የተሰጣቸው የማዕረግ ሹመት ለበለጠ ስራ እና ሃላፊነት እንደሚያነሳሳቸው ተሿሚዎች ገለጹ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም
የተሰጣቸው የማዕረግ ሹመት ለበለጠ ስራ እና ሃላፊነት እንደሚያነሳሳቸው ተሿሚ የሠራዊት አመራሮች ገለጹ።
በጠቅላይ ሚኒስትር እና በጦርሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) አቅራቢነት በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም ወታደራዊ የማዕረግ ሹመት ከተሰጣቸው አመራሮች መካከል የሠሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ ሹመቱ ለበለጠ ስራ እና ሃላፊነት እንደሚያነሳሳቸው ገልጸው እንደተቋም ለዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ዕዝ አንድ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ግርማ አየለ በበኩላቸው የማዕረግ ሹመት ቀደም ብሎ በነበረህ ሃላፊነት ለሰራኸው ስራ የሚሰጥ ዕውቅና እና በቀጣይም ለሚጠብቅህ ከፍተኛ የስራ ሃላፊነት የምትዘጋጅበት ምዕራፍ ነው ካሉ በኋላ ወደ ፊትም ከሚመሩት ሠራዊት ጋር በመሆን ህዝብ እና መንግስት የሰጧቸውን ተልዕኮ በላቀ ብቃት ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ብርጋዲየር ጄኔራል ቾምቤ ወርቁ በበኩላቸው ያገኘነው የማዕረግ ሹመት የሰራዊታችንን ተልዕኮ የመወጣት አቅም ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ እያከናወን ላለው ሁለንተናዊ የዝግጁነት ስራ ጥሩ ሞራል እና መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ብለዋል
ዘጋቢ ወንድማገኝ ታደሠ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://xn--r1a.website/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

❤53🔥4👏2👍1🥰1
የሁርሶ አጭር ኮርስ እጩ መኮንን ትምህርት ቤት የ26ኛ ንስር ኮርስ ሰልጣኞችን አሥመረቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም
በዚሁ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ቀደምት አርበኞች ያለጫማ፣ ባልሰለጠነ የሰው ሀይል እና ባልሰለጠነ መሣሪያ የሀገር ውስጥና የውጭ ጠላትን መክተው ሀገር በደማቸውና በአጥንታቸው ማግረው አስረክበውናል፤ እናንተም የእለቱ ተመራቂዎች የቀደምት አርበኞች ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን ሀገርን ጠብቃችሁ ለትውልድ ማስረከብ ይኖርባችኋል ብለዋል።
የኮርሱ ስያሜ ንስር እንደመሆኑ የበራሪዋን የንስርን ጠላትን ከሩቅ የመመልከት፣ ከፍ ብሎ የመብረርን እና ከሀይል በላይ የሆነ ጠላት ሲገጥም ከሩቅ ተመልክቶ የመደምሰስን እንዲሁም ራስን በስልጠና በየጊዜው መለወጥን እንደንስሯ በራሪ አህዋፍ ባህሪ ልትላበሱ ይገባል ሲሉ አሥገንዝበዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ሀገራችን ከጥንትም ጀምሮ ከውስጥም ይሁን ከውጭ ጠላት የማታጣ በመሆኗ አሁንም ሀገርን ለማዳከም የውጭ አጀንዳ ተቀብለው የሚገኙ ፀረ ሰላም ሀይሎች ለማተራመስ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ቢሆንም ኢትዮጵያ ሰላሟ የተረጋገጠ ያደገችና የበለፀገች ሆና ልጆቿን ማኖር እንድትችል በስልጠና ያገኛችሁትን አቅም መጠቀም ይኖርባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።
በእለቱ በስልጠናው ብልጫ ላመጡ ተመራቂዎችና ለስልጠናው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚሁ የዕጩ መኮንኖች የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና፣ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ይመር መኮንን፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ጀነራል መኮንኖች፣ የሠራዊት አባላት፣ አባ ገዳዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ ልደት አስረስ
ፎቶ ግራፍ አበረ አየነው

❤42👍18🔥4🏆1
ተመራቂ መኮንኖች ማንኛውንም ተልዕኮ ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸው ተረጋግጧል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም ዘርፍ ራሷን ለመቻል እያደረገች ያለችውን ተስፋ ሰጪ የልማት እንቅስቃሴዎች እኛ የሰራዊት አባላትና አመራሮች በእጅጉ የምንኮራባቸው ናቸው ሲሉ የመከላከያ ትምህርት እና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን ተናግረዋል።
የማይታሰበውን የአባይ ግድብ ገድቦና ታላቁን የህዳሴ ግድብ ገንብቶ ማጠናቀቅ ለሀገራችን ትልቅ የድል ብስራት ነው ያሉት ጄኔራል ይመር መኮነን ሠራዊታችን ይህን የብሔራዊ ጥቅማችን ማረጋገጫ የሆነውን ግድብ ያለማቋረጥ ከወር ደመወዙ እየቆረጠ የገነባው በመሆኑ የመጠናቀቁ ዜና እጅግ አስደስቶታል ብለዋል።
ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሠልጠን፣መደራጀትና መታጠቅ እንዳለብን እናምናለን ያሉት ጀኔራል ይመር ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ተመራቂዎች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
እንደ ስልጠና ዋና መምሪያ በተቋሙ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ዘብ የሚቆሙ ፕሮፌሽናል አመራሮችን፣ልዩ ልዩ ሙያተኞችን እና ተዋጊዎችን ያለ ማቋረጥ በተለያዩ ማሰልጠኛዎች በማሰልጠን ላይ እንደሚገኙም ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁ የንስር ኮርስ እጩ መኮንኖች ለተከታታይ ወራቶች ሰልጥነው የመመረቂያ መስፈርቱን በወታደራዊ ስልጠናዎችና በልዩ ልዩ የግንባታ ትምህርቶች የወሰዱ በቀጣይ በመቶ አዛዥነትና በተመጣጣኝ የሀላፊነት ደረጃ ተመድበው የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ የታመነባቸው ናቸው ብለዋል።
ዘጋቢ ልደት አስረስ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

👍29❤23🔥2