FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34.2K photos
39 videos
9 files
9.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከፀጥታ አካላት ጋር ሊሰራ እንደሚባ ተገለፀ።

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

‎ከዞን ከወረዳ እና ከሠራዊቱ የተውጣጡ የፀጥታ ሃይል አመራሮች በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳበርጋና ሜታ ውልቂጤ ወረዳ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

‎በውይይቱ ላይ የምዕራብ ሸዋ ዞን የአካባቢና ተፈጥሮ ሀብት ሃላፊ ፣የአዳበርጋና የሜታ ውልቂጤ ወረዳ አስተዳደሮች ፣የሃገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ሀደስንቄዎች፣የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ የፀጥታ ኃይሎች እና የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

‎በዉይይት ላይ የተመሰረተ አማራጭን መከተል እንደሚገባና ህዝቡ የራሱን ሚና መለየትና መወጣት እንዳለበት የገለጹት የ6ኛ ዕዝ የኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ጌትየ ዘውዱ በዞኑ የሸኔ አባላት እጅ እንዲሰጡ እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።

‎ኮሎኔል ጌትየ ዘውዱ የሰላም ግንባታ ሂደት በአፈሙዝ ብቻ የሚረጋገጥ ባለመሆኑ መላው ህዝቡ ተደብቀው ያሉ የሸኔን አባላትና መረጃ አቀባዮችን በመለየት፣ ለህግ በማቅረብ ለሰላም የሚበጁ ተግባራትን በመፈፀም የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ማሥቀጠል ይገባል ብለዋል።

‎የምዕራብ ሸዋ ዞን የአካባቢና ተፈጥሮ ሀብት ሃላፊ አቶ አዳሙ ዲንቂሲሳ የዞንና የወረዳ አመራሮች በቅንጅት በመስራት ይህንኑ ፀረ ሰላም ሀይል አምርሮ በመጥላት እንዲሁም በሀቀኝነትና በታማኝነት ለህዝብ በማገልገል የሚጠበቅብንን ሀላፊነት በመወጣት የህዝብን አደረጃጀት በማስተካከልና የነቃ ህዝባዊ ተሳትፎ በማድረግ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን መቆም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ዘገባው የኮሩ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27👍12🔥1👏1
ሠራዊታችን የጠላቶቻችን ህልም ከንቱ ቅዠት ሆኖ እንዲቀር አድርጓል፦
      ጀኔራል ይመር መኮነን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

በሰሜን ምስራቅ እዝ የቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ወስደው ወደ ዕዙ የተመደቡ መሰረታዊ ወታደሮችን ለወራት ተጨማሪ ሰልጠና በመስጠት አስመርቋል።

በዚሁ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ይመር መኮነን ኢትዮጵያ በእድገት ጎዳና እየገሰገሰች ፈተናዎችንና ተግዳሮቶችን በፅናት እያለፈች እንደምትገኝ ገልፀው ይህ የሀገራችን የእድገትና የልማት ግስጋሴ ያልተመቻቸው የውስጥና የውጭ ጠላቶች እድገቷን ለማሰናከል ያለዕረፍት እየሰሩ መገኘታቸውን ገልፀዋል።

ሠራዊታችን የሚቃጡ ትንኮሳዎችን በብቃት በመመከት አኩሪ ድል እያስመዘገበ መገኘቱን የተናገሩት ኃላፊው የሠራዊቱን የዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ ሂደት የሚያሳልጡ ተግባራትና የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑንም ተናግረዋል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ አኩሪ ድሎችን የፈፀመ ጀግና ዕዝ መሆኑን የገለፁት ጄኔራል ይመር መኮነን የእለቱ ተመራቂዎች የሰራዊታችንን ድል አስጠብቀው መቀጠልና ማንኛውንም ግዳጅ በፅናት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችና ስቪል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል። ዘገባው የንጉሴ ውብሊቀር ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2116🔥2👏1
ዕዙ የሀገርን ህልውና ለመፈታተን በሚሞክሩ የጥፋት ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል
   ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ እዝ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመጠበቅና ሰላምን ለማስከበር የሚደረገውን ሀገራዊ ተልዕኮ የሚያጠናክሩ፣ ለማንኛውም ግዳጅ ብቁና ዝግጁ የሆኑ መሠረታዊ ወታደሮችን የማጠናከሪያ ሥልጠና በመሥጠት በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው የክልል የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ፣ ሰራዊቱ በቴክኖሎጂና በክህሎት የታገዘ ዘመናዊ የውጊያ ዝግጁነቱን ያሳየባቸው ወታደራዊ ትርኢቶችም ቀርበዋል።

በእለቱ የሰሜን ምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል ህዝብና መንግስት የሀገሪቱን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል። የሰላም አማራጭን ወደጎን በመተው የጥፋት መንገድን የመረጡ ኃይሎች ላይ የዕዙ ሰራዊቱ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል ኃላፊ ኮሎኔል ግርማ ስዩም በበኩላቸው፤ ሰልጣኞች በማንኛውም አስቸጋሪ የአየር ንብረትና ፈታኝ መልክዓ-ምድር ላይ ተሰማርተው የጠላትን እንቅስቃሴ መቆጣጠርና ማምከን የሚያስችል አቅም እንዲጨብጡ መደረጉን ገልፀዋል።

ከቴክኒካዊ እና ወታደራዊ ሳይንስ በተጨማሪ፣ ሰራዊቱ የታጠቀውን ዘመናዊ የግልና የቡድን መሳሪያ በአግባቡና በብቃት ስራ ላይ ማዋል እንዲችል ቀንና ሌሊትን ያካተተ ሰፊ ስልጠና መውሰዳቸውንም ተናግረዋል።

በስልጠና ቆይታቸው በዲሲፕሊን እና የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ሰልጣኞች በከፍተኛ አመራሮቹ እጅ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የዘገበው አደም አሊ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍6🔥6
ዩኒቨርሲቲው ወቅታዊ የመከላከያን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ እያካሄደ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን ዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ እዉቅና  ለመጠየቅ ብሎም ወቅታዊ የመከላከያን ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዉጤት ተኮር ስርዓተ ትምህርት መሰረት እየተከለሱ ያሉ የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ፣ የጤና ሳይንስ እንዲሁም የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጆች ፕሮግራሞችን ለማጠናከር በውጤት ላይ የተመሰረተ የትምህርት ስርዓት በሚል ርዕስ አውደ ጥናት አካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ኘሬዝዳንት ዶክተር ተስፋዬ ቶሉ በአውደ ጥናቱ መክፈቻ
የአካዳሚክ ምክትል ኘሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የአካዳሚክ ኘሮግራም ዳይሬክቶሬት በሁሉም ኮሌጆች ፕሮግራሞችን ለእዉቅና ጥያቄ  ለማዘጋጀት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ማከናወኑን አስታውሰዋል።

ምክትል ኘሬዝዳንቱ ዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ እዉቅና ለመጠየቅ በዉጤት ተኮር ስርዓተ ትምህርት መሰረት ፤ ከመከላከያ ወቅታዊ ፍላጎት አንፃር የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ይህን ስራ ሲያከናውን መቆየቱንም ጠቁመዋል። 

የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣  መምህራን ብሎም የዘርፉ አካላት ይበልጥ የተሻለ ግንዛቤን እና ክህሎትን እንዲጨብጡ ለማስቻል በውጤት ላይ የተመሰረተ የትምህርት ስርዓት በሚል ርዕስ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከተጋበዙ ሙሁራን ጋር ውይይት ማካሄድ ማስፈለጉንም ዶክተር ተስፋዬ ገልፀዋል።

በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ኘሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሻለቃ ዶክተር መዝገቡ በላይው በአደጥናቱ የተለያዩ ኘሮግራሞቹን በዓለም አቀፍ እንዲሁም አገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ካገኘው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር የተደረገው ውይይት ትልቅ ግንዛቤን በአካዳሚው ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለድርሻዎች የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ድንቁ ስዩም ዩኒቨርሲቲው በዓለም አቀፍ እንዲሁም አገር አቀፍ ደረጃ ኘሮግራሞቹ እውቅና እንዲያገኙ የሄደባቸውን የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ሳይንሳዊ ደረጃዎችን ለአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል።

ወቅታዊ የመከላከያን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ በማድረግ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዕውቅና ለማግኘት ሊሰሩ የሚገባቸውን ስራዎችንም ዶክተር ድንቁ ገልፀዋል። ዘገባው የዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
12👍11