FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34.2K photos
39 videos
9 files
9.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሁርሶ አጭር ኮርስ እጩ መኮንን ትምህርት ቤት የ26ኛ ንስር ኮርስ ሰልጣኞችን አሥመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም

በዚሁ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ቀደምት አርበኞች  ያለጫማ፣ ባልሰለጠነ የሰው ሀይል እና ባልሰለጠነ መሣሪያ የሀገር ውስጥና የውጭ ጠላትን መክተው ሀገር በደማቸውና በአጥንታቸው ማግረው አስረክበውናል፤ እናንተም የእለቱ ተመራቂዎች የቀደምት አርበኞች ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን ሀገርን ጠብቃችሁ ለትውልድ ማስረከብ ይኖርባችኋል ብለዋል።

የኮርሱ ስያሜ ንስር እንደመሆኑ የበራሪዋን የንስርን ጠላትን ከሩቅ የመመልከት፣ ከፍ ብሎ የመብረርን እና ከሀይል በላይ የሆነ ጠላት ሲገጥም ከሩቅ ተመልክቶ የመደምሰስን እንዲሁም ራስን በስልጠና በየጊዜው መለወጥን እንደንስሯ በራሪ አህዋፍ ባህሪ ልትላበሱ ይገባል ሲሉ አሥገንዝበዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ሀገራችን ከጥንትም ጀምሮ ከውስጥም ይሁን ከውጭ ጠላት የማታጣ በመሆኗ አሁንም ሀገርን ለማዳከም የውጭ አጀንዳ ተቀብለው የሚገኙ ፀረ ሰላም ሀይሎች ለማተራመስ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ቢሆንም ኢትዮጵያ ሰላሟ የተረጋገጠ ያደገችና የበለፀገች ሆና ልጆቿን ማኖር እንድትችል በስልጠና ያገኛችሁትን አቅም መጠቀም ይኖርባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

በእለቱ በስልጠናው ብልጫ ላመጡ ተመራቂዎችና ለስልጠናው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዚሁ የዕጩ መኮንኖች የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና፣ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ይመር መኮንን፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ጀነራል መኮንኖች፣ የሠራዊት አባላት፣ አባ ገዳዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ልደት አስረስ
ፎቶ ግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
42👍18🔥4🏆1
ተመራቂ መኮንኖች ማንኛውንም ተልዕኮ ለመፈፀም  ዝግጁ መሆናቸው ተረጋግጧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ዘርፍ ራሷን ለመቻል እያደረገች ያለችውን ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች እኛ የሰራዊት አባላትና አመራሮች በእጅጉ የምንኮራባቸው ናቸው ሲሉ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን ተናግረዋል።

የማይታሰበውን የአባይ ግድብ ገድቦና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ገንብቶ ማጠናቀቅ ለሀገራችን ትልቅ የድል ብስራት ነው ያሉት ጄኔራል ይመር መኮነን ሠራዊታችን ይህን የብሔራዊ ጥቅማችን ማረጋገጫ የሆነውን ግድብ ያለማቋረጥ ከወር ደመወዙ እየቆረጠ የገነባው በመሆኑ የመጠናቀቁ ዜና እጅግ አስደስቶታል ብለዋል።

ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሠልጠን፣መደራጀትና መታጠቅ እንዳለብን እናምናለን ያሉት ጀኔራል ይመር ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ተመራቂዎች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

እንደ ስልጠና ዋና መምሪያ በተቋሙ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ዘብ የሚቆሙ ፕሮፌሽናል አመራሮችን፣ልዩ ልዩ ሙያተኞችን እና ተዋጊዎችን ያለ ማቋረጥ በተለያዩ ማሰልጠኛዎች በማሰልጠን ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁ የንስር ኮርስ እጩ መኮንኖች ለተከታታይ ወራቶች ሰልጥነው የመመረቂያ መስፈርቱን በወታደራዊ ስልጠናዎችና በልዩ ልዩ የግንባታ ትምህርቶች የወሰዱ በቀጣይ በመቶ አዛዥነትና በተመጣጣኝ የሀላፊነት ደረጃ ተመድበው የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ የታመነባቸው ናቸው ብለዋል።

ዘጋቢ ልደት አስረስ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2923🔥2
የብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ፣ ባደረባቸው የልብ ህመም ምክንያት በአሜሪካን አገር ሲታከሙ ቆይተው፣ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ስርዓተ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት በመንበረ ፅባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ጦርን በመምራት፣  ወታደራዊ የአውደ ውጊያ ግዳጆችን በብቃት እና በጀግንነት በመወጣት፣ ለእናት ሀገራቸው ከፍተኛ ውለታን ሰርተው አልፈዋል።

በተሰለፉባቸው አውደ ግምባሮች ሁሉ፣ የጦር አውደ ውጊያን በመምራት፣ ለእናት ሃገራቸው ክብርና አይደፈሬነት፣ በከፍተኛ ጀግንነት ወታደራዊ ግዳጃቸውን የተወጡ መሪ ናቸው።

ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ፣ በ32 ዓመት የአገልግሎታቸው ዘመን ወቅት የበርካታ ሚዳሊያዎች ተሸላሚም ነበሩ።

ከእነዚህም መካከል፣ የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ፣ የፈረሰኛ ደረጃ፣ የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የመኮንን ደረጃ፣ የተባበሩት መንግስታት ሜዳይ በኮንጎ ዛየር ሪፐብሊክ፣ የካቲት 66 ሜዳይ 1ኛ ደረጃ ሜዳይ፣ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ የጦር ባለዘንባባ ሜዳይ፣ ከፍተኛ የአመራር  ሊደርሽፕ ሜዳይ፣ ፣የየመን ዲሞክራቲክ መንግስት የመታሰቢያ ሜዳይ ይጠቀሳሉ።

ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመታሰቢያነታቸው በመንበረ ፅባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ፣ ከባለቤታቸው ከወይዘሮ ምንትዋብ ሰይፉ ጋር ሁለት ሴት እና አንድ ወንድ በድምሩ 3 ልጆችን አፍርተዋል።

ዘጋቢ ቢያድግልኝ መሪ
ፎቶ ግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31🔥4👏4👍2👎1