#gitemsitem #poetic_saturdays #ግጥም_ሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #seifetemam
ህመሜን ላጣጥም
-----------------------
እስቲ ልንቆራጠጥ ተዉኝ ላቃስትበት
ህመሜን ላጣጥም እስክፈወስበት
እንዳትወጉኝ ማደንዘዣ
እንዳትሰጡኝ ማስታገሻ
በሰፊ አውታር መገናኛ
በብልጭልጭ መሸፈኛ
የዘመን ጎርፍ አግበስብሶ
በከሰተው መከወኛ
ከኔ በላይ ላያማችሁ
ከህመሜ ላይ ሰራርቃችሁ
በሽተኛ ስንኩል ሳለሁ
አታፍጥኑት ሞቴን ካለው
እያላችሁ ጤነኛ ሰው
ልዳን እንጂ አታስታግሱኝ
ተዉኝ ተዉኝ ልንቆራጠጥ
ላተኩሰው ሆዴ ይቁረጥ
እራሴ ይምታ አይኔ ይበጥ
ሰው አድርጉኝ የሚሰማው
ከራሱ ጋር የሚታደም
በሽታዬን ካልተቀማሁ
በህመሜ ነው የምታከም
ሰይፈ ተማም 2009
ህመሜን ላጣጥም
-----------------------
እስቲ ልንቆራጠጥ ተዉኝ ላቃስትበት
ህመሜን ላጣጥም እስክፈወስበት
እንዳትወጉኝ ማደንዘዣ
እንዳትሰጡኝ ማስታገሻ
በሰፊ አውታር መገናኛ
በብልጭልጭ መሸፈኛ
የዘመን ጎርፍ አግበስብሶ
በከሰተው መከወኛ
ከኔ በላይ ላያማችሁ
ከህመሜ ላይ ሰራርቃችሁ
በሽተኛ ስንኩል ሳለሁ
አታፍጥኑት ሞቴን ካለው
እያላችሁ ጤነኛ ሰው
ልዳን እንጂ አታስታግሱኝ
ተዉኝ ተዉኝ ልንቆራጠጥ
ላተኩሰው ሆዴ ይቁረጥ
እራሴ ይምታ አይኔ ይበጥ
ሰው አድርጉኝ የሚሰማው
ከራሱ ጋር የሚታደም
በሽታዬን ካልተቀማሁ
በህመሜ ነው የምታከም
ሰይፈ ተማም 2009