እና የማቴርያል ማምረቻ ስፍራዎችን የማዘጋጀት ስራዎች ላይ መሆናቸውን ተናግረው ስራውን በሙላት ለመጀመር በሣውላ ከተማ የካሳ እና ግመታ ስራዎች ሙሉ ለሙሉ ባለመጠናቀቃቸው እና የዝናብ ወቅት በመሆኑ መቸገራቸውን ገልጸዋል።
የሣውላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ተፈሪ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ከገማች ኮሚቴዎች ጋር በመነጋገር እና ህብረተሰቡን በማወያየት አብዛኛውን ስራ የጨረሰ መሆኑን በመግለፅ ቀሪ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በመድረኩ ጊዜያዊ የጥገና ስራ ከነገ ጀምሮ እንዲጀመር በመግባባት ተጠናቋል።

የጎፋ ዞን አመራሮች ወቅታዊ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ዙሪያ ዞናዊ የምክክር መድረክ በሣውላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሣውላ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2016 ዓ.ም የጎፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች '' ግጭትን ማስቀረት ብልፅግናን ማስቀጠል!! '' በሚል መሪ ቃል የፓርቲ እና የመንግሥት የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በሣውላ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
መድረኩን የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ፣ የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የከተማና መሠረተ-ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ወሰኔ እና የዞኑ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ እና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ በጋራ መርተውታል።
የጎፋ ዞን የመንግሥት ረዳት ተጠሪ እና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ በዞኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በፓርቲና በመንግሥት የተሠሩ ተግባራትን በጥንካሬ እና በጉድለት የሚያሳይ መነሻ ሰነድ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በመድረኩ እንደገለፁት ከሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ ድሎች እየተመዘገቡ ቢገኝም ለውጡን ከባህሪው ተረድቶ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
አክለውም ሁሉም አመራር በተሠማራበት ዘርፍ ከአሉባልታዎች ራሱን በማራቅ የህዝቡን አዳጊ ፍላጎት ለሟሟላት በሙሉ አቅሙ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።
በግብርና ፣ በገቢ ፣ በጤና ፣ በትምህርት እና በሌሎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።
በመድረኩ የዞን ማዕከል አመራሮች ፣ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር መዋቅር አስተባባሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
ስለ ተከታተላችሁን እናመሠግናለን !
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮች መረጃዎች እንዲደርሶት
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/gofazonecommunicationaffairs
በቴሌግራም :- https://tttttt.me/Gofazonecommunicationaffairs
በዩቲዩብ :- https://youtube.com/@goffazonecommunicationaffa5679
በቲክቶክ :- https://www.tiktok.com/@goffazonecommunic?_t=8dzED3aHE98&_r=1 ላይ ይከታተሉን!

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
በሀገራችን የተጀመረው የገዥ ትርክት ግንባታ ሂደት ውጤታማ እንዲሆን የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ የጎላ ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ
ሣውላ፣ ግንቦት 18/2016 ዓ.ም በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ አዘጋጅነት በዞኑ 39ሺህ የሚዲያ ተከታይ አባላትን የማፍራት ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ በሣውላ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ ሚዲያ አራተኛ መንግስት እንደመሆኑ በልዩ ትኩረት ሊመራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በሀገራችን የተጀመረው የገዥ ትርክት ግንባታ ሂደት ውጤታማ እንዲሆን የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ የጎላ ሚና እንደሚጫወት አቶ ጳውሎስ ተናግረዋል።
የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች በተግባር አጅበውና አሳልጦ ለመምራትና ጠንካራ ተግባቦት ለመፍጠር ትልቅ አቅም አለው ብለዋል።
ፓርቲው በርካታ ተግባራቶች እያከናወነ ያለ ቢሆንም የፖርቲም ሆነ የመንግስት ሚዲያዎች ከተቀባይነትና ሽፋን ከመስጠት አንጻር በዞን ደረጃ ጉድለቶች እንዳሉ ተለይተዋል ብለዋል ኃላፊው።
አክለውም በሀገራችን፣ በክልላችን ብሎም በዞናችን የሚሰሩ መልካም ሥራዎች በዓለምአቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ከማድረግ አኳያ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳሁን አባይነህ የመንግስት ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ተከታይ ማፍራት በሚቻልባቸው መንገዶችና አጠቃቀም ዙሪያ ለተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል።
አቶ ካሳሁን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ተቋማት ወቅታዊ፣ ታአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች በማሰራጨት በመንግስት እና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙት ዘርፍ ም/ ኃላፊ አቶ የትምጌታ ተስፋዬ "በዞኑ 39ሺህ በላይ ተከታይ በሚዲያ የማፍራት ንቅናቄ ገለጻ አድርገዋል።
ንቅናቄው አሁን ያለውን የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ለመሻገርና ጠንካራ አመራርና አባላት ለማፍራት የሚያግዝ መሆኑን አቶ የትምጌታ ገልጸዋል።
በዋናነት ፓርቲው አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ወደ ዳር ለማድረስ የዲጂታል ሚዲያ አዎንታዊ ሚናን አበርክቷል፣ ለዚህም መላው አመራርና አባል ለማሳተፍ በቀጣይ ቀሪ ቀናቶች ውስጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጸዋል።
ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር የፖርቲው አባላት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ትክክለኛ ማንኘት ያላቸውንና በኃላፊነት የሚሰሩትን የሚዲያ ተቋማትን መከተል እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በመድረኩ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ፣ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት፣ የወጣቶችና የሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል።

Forwarded from kassahun abayneh
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርባምንጭ ዲስትሪክት ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሣውላ ደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል ተመረቀ
ሣውላ፣ ግንቦት 24 ፣ 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርባምንጭ ዲስትሪክት በ6.3 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የሣውላ ደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል የጎፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣ የደቡብ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ አቶ ክንፈ ነጋሽ እና የአርባምንጭ ዲስትርክት ዳይሬክተር አቶ ገረመው ወንድምሁነኝ ሕንፃን መርቀው ከፍተዋል።
የደቡብ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ አቶ ክንፈ ነጋሽ በመርሃ-ግበሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ ኤሌክትሪክ በማዳረስ የሀጋራችንን ፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት መሸከም የሚችል ተቋም ለመሆን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት በአርባምንጭ ዲስትርክት 72 ኪ.ሜ የሚደርሱ የመስመር ማሻሻያ ፕሮጀክቶች በሪጅን ታቅደው እየተሰሩ መሆናቸውንና ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የሣውላ ከተማ እና የአርባምንጭ ከተማን ሙሉ ለሙሉ የማዘመን ስራ ለመስራት የጨራታ እና ሌሎች የዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
አቶ ክንፌ አክለውም ተቋሙ በዋናው ቢሮ እየተሰራ ያለውን ለሀገር ኩራት የሚሆን ኤክሰለንስ ሴንተርና የዋናው ቢሮ ህንጻ ግንባታ ጨምሮ ከ 64 በላይ ህንጻዎች እየገነባ ሲሆን ዛሬ የምንመርቀውን ጨምሮ በሪጅናችን 13 ሕንጻዎች እየተገነቡ በተለያየ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
የአርባምንጭ ዲስትርክት ዳይሬክተር አቶ ገረመው ወንድምሁነኝ በበኩላቸው የአርባ ምንጭ ዲስትሪክት ዘጠኝ ዞኖችንና ሶስት ከተማ አስተዳደሮችን በአስራ ስምንት አገልግሎት መስጫ ማዕከል አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፣ አንዱ ሣውላ ደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ በሣውላ ማዕከል ከተሰሩ ስራዎች ዋና ዋናዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው የከፍተኛና የዝቀተኛ መስመር ማስፋፊያዎችና የትራንስፎርመር ተከላ ስራዎች መከናወናቸውን አቶ ገረመው ገልጸዋል።
ከ14 በላይ በተለያዩ ምክንያቶች የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮችንም መቀየሩንና ከ1 ሺ 400 በላይ አዲስ ደንበኞችን የኃይል ተጠቃሚ መደረጉን የገለጹት አቶ ገረመው፣ በመሬት መንሸራትትና በአደገኛ አውሎ ነፋስ የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በፈጣን ርብርብ መልሶ ማገናኘት ተችሏል ብለዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ፥ ድስትሪክቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትንና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ ለማሳደግ የሚያከናውነው ተግባር ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
ዞኑ በሁሉም መስኮች እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ ያሉንን አቅሞችን ወደ ሀብትና ብልጽግና ለመቀየር የኃይል አቅርቦት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚይዝ ኢንጂነር ዳግማዊ ተናግረዋል።
ሣውላ ከተማ የአራት መዋቅሮች መቀመጫ እንደመሆኗ የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ ለማሳደግ የዞኑ መንግስት ከዲስትሪክቱ ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ዲስትሪክቱ በዞኑ የኃይል አቅርቦቱን በፍትሐዊ መንገድ ተደራሽ ለማድረግና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያከናወነ ስላለው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።
በመጨረሻም ሕንፃው በተያዘለት ጊዜና ጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለተዘጡ አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
በምረቃው ፕሮግራም ላይ የጎፋ ዞንና የሣውላ ከተማ አሰተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የደቡብ ሪጅን፣ የዲስትሪክቱ፣ የማዕከሉ ማኔጅመንትና ሰራተኞች ያህዌ ንሲ የሕንፃ ተቋራጭ ድርጅት አመራሮች ተገኝተዋል።