ተመራቂ መኮንኖች ማንኛውንም ተልዕኮ ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸው ተረጋግጧል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ዘርፍ ራሷን ለመቻል እያደረገች ያለችውን ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች እኛ የሰራዊት አባላትና አመራሮች በእጅጉ የምንኮራባቸው ናቸው ሲሉ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን ተናግረዋል።
የማይታሰበውን የአባይ ግድብ ገድቦና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ገንብቶ ማጠናቀቅ ለሀገራችን ትልቅ የድል ብስራት ነው ያሉት ጄኔራል ይመር መኮነን ሠራዊታችን ይህን የብሔራዊ ጥቅማችን ማረጋገጫ የሆነውን ግድብ ያለማቋረጥ ከወር ደመወዙ እየቆረጠ የገነባው በመሆኑ የመጠናቀቁ ዜና እጅግ አስደስቶታል ብለዋል።
ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሠልጠን፣መደራጀትና መታጠቅ እንዳለብን እናምናለን ያሉት ጀኔራል ይመር ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ተመራቂዎች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
እንደ ስልጠና ዋና መምሪያ በተቋሙ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ዘብ የሚቆሙ ፕሮፌሽናል አመራሮችን፣ልዩ ልዩ ሙያተኞችን እና ተዋጊዎችን ያለ ማቋረጥ በተለያዩ ማሰልጠኛዎች በማሰልጠን ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁ የንስር ኮርስ እጩ መኮንኖች ለተከታታይ ወራቶች ሰልጥነው የመመረቂያ መስፈርቱን በወታደራዊ ስልጠናዎችና በልዩ ልዩ የግንባታ ትምህርቶች የወሰዱ በቀጣይ በመቶ አዛዥነትና በተመጣጣኝ የሀላፊነት ደረጃ ተመድበው የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ የታመነባቸው ናቸው ብለዋል።
ዘጋቢ ልደት አስረስ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

👍29❤23🔥2
የብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ፣ ባደረባቸው የልብ ህመም ምክንያት በአሜሪካን አገር ሲታከሙ ቆይተው፣ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ስርዓተ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት በመንበረ ፅባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ጦርን በመምራት፣ ወታደራዊ የአውደ ውጊያ ግዳጆችን በብቃት እና በጀግንነት በመወጣት፣ ለእናት ሀገራቸው ከፍተኛ ውለታን ሰርተው አልፈዋል።
በተሰለፉባቸው አውደ ግምባሮች ሁሉ፣ የጦር አውደ ውጊያን በመምራት፣ ለእናት ሃገራቸው ክብርና አይደፈሬነት፣ በከፍተኛ ጀግንነት ወታደራዊ ግዳጃቸውን የተወጡ መሪ ናቸው።
ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ፣ በ32 ዓመት የአገልግሎታቸው ዘመን ወቅት የበርካታ ሚዳሊያዎች ተሸላሚም ነበሩ።
ከእነዚህም መካከል፣ የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ፣ የፈረሰኛ ደረጃ፣ የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የመኮንን ደረጃ፣ የተባበሩት መንግስታት ሜዳይ በኮንጎ ዛየር ሪፐብሊክ፣ የካቲት 66 ሜዳይ 1ኛ ደረጃ ሜዳይ፣ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ የጦር ባለዘንባባ ሜዳይ፣ ከፍተኛ የአመራር ሊደርሽፕ ሜዳይ፣ ፣የየመን ዲሞክራቲክ መንግስት የመታሰቢያ ሜዳይ ይጠቀሳሉ።
ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመታሰቢያነታቸው በመንበረ ፅባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ፣ ከባለቤታቸው ከወይዘሮ ምንትዋብ ሰይፉ ጋር ሁለት ሴት እና አንድ ወንድ በድምሩ 3 ልጆችን አፍርተዋል።
ዘጋቢ ቢያድግልኝ መሪ
ፎቶ ግራፍ ፉራ አብደላ

❤31🔥4👏4👍2👎1
ተመራቂ መኮንኖች የሚጠበቅባቸውን ሥልጠና በአግባቡ መውሰዳቸው ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም
የሀገራችንን ሰላምና ጥቅም ለማስጠበቅ የሰለጠነ እና ዘመኑን የሚመጥን ፕሮፌሽናል መኮንን እየገነባን እንገኛለን ሲሉ የሁርሶ አጭር ኮርስ እጩ መኮንን ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ገልፀዋል።
ተመራቂ መኮንኖቹ በቴክኒክ ትምህርት፣በውጊያ አካል ብቃት፣በወታደራዊ ሰልፍ፣በነፍስ ወከፍና በቀላል መሣሪያዎች ትምህርት መሸፈን የሚገባቸውን የስልጠና ጊዜ የሸፈኑ መሆናቸውንም አዛዡ ተናግረዋል።
የሀገራችን ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት መብት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተገነዘብንበት እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ በተመረቀበት ማግስት መኮንኖቹ መመረቃቸው ልዩ ያደርጋቸዋል ብለዋል።
የትምህርትና የስልጠና አሰጣጥ ሂደቱ የወቅቱን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መደበኛና ኢ-መደበኛ የውጊያ ስልቶች ላይ ትኩረት በመስጠት በማንኛውም ሁኔታ፣ ጊዜና ወቅት ጠላትን ድል ማድረግ የሚያስችል አቅም እንዲኖራቸው መደረጉን ኮሎኔል ከድር ጫጮ ተናግረዋል።
ሰልጣኞች በቆይታቸው 15 ሚሊዮን ብር የሚገመት መሠረተ ልማቶችና የፈጠራ ውጤቶችን ለትምህርት ቤቱ በመስራት ተቋሙንም ማሰልጠኛውንም ከወጪ መታደግ መቻላቸውን የገለፁት ኮሎኔል ከድር ለአካባቢው ማህበረሰብም የተለያዩ የድጋፍ ስራዎች መስራታቸውንም ጠቁመዋል።
ተመራቂ መኮንኖቹ የመመረቂያ መሥፈርቱን አሟልተው መመረቃቸውን የገለፁት ኮሎኔል ከድር ጫጮ ለስልጠናው መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

❤44🔥7👍5🥰2
ዓላማችን የዘመኑ አርበኛ ሆነን እዚህ የደረሰችውን ኢትዮጵያን ማስቀጠል ነው።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም
ዓላማችን የዘመኑ አርበኛ ሆነን እዚህ የደረሰችውን ኢትዮጵያን ማስቀጠል ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሰሜን ምዕራብ ዕዝ አመራሮች ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ በሰጡት የስራ መመሪያ አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ በክብር ያቆዩ አርበኞች ናቸው፤ ሠራዊታችን ደግሞ የዚህ ዘመንና ትውልድ አርበኛ ነው ብለዋል።
ሰሜን ምዕራብ ዕዝ በአገራዊ ለውጡ ማግስት የተመሰረተ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ራሱን እያደራጀና እያጠናከረ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት እየፈፀመ የመጣ ዕዝ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አገር ለማሻገር ከባንዳ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ የጀግንነት ታሪኩን በደማቁ የፃፈ ዕዝ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰሜን ምዕራብ ዕዝ በጎንደር ፤በወልቃይት ጠገዴ፤ በኤርትራና ሱዳን ደንበር አካባቢ ያለውን ወስብስብ ግዳጅ ለምንም ነገር ሳይበገር ተልዕኮውን በፅናት የተወጣ ዕዝ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
እንደ ሃገር የተጀመሩ የልማት ዕቅዶችን ለማሳካት ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ ይጠበቅባችኋል ያሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ክፍተቶቻችሁን በመሙላት ለቀጣይ ግዳጅና ተልዕኮ የበለጠ መዘጋጀት ይጠበቅባችኋል ሲሉም አሳስበዋል።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

❤42👍12🔥5