ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ዝምታዬ
#ሰይፈተማም Seife Temam
-------------
አፌ የተለጎመ
ዝም ሲል የኖረ
'ዝምታ ወርቅ ነው'
ብዬስ አልነበረ
ወርቅ ያብለጨልጫል
ይጣራል ከሩቁ
የጎንም ይሸሻል
ዝምን ግን ሲያጠልቁ

በእጄ ብትሆን ፀሀይ
ላይተን አላበራም ከውቅያኖሱ ላይ
ቢታዘዘኝ ዝናብ ቢሰማኝ ደመና
ምድር አልከውም ካልሰፈረ መና
የብቻዬም ቢሆን አየሩ ንፋሱ
አላስጠጋችውም ከሰውም አይደርሱ
… … … ... ... ነፍስ እስካላደሱ
ኑር
#ግጥምሲጥም #ሰይፈተማም
ጽደቅ እንደ ችግኝ አፍላ እንደ ሾላ
ከአለም ደጉን ወስደህ መልካም ፍሬ ዝራ
ዘላለም ለመኖር 'አሁን'ን አትፍራ
አትቅጠፍ
ቅርንጫፍ
ካላፈራ ኋላ

2012