የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
30.4K subscribers
1.66K photos
102 videos
41 files
318 links
በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡

ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot

Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
Download Telegram
ጥር ፲፩
ጥምቀተ ኢየሱስ


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሳ ዓመት ሲመላው ዮሐንስ ሰላሳ ዓመት ከስድስት ወር ሲሆነው በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ሄደ፤
🌿 ለምን ወደዮሐንስ ሄደ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ለምን አልመጣም ቢሉ ባሪያ በጌታው እጅ ይጠመቃል እንጂ ጌታ በባሪያው እጅ ይጠመቃልን ቢሉ ?

1. ለትህትና

ጌታችን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሰው የሆነው ለትህትና ነው እንጂ ለልእልና አይደለምና

2. አብነት ለመሆን

ጌታችን ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ቢለው ዛሬ ነገሥታት መኳንንት ሀብታሞች መጥታችሁ አጥምቁን ይሉ ነበርና ሂዳችው ተጠመቁ ለማለት።

🌿 ከሌሎች ወንዞች ለይቶ ጥምቀቱን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው ቢሉ?

1. ትንቢቱን ለመፈፀም

ዮርዳኖስ ወደሃላው ተመለሰ ብሎ መዝሙረኛው ዳዊት ስለ ዮርዳኖስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈፀም ነው።

2. የአዳምና የሄዋን የእዳ ደብዳቤአቸውን ለመደምሰስ

ከእለታት አንድ ቀን ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ስቃይ አጽንቶ ስመ ግብርናታችውን ጽፋችሁ ብትሰጡኝ ስቃይ አቀልላችኋለሁ ብሏቸው ስቃዩን ያቀለለልን መስሏቸው።

አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ነው ሔዋን የዲያብሎስ ባሪያ ናት ብለው ጽፈው ሰጡት።

ያን ተቀብሎ በሁለት እብነ ሩካም ጽፎ አንዱን ሲኦል አንዱን ዮርዳኖስ ጥሎት ነበርና በዮርዳኖስ የተጣለውን በጥምቀቱ ለመደምሰስ ዮርዳኖስን መርጧል።

ሲጠመቅም እንደአምላክነቱ አቅልጦ እንደ ሰውነቱ ረግጦ የእዳ ደብዳቤአቸውን አጥፍቶላቸዋል ።

በሲኦል የጣለውን በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ ደምስሶታል።

ጌታችን ዮሐንስን "አጥምቀኝ" ሲለው

"ሌላውን
በአንተ ስም
በአብ ስም
በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለው አንተን በማን ስም ላጥምቅህ?" አለው።

"የቡሩክ አብ ልጁ ብርሃንን የምትገልጥ ይቅር በለን የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ እነሆ ክህነትህ እንደ መልከጼዴቅ ክህነት ለዘለአለም ነው" እያልክ አጥምቀኝ አለው።

+የአብ ልጅ መሆኑን

+ብርሃን የሚገልጥ መሆኑን

+ይቅር ባይ መሆኑን

+የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን

+ክህነቱ ዘለዓለማዊ መሆኑን እየመሰከረ አጥምቆታል

🌿ጥምቀቱን በውሃ ያደረገው ስለምን ነው ቢሉ?

+ውሃ በዙፋን ካለ ንጉሥ በአደባባይ እስካለ ጽኑስ ለሁሉ የሚገኝ ነው።

+ውሃ ጽንፍ እስከ ጽንፍ ይፈሳል ጥምቀትም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ይደርሳልና

+ውሃ ከእድፍ ያነጻል ጥምቀትም ከኀጢአት ያነጻልና

+ውሃ የወሰደው ፍለጋ የለውም በጥምቀትም የተሰረየ ኀጢአት በፍዳ አያስዝምና

+ውሃ መልክ ያሳያል መልክ ያለመልማል

ጥምቀትም መልክአ ነፍስ ያሳያል መልክአ ነፍስ ያለመልማልና

+በውሃ የታጠበ ልብስ እየቀደም እየነፃ ኃይል ግዘፍ እየነሳ ይሄዳል

ምእመናንም ተጠምቀው ገድል ትሩፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰሩ እየጨመሩ ይሄዳሉና

+ርብቃ ለይስሐቅ የታጨችው ውሃ ስትቀዳ ነው

ምእመናንም ለክርስቶስ ሙሽራነት የሚታጩት በውሃ ተጠምቀው ነውና

+በውሃ ቀድሞ ሰብአ ትካት ሰብኣ ግብጽ ጠፍተው ነበርና ውሃ ለመአት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ብለውት ነበርና ለመአትም ለምሕረትም እንደተፈጠረ ለመግለጽ ከሁሉም ውሃን መርጦ በውሃ ተጠመቀ።

በመአር በወተት በወይን በዘይት ተጠምቆ ቢሆን ኑሮ ሀብታሞች እንጂ ድሃዎች አያገኙትምና ሁሉ በሚያገኘው በውሃ ተጠመቀ።

ሲጠመቅም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዷል።

🌿መንፈስቅዱስን ስለምን ርግብ አለው ቢሉ?

+ርግብ ሀዳጊተ በቀል ናት መንፈስ ቅዱስም ሀዳጌ በቀል ነውና

+ርግብ በኖህ ጊዜ ኀፀ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ ስትል ቆጽለ እፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበስራልና

+ርግብ ክንፋን ቢመቷት እንቁላልዋን ቢሰብሩባት ቤታን ካላፈረሱባት ቦተዋን አትለቅም መንፈስ ቅዱስም ኀጢአት ቢሰሩም ለንስሓ ይጠራል እንጂ ፈፅሞ ካልካዱት አይርቅምና ።

🌿ጥምቀቱን በመአልት ያላደረገው በሌሊት ያደረገው ስለምነው ቢሉ?

በመአልት አድርጎት ቢሆን መንፈስ ቅዱስ በቁሙ ርግብ ነው ብለው በተጠራጠሩ ነበርና

🌿አሁንስ ርግብ አለመሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ ?
ጌታችን የተጠመቀ ከሌሊቱ አስር ሰአት ነው ፤በአስር ሰአት ወፎች ርግቦች አይበሩም ተሀዋስያን ከቦታቸው አይንቀሳቀሱምና በዚህ ርግብ አለመሆኑ ይታወቃል።

መንፈስ ቅዱስ የወረደው ከውሀው ከወጣ ከዮሀንስ ከተለየ በሇላ ነው፤ ከውሃው ሳለ ወርዶ ቢሆን ለቀድሶተ ማያት የወረደ ነው ባሉ ነበርና።

ከዮሐንስ ጋራም ሳለ ቢሆን ስለ ክብረ ዮሐንስ የወረደ ነው ባሉ ነበርና ።

ሲወርድም ረቦ ወርዷልቢሉ
አብ ምሉእ ነው ፤አንተም ምሉእ ነህ
እኔም ምሉእ ነኝ ሲል ነው።

አንድም አሰይፎ ወርዷል ቢሉ፤ የብሉየ መዋእል የአብሕይወት ነኝ፤የብሉየ መዋእል የአንተም ህይወት ነኝ።

እኔም ብሉየ መዋእል ሕይወት ነኝ ሲል ነው።
ወርዶም ራሱን ቆንጠጥ አድርጎ ይዞታል

አብ አኃዜ ዓለም ነው
አንተም አኀዜ ዓለም ነህ
እኔም አኀዜ ዓለም ነኝ ሲል ነው።

መውረዱ ለአብነት ነው

እናንተም ስትጠመቁ እንደዚህ እወርድላችዋለው ሲል ነው።

ከዚህ በሃላ አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ብሎ ልጁ መሆኑን መስክሯል።

🌿ጌታችን ሲጠመቅ አንድነት ሶስትነት ተገልጿል

ወልድ በመጠመቅ
መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በመውረድ
አብ በደመና ሁኖ በመመስከር

አንድ ሲሆኑ ሶስት ሶስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸው ተገልጧል ማቴ 3÷13-17።

+++መልካም በዓል+++

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
25👌1😍1😇1
"መኑ ይወርድ አዲስ የጥምቀት መዝሙር" ZwT || ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)
ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን - Zema WeTibeb zMK
"መኑ ይወርድ"
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ{፪}
አሐዱ እምነ ሠለስቱ ወልድ/ክርስቶስ ውእቱ{፪}

ዳዊት በመዝሙሩ የተነበየለት
ውኆች አይተው ደንግጠው የሸሹት
ኮረብቶች እንደእንቦሳ ዘለው ያከበሩት
በውኃ የተጠመቀው እርሱ(፪) ነው መድኃኒት

በልዩነት መንፈስ ታጥሮ ለነበረው
ህዝብና አህዛብ ተብሎ ለተለየው
በዮርዳኖስ ተጠምቆ አንድ ያደረገን
ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ እግዚአብሔር ነው

በአዳም እና ሄዋን የነበረውን እዳ
ደምስሶ ሊያድነን ከዘለዓለም ፍዳ
በሰውነቱ ረቅቆ በአምላክነቱ የሻረው
ወልደ እግዚአብሔር ወልደ(፪) ማርያም ነው

ጌታችን ሲጠመቀ በዮሐንስ እጅ
ምሥጢር ተገለጠ የድኅነት አዋጅ
መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አብም በደመና
ተገልጠው አሳዩ ወልድ ወልደ አምላክ ነውና

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
28😍1😇1
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
"ከውኃ እንዴት እንወለዳለን የሚል ሰው ካለ እንዴት ከአፈር ተወለድን ብዬ እጠይቀዋለሁ!!!" ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን፥ አደረሳችሁ።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
19😇5😍2
Audio
መጽዐ ቃል እም ደመና ዘይብል ዘይብል፤(፪)
ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር።(፪)

መጣ ቃል ከደመና እንደዚህ የሚል፤(፪)
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይኽ ነው።(፪)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
20😇2
ጥር ፲፪
ቃና ዘገሊላ


"የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች"
ዮሐ ፪:፭

@Ethiopian_Orthodox

ቃና ከናዝሬት ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ በገሊላ አውራጃ የምትገኝ ከተማ ስትሆን በወቅቱ ትንሽና ገጠራማ መንደር ናት፡፡ ነገር ግን በውስጧ በተደረገው ተአምር መጽሐፍ ቅዱስ ስለመዘገባት ሁሌም የሚታወስ ታሪክ ያላት ሥፍራ ናት፡፡

ቃና ጌታችን ሁለት ታላላቅ ተአምራት ያደረገባት መንደር ስትሆን አንዱን ተአምር በቅርበት (በአካል ተገኝቶ) ሁለተኛውን ደግሞ በርቀት (ቃል ብቻ ተናግሮ) ያደረገው ተአምር እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ይህውም የጌታችን ቀዳሜ ተአምር የሆነው ቃና ሠርግ ቤት ተአምር ሲሆን፤ ሁለተኛው በቅፍርናሆም የንጉሥ ባለሟል የሆነ አንድ ሹም ጌታ ወደ ገሊላ እንደመጣ ሰምቶ ከቅፍርናሆም ሠላሳ ኪሎ ሜትር ተጉዞ በመምጣት ልጁ በንዳድ (yellow fever) መታመሙን ነግሮት ወደቤቱ ወርዶ እንዲፈውስለት ለመነው ፡፡ ዛሬ በሚሊየን የሚቆጠሩ ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች በአፍሪካና ኢስያ ብሎም በኢትዮጵያ ለሞትና ለስቃይ የሚዳረጉበት ህመም መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ ለአፍሪካ ህጻናትና እናቶች ሞት ይርቅ ዘንድ ጌታ ሆይ ቃል ተናገር ሞት ሰምቶ ይደንግጥ ያለ እድሜ ሞት ይጥፋ እንበለው፡፡ጌታ ግን ለሹሙ ልጁ እንደማይሞት ሲነግረው ይህንን አምኖ ሄደ ልጁ ባለበት ቦታ ሆኖ ጌታ በተናገረበት ሰዓት ተፈወሰለት፡፡ ይህንን ነው በርቀት የተደረገ ተአምር የምንለው፡፡ ዮሐንስ ፬፥፵፮-፶፬

የቃና ዘገሊላ ሠርግ የጌታችን የመጀመሪያ ተአምር ነው ሲባል ከልጅነቱ ጀምሮ ተአምራትን ያደርግ እንደነበር ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዱናል፡፡ ነገር ግን በግልጥ በአደባባይ በህዝብ ፊት ማስተማር የጀመረው ከሠላሳ ዓመቱ በኋላ ነበር፡፡ይሄውም በብሉይ ልማድ ለማስተማር በነቢያነት የሚመረጡትና የሚላኩት ከሠላሳኛው እድሜ በኋላ ነበርና ነው፡፡ የቃና ገሊላ ሠርገኞችን ስም መጽሐፍ ቅዱስ በስም ባይጠቅስልንም ሊቃውንት ዶኪማስ እንደሆነ ሲያስተምሩ ለእመቤታችን ዘመድ መሆኑንም የሚጽፉም አሉ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ይህንን ተአምር ሲናገር “እንዲህ በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሠርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ይላል”፡፡ በሰርጉ ጌታ የተገኘው ብቻውን አይደለም እናቱና ደቀመዛሙርቱ ነበሩ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ቤተክርስቲያን ፈጣሪ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስትሰብክ እመቤታችንን ቅዱሳንን የማትለየው፡፡ ይህንን እንድንሰብክ የነገረን ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡

በክርስቲያኖች ልብ በህይወታችን በኑሮአችን ጌታን እንደማንለየው ድንግል ማርያምን ቅዱሳንን አንለይም፡፡እርሱ በአምላክነቱ ድንግል ማርያም በእናትነትዋ ቅዱሳን በምልጃቸው አንለያቸውም ፡፡ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ”። ዮሐ ፲፭፥፭ ዛሬ የአለም ሩጫ የመናፍቃን ተንኮል ትውልዱን ከድንግል ማርያም መለየት ከቅዱሳን መለየት አላማቸው አድርገውታል፡፡ ምናልባት መብቱን ቢያገኙ ቅዱስ ዮሐንስን በዚህ ምዕራፉ ጌታን አልሰበከም ይሉት ይሆን?

ጌታ በቃና ዘገሊላ ተአምር የጀመረው በሠርግ ቤት መሆኑን ቅዱስ ዮሐንስ ሲናገር በቃና ሠርግ ነበር ነው የሚለው፡፡ ይሄውም ሠርግ ቤትን የተአምር መጀመሪያ ያደረገበት ምክንያት ሰይጣን የሰውን ልጅ የመጀመሪያ ኃጢያት በማሰራት ያፈረሰው የጋብቻን አንድነት በመሆኑ በማዳኑም ሂደት የጉሰቆለ ጋብቻን ወደ ቀደመ ቅድስናው ለመመለስ ጋብቻን ለመባረክ በሠርግ ቤት ጀመረ፡፡

ሰይጣን አዳምንና ሔዋንን ከእግዚአብሄር ከለያቸው (ዕፀ በለስን ከበሉ) በኋላ መግባባት መስማማት አቃታቸው፤ አንዱ አንዱን ይከስ ጀመር አንድ አካል መሆናቸው ቀረ፡፡አዳም ህይወቴ ያላትን ሔዋንን አጥፊዬ ናት አላት፡፡ የጋብቻ አንድነት ጠፋ፤ ውድቀት ወደ ቤተሰብ ገባ፡፡አለመታዘዝ በዘር ወደ ሰው ልጅ ሁሉ ደረሰ፡፡ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ”፡፡ ሮሜ ፭፥፲፪

ስለሆነም ጋብቻን ይቀድስ ያከብር ዘንድ የሰው ልጆችን ብሎም የአዲሲቷን የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን መሰረት የሆነው ቤተሰብ የሚመሠረተው ከተቀደሰ ቤተሰብ በመሆኑ ጋብቻን መባረክ የመጀመሪያ ተአምር እንዳደረገ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይነግረናል፡:

የቃና ገሊላ ሠርግ የጌታችን ፍጥረታት የሚታዘዙት፤ እንዲሁም የእመቤታችን ምልጃ የተገለጠበት ተአምር ነበር ፡፡ይህንንም የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው”። ሠርጉ መካከል ላይ ወይን ጠጅ አለቀ ይህ ለሰርገኛው ትልቅ ሀፍረት ነው ነገር ግን እርሷ ግን ጭንቀታቸውን፤ችግራቸውን ስላወቀች ያውም ሳያማክሯት የልባቸውን ሐዘን አውቃ ወይኑ ማለቁን ነገረችው፡፡ ከዚህ በላይ ለእመቤትችን የምልጃ ማስረጃ ምን ይሆን? ፡፡ዛሬም እንደዶኪማስ ሠርግ ሕይወታችን ብዙ ነገር ያልቅበታል። በተለይ ያለንበት ዘመን በሰዎች ዘንድ ፍቅር፤እምነት፤ሰላም የጠፋበት መተማመን የጎደለበት በመሆኑ እመቤትችን ልጅዋን ፍቅር እኮ የላቸውም፤ እምነት እኮ የላቸውም፤ ሰላም እኮ የላቸውም፤ በማለት የጎደለንን እዲሞላልን ትጸልያለች፤ጌታም ልመናዋን ወዶ ሲመልስ ጊዜዬ ገና አልደረሰም ሲል አማናዊውን ወይን ደሜን የምሰጥበት ጊዜ ገና አልደረሰም ማለቱ ነው፡፡ ጌታም ለእናቱ ልመና ይህንን የማላደርግበት ምክንያት የለም በማለት ሲመል፤ “ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት”። ይህንን ቃል ነው እንግዲህ ካንቺ ጋር ምን አለኝ ስላላት ምልጃዋን አልተቀበለም በማለት ትርጉሙን ማጣመም የሚፈልጉት፡፡ ነገር ግን የንባቡም ሆነ ትርጉሙ ልመናሽን የማልቀበልበት የማላደርግበት ምክንያት የለም ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይህንንም ቅዱሳት መጻሕፍት ሲያስረዱ፡- ኤልያስን በቤቷ የተቀበለች የሰራጵታዋ ሴት ልጅዋ በሞት ሲለይባት ታገለግለው የነበረውን የእግዚአብሔር ሰው ኤልያስን፦ "የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ ኃጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?" አለችው። ፩ኛ ነገ ፲፯፥፲፰ ይህን ማለቷ በእኔና ባንተ መካከል ምን ጠብ አለ ለማለት እንጂ የንቀት አነጋገር እንዳልሆነ መገንዘብ ይገባል፡፡
ከሰው የወጣው መናፍስት ኢየሱስን ባየው ግዜ “በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ” በማለት ሲናገር አንተ እኔን ማዘዝ አትችልም የሚል ትርጉም አይሰጥም፡፡

በዚህም መሰረት የእናቱን ልመና ስለተቀበለ "እርሷም እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው፡፡" ይላል በዚህም ሰው አምላኩን ፈጣሪውን ይሰማ ይታዘዝ ዘንድ እንዲገባ አስተማረችን፡፡ የስራውን መጀመሪያ ባደረገው በዮርዳኖስ ሲጠመቅ እግዚአብሄር አብ የኢየሱስን ተወዳጅ ልጅነት እንዲሁም በደብረ ታቦር ላይ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ”። ማቴ 17፡5 እመቤታችንም የተናገረችው እግዚአብሄር አብ በዮርዳኖስ የተናገረውን በደብረ ታቦር ስለ ልጁ የመሰከረውን ቃል ነው፡፡
17😇2
በአጠቃላይም የመጽሀፍትን ትርጉምና የአነጋገር ዘይቤ ካለማወቅ የሚመጣ ስህተት ከመሆኑም ባሻገር ለገዛ ጥፋት መጻሕፍትን የሚያጣምሙ ስለመኖራቸው፤ ሲናገር “ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ”። ፪ኛ ጴጥ. ፫፥፲፮
ከዚያም በውሃ የተሞሉ ጋኖች ወደ ወይን ተለወጡ፡፡ ይህ ተአምር በዮሐንስ ወንጌል ከተጻፉት አምላክነቱን ከገለጸባቸው ሰባት ምልክቶች (ተአምራት) ውስጥ ሲሆን በፍጥረታት ላይ ስልጣን እንዳለው ያሳየበትም ነበር፡፡ መርከቢቱን ከማእበል መናወጽ ፤ደቀመዛሙርቱን ከመጨነቅ አድኖ ማእበሉን ጸጥ ባደረገ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ፍጥረታት ለእርሱ መታዘዙን ሲያዩ፤”ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ “። ይላል፡፡ ከዚህም ባሻገር እርሱ ሰው ሆኖ ተገልጦ የሰውን አልጫ ማንነት በእርሱ የድህነት ሥራ ለወጠ፡፡ የብዙዎቻችንን የትላንት ማንነት በኃያአት ያሳለፍነውን ጊዜ ውሃችንን ለውጦት ነው በቤቱ እንድንኖር ያደረገን፡፡ ኢሱስም ቀድተው ለአሳዳሪው እንዲሰጡ አዘዘ፡፡

በዚህመ ዶኪማስ ተደነቀ በደስታ ተሞላ ታዳሚዎቹም የተለወጠው ወይን ጠጅ ከመጀመሪያው በእጅጉ በመብለጡ ተገርመው “ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው”። ሰውም በአግዚአብሄር ሲለወጥ እንዲሁ ነው። በኃጢአት ያሳለፈው ህይወት መራራ ነው። በእግዚአብሔር መደገፍ ሲጀምር፤ ማመን ሲጀምር፤ የመረረ ሀይወቱ ተለውጦ ለሌሎች መጣፈጥ ይጀምራል፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ፍቅር ካልቀመሰ በቀር ሊያውቀው አይችልም፤ እርሱን ለማወቅ ቃሉን መጠጣት፤ ስጋውና ደሙን መንፈሳዊውን ምግብ መመገብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ነው የክርስቲያኖች እምነት መንፈሳዊ ህይወት የሚቀይረው፤ ለመንግስቱ የሚያበቃው፡፡ ደቀመዛሙርቱ ይህንን ቃና ወይን መለወጥ ባዩና በቀመሱ ግዜ እምነታቸው ጨመረ “ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ” ይለናል፡፡ በአጠቃላይ የቃና ዘገሊላ በዓል ብዙ የምንማርበት ሲሆን የጌታ ህይወት ለዋጭነት፤ የድንግል ማርያምን አማላጅነት ተገልጦ፤ ያየንበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው፡፡

የአምላካችን ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

©መ/ር ንዋይ ካሳሁን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
22🙏3😇3
Audio
"እንዘ ስውር"
እንዘ ስውር እምኔነ ይእዜሰ ክሡተ ኮነ(፪)
ተአምረ ወመንክረ ገብረ መድኃኒነ በቃና ዘገሊላ ከብካብ ኮነ ማየ ረሰየ ወይነ(፪)

©በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
21😍4🕊2😇2
ጥር ፲፬
ጻድቁ አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)


ጥር አሥራ አራት በዚህች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተወለዱበት እና ወደ ደብረ ዳሞ የወጡበት ነው።

እኚህ አባት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግስት እደና ይባሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድርያ ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓረገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡

የንጉሳዊ የቅንጦት ኑሮ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ ማዕረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል።

በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችን ኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም ከአባ ፍሬምናጦስ በኋላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ተሸክሞ አክሱም አድርሷቸዋል፡፡

ተመልሰውም ሄደው ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱም ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡

አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀ መዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሰዋል፡፡

ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/91፥11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡

ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላም ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡

ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁ ብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት ሾመውላቸው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ ተሰውረዋል፡፡

የጻድቁ አባታችን ረድኤት በረከታቸው እንዲሁም አማላጅነታቸው አይለየን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
12👍5
አባ አረጋዊ
@Ethiopian_Orthodox
"አቡነ አረጋዊ"
ጽድቅህ ጠርቶናል አባትነትህ
በቅድስና ያማረ ሕይወትህ
ጌጥ ውበታችን አባ አረጋዊ
መናኝ መነኩሴ መልአክ ምድራዊ (፪)

ተቃኝተህ ስላደግክ በመንፈስ ቅዱስ
ወደ ፅርዕ ተጓዝክ ወደ አባ ጳኩሚስ
ተዘጋጅተህ ነበር ለችግር ፈተና
ዘሚካኤል አለህ ሰጥቶህ ምንኩስና (፪)

ለኢትዮጵያ ምእመናን አባት ተብለሃል
ወንጌል በማስተማር ብዙ አትርፈሃል
መጻሕፍት ተርጉመህ ያበረከትክ ለአበው
የአንተስ ትሩፋት እፁብ ነው ድንቅ ነው (፪)

የዓለም ጨው ሆነህ አጣፈጥካት ምድርን
በልባችን ሳልካት ቤተ ክርስቲያንን
ደብረ ሀሌ ሉያ ደብረ ዳሞ ቅድስት
የፈውስ ቦታ ናት መካነ ትኅርምት (፪)

ልክ እንደ አባቶችህ አስተዋይ ስለሆንክ
ገና ወጣት ሳለህ አረጋዊ ተባልክ
የሥጋን ሞት ሳታይ ተሰውረህ ከምድር
ብሔረ ሕያዋን ተቀላቀልክ በክብር (፪)

©በቦሌ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ በፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
17🥰2😍2
ጥር ፲፭
ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ


ጥር ዐሥራ አምስት በዚህች ዕለት የከበረ ሕፃን ቂርቆስ :እናቱ ብፅዕት ኢየሉጣ ዳግመኛ ለከበረ ሕፃን ቂርቆስ ማኅበር የሆኑ ዐሥራ አንድ ሺህ አራት ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ።

በዚያንም ወራት የክብር ባለቤት የሆነ ክርስቶስን በሚያምኑ የክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራና ስደት ሆነ። ስሟ ኢየሉጣ የሚባል አንዲት ሴት ነበረች እርሷም ከታናሽነቷ ጀምራ ደግ ናት ስደትም እንደሆነ በሰማች ጊዜ መኰንኑን ከመፍራት የተነሣ ሕፃኗን ይዛ ከሮም ከተማ ተሰዳ የኪልቅያ አውራጃ ከሆነ ከጠርሴስ ደርሳ ከዚያም በሀገሮች ውስጥ እየተዘዋወረች ተቀመጠች።

ወደዚያች አገርም ያ ከእርሱ የሸሸችው መኰንን እለእስክንድሮስ መጣ ጭፍሮቹም ክርስቲያኖችን ፈለጓቸው። ይቺንም ቅድስት ኢየሉጣን አግኝተው ያዝዋትና ወደ መኰንኑ አደረሷት የክርስቲያን ወገንም እንደሆነች ነገሩት።

መኰንኑም ሴትዮ ተናገሪ ከወዴት ሕዝብ ወገን ነሽ ነገድሽ ምንድን ነው ሀገርሽስ ወዴት ነው አላት። የከበረች ኢየሉጣም እንዲህ ብላ መለሰችለት የአንጌቤን ሰው ለሆንኩ ለእኔ ወገኖቼ ለኢቆንዮን አገር አለቆች የሆኑ ኤሳውሮሳውያን ናቸው እኔም በአንተ ምክንያት ሸሽቼ ነበር እነሆ ዛሬ ግን በእጅህ ውስጥ ነኝ አለችው።

መኰንኑም በእጄ ውስጥ እንደተገኘሽ ታውቂያለሽን አላት አሁንም የሚሻልሽን ምረጪ ስምሽንም ተናገሪ እኔንም እሺ በይኝና ለአማልክት ሠዊ የከበረች ኢየሉጣም ለረከሱ አማልክት እኔ አልሰዋም አለችው መኰንኑም ስምሽን ስጪ ተናገሪ አላት እርሷም የኔ ስም ክርስቲያን መባል ነው አለችው። መኰንኑም ይህስ ስንፍና ነው የሚጠቅምሽ አይደለም እንዳትሞቺ ስምሽን ስጪ ተናገሪ አላት። የከበረች ኢየሉጣም የኔ ስም ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞት የሚሽረው በሰዎች ዘንድ የምጠራበትን ከፈለግህ ስሜ ኢየሉጣ ነው ብላ መለሰችለት።

መኰንኑም ጽኑ የሆኑ ሥቃዮችን በላይሽ ሳይመጣ ተነሥተሽ መሥዋዕትን ለአማልክት አቅርቢ አላት። የከበረች ኢየሉጣም ዕወነት ነገርን ለመሥራት የምትሻ ከሆነ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነ ሕፃን ልጅ ይፈልጉ ዘንድ ወደ ሀገሩ መንደር ላክ ወዳንተም ያምጡትና የምንገዛለትንና የምናመልከውን እርሱ ይንገረን አለችው።

ያን ጊዜም የሦስት ዓመት ልጅ ይፈልጉ ዘንድ መኰንኑ ወታደሮችን ላከ የሀገር ሰዎችም ልጆቻቸውን ሠውረዋልና አላገኙም ከዚያም ከከተማው ቅጽር ውጭ በፀሐይ መውጫ ወዳለው በረሀ በኩል ወጡ የቅድስት ኢየሉጣንም ልጅ አገኙት ይህ ሕፃን የስንት ዓመት ልጅ ነው ብለው ስለርሱ ጠየቁ ሰዎችም ይህ ሕፃን የሦስት ዓመት ሲሆን የክርስቲያናዊት መበለት ልጅ ነው አሏቸው።

ያንንም ሕፃን ይዘው ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑም መልኩ የሚያምርና ደም ግባት ያለው እንደሆነ በአየው ጊዜ ደስ የምትል ደስተኛ ሕፃን ሰላምታ ይገባሃል አለው። ሕፃኑም እኔን ደስተኛ ማለትህ መልካም ተናገርክ ላንተ ግን ደስታ የለህም እግዚአብሔር ለዝንጉዎች ደስታ የላቸውም ብሏልና ብሎ መለሰለት መኰንኑም ሕፃኑን ሳልጠይቅህ ይህን ያህል ትመልስልኛለህን አለው። ሕፃኑም ገና ከዚህ የሚበዛ ነገርን እመልስልሃለሁ አለው።

መኰንኑም ሕፃኑን ስምህ ማን ነው አለው ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ሕፃን ስሜ ክርስቲያን መባል ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ዳግመኛ እንዳትሞት ስምህን ንገረኝ አለው የከበረ ሕፃንም ስሜ ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞክሼ ስም የምትሻ ከሆነ እናቴ የሰየመችኝ ቂርቆስ ነው።

መኰንኑም ሕፃን ቂርቆስን እሺ በለኝና ለአማልክት ሠዋ በሥጋህም ስታድግ እሾምሃለሁ በብዙ ወርቅና ብርም አከብርሃለሁ አለው። ሕፃኑም የሰይጣን መልእክተኛ ለዕውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ አለው።

መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ ቆዳውን እንዲጨምቁትና እንዲገፉት አዘዘ። የከበረች ኢየሉጣም የልጅዋን ትዕግሥት ባየች ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነችው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ጨውና ሰናፍጭ አምጡ አለ የሁለቱንም አፍንጮቻቸውን ከፍተው ያንን ጨውና ሰናፍጭ እንዲጨምሩባቸው አዘዘ ያን ጊዜ ሕፃኑ ትእዛዝህ ለጕረሮዬ ጣፋጭ ሆነ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ ብሎ ጮኸ።

ሁለተኛም መኰንኑ እንዲህ ብሎ አዘዘ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች አምጡ ሰባቱን በእናቱ አካላት ውስጥ ጨምሩ በሕፃኑም ሁለት በጆሮዎቹ ሁለት በዐይኖቹ ሁለት በአፉና በአፍንጫው አንድ በልቡ ጨምሩ እንዲህ ሲጨመርበት ጆሮዎቹ እንዲአሩ ዐይኖቹም ይጠፉ ዘንድ አንደበቱም ይቃጠል ዘንድ ወደ ልቡም ጽኑ ሕማም ገብቶ እርሱ ከዚህ ዓለም በሞት እንዲለይ ለእናቱም እንዲሁ አድርጉ ችንካሮችም በቅዱሳኑ በሥጋቸው ሁሉ ተጨመሩ።

የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ትእዛዝ የብረቶቹ ግለት ጠፍቶ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ ጤነኞችም ሆኑ መኰንኑም ወደ ወህኒ ወስዳችሁ በዚያ አሥራችሁ ዝጉባቸው አለ።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ የሥቃይ መሣሪያ ይሠራ ዘንድ አንዳዝዘው ብረትን የሚያቀልጥ ሰው አምጡልኝ አለ። በአመጡለትም ጊዜ ሰይጣኑ ወደ መኰንኑ ልብ ገብቶ አንደበቱን ዘጋውና መናገር ተሳነው ሕፃኑ ፈጥኖ አክሊልን ለመቀበል እንደሚተጋ ሰይጣን ስለ አወቀ ስለዚህ ዘጋው።

ከዚህም በኋላ ሕፃኑ ሠራተኛውን ጠርቶ እኔንና እናቴን የሚያሠቃዩበትን የሥቃይ መሣሪያ መሥራት ትችላለህን ይህ መኰንን ግን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም አለው ሠራተኛውም እንደምትሻው በል ንገረኝ እንደምታዝዘኝ እኔ መሥራት እችላለሁ አለው።

ሕፃን ቂርቆስም ሊአዝዝ ጀመረ እንዲህም አለ ሁለት መላጫዎች ስፋታቸው አራት ክንድ የሆነ ለእኔና ለእናቴ ሥራ። ዳግመኛም የሚያስጨንቅ ራስን የሚመታና የሚሰብር አንገትንም የሚያሥር የሚዝቅም ሹካ ዐይንንም የሚያወልቅ አካልንም የሚበሳሳ አፍንጫንም የሚያጣምምና የሚሰብር ጆሮንም የሚልጥ ሕዋሳትን የሚፈታና የሚለያይ እንደ ልጓም ሁኖ ምላስን የሚቆርጥ በሰውነትም ውስጥ ገብቶ የሚንቀሳቀስ ቆላፋ ጉጠትን ጐኖችንም የሚፍቅና የሚቆለምም አስጨናቂ የሆነ ጉልበቶችንና ጭኖችን የሚሰብር ጅማቶችንም የሚቆራርጥ ሥሮችንም የሚመዝ በዚችም አስጨናቂ መሣሪያ ጅማቶችን የሚታታ አድርግ።

ዳግመኛም በላም አምሳል ሰፊ መቀመጫ ከናስ ሥራ ሦስት ቀዳዳዎችንም በዚያ መቀመጫ ውስጥ ቅደድ። በቁመቴም ልክ ሦስት ችንካሮችን ሥራ የችንካሮቹንም ራስ ከናስ አድርገህ በውስጡ ከሚጠሩት ዘንድ ፈጽሞ የማይለይ ልዩ ሦስት ብለህ ጻፍ።

ዳግመኛም ጠምዝዞ ወደ ላይ የሚያወጣ ሁለት መሣሪያ ሁለት መጋዞችን ሁለት የብረት ምጣዶችን ሥራ አሁንም አንድ ታላቅ ጋን ሠርተህ በውስጡ አንገትን የሚጠመዝዝና የሚሠነጥቅ ተሽከርካሪ መሣሪያ አድርግ።

በውስጥ የተሸሸገ የሆድ ዕቃን የሚመረምር እጅን ከብረት ሥራ እኔ የጻዕር ስቃይን የምሠቃይበት ይህ ነው አለ። ብረት ሠሪውም ሰምቶ እጅግ አደነቀ የሚረዱትንም ከሀገር ውስጥ መቶ ሠራተኞችን ሰብስቦ መሥራት ጀመረ በአርባ ቀንም ጨረሰ።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ እለእስክንድሮስ ቂርቆስንና እናቱን ወደ አደባባይ ያመጡአቸው ዘንድ አዘዘ ያን ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ ነበርና እንዲህም አለ ሕፃኑንና እናቱን ከቆዳቸው ጋር ራሳቸውን ላጩአቸውና በላያቸው የእሳት ፍሞችን ጨምሩ እርር ብለው እንዲቃጠሉ ዳግመኛም አራት ችንካሮችን ከትከሻዎቹ እስከ ተረከዙ ድረስ እንዲተክሉበት አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ ሥቃዮችን ከርሱ አራቀ።
14
ዳግመኛም ከጥዋት እስከ ማታ ከሥቃይ መሣሪያዎች ውስጥ ጨምረው አዋሏቸው ግን ማሠቃየት ተሳናቸው። ከዚህም በኋላ ከማምጠቂያው ውስጥ ጨምረው መገዙአቸውና አመድ እስከሆኑ ከቅባትና ከጨው ጋር በብረት ምጣድ ውስጥ ቆሉአቸው ጌታችንም ከሞት አስነሥቶ አዳናቸው።

ወደ መኰንኑም በገቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው በእውነት ከሙታን ተለይታችሁ የተነሣችሁ ከሆነ ይህ ጫማዬ ከእግሬ ወጥቶ እንደ ቀድሞው ሕያው እንዲሆን አድርጉ ሕፃን ቂርቆስም በጸለየ ጊዜ ያ ጫማ ታለቅ በሬ ሆነ ከአንገቱም ፍየል ወጣ።

በዚያንም ሰዓት ለዐሥራ አንድ ሽህ አራት ሰዎች በሬውንና ፍየሉን አርደው ምሳ እንዲያደርጉላቸው መኰንኑ አዘዘ እንዲህም አለ ይህ በቅቷቸው ከጠገቡ ከዚህም ሌላ ምግብ ካልፈለጉ የተሠራው ሁሉ ዕውነተኛ ነዋሪ ነው። ከዚህም በኋላ አርደው ምሳ አደረጉላቸውና ከፍየሉ ሥጋ ስድስት እንቅብ ከበሬው ሥጋ አራት እንቅብ አተረፉ መኰንኑም የተረፈውን ሥጋ አይቶ ወደ ባሕር እንዲጥሉት አዘዘ።

መኰንኑም ቢያፍር የሕፃኑን ምላስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ምላሱን መለሰለት ዳግመኛም በታላቅ ጋን ውኃ እፍልተው ሕፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እናቱም አይታ ፈረች። ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር በጸለየላት ጊዜ አምላካዊ ኃይልን አሳደረባትና ከልጅዋ ጋር ወደ ጋኑ ገባች። እንደ ውርጭም ቀዝቀዛ ሆነ ደግሞም በውስጡ መንኰራኲር ወዳለበት የብረት ምጣድ እንዲጨምሩአቸውና ሥጋቸው እሰከሚቦጫጨቅ እንዲስቡአቸው አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕይወት አወጣቸው።

መኰንኑም እነርሱን ማሸነፍ በተሳነው ጌዜ ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚያን ጊዜ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ሕፃን ቂርቆስንም የምትሻውን ለምነኝ አለው።

ሕፃኑም ሥጋዬ በምድር አይቀበር ስሜን ለሚጠራ መታሰቢያዬን ለሚያደርግ ቤተ ክርስቲያኔን ለሚሠራ የተጋድሎዬን መጽሐፍ ለሚጽፍና ለሚያጽፍ ወይም ለሚያነበው ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ለሚያገባ በውስጧም ለሚጸልይ ለሁሉም ፍላጎታቸውን ስጣቸው ኃጢአታቸውንም ይቅር በል ስሜም በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ በሰውም ላይ እባር ቸነፈር በእህልም ላይ ድርቅ የውኃም ማነስ አይሁን።

መድኃኒታችንም የለመንከኝን ሁሉ እሰጥሃለሁ አንተም በቀኜ ትኖራለህ ሥጋህንም ኤልያስ በዐረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖራለሁ አለው ሕፃን ቂርቆስም በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት ጌታችንን አመሰገነው። ከዚህም በኋላ በሌሊቱ እኩሌታም ከእናቱ ጋር አንገቱን ተቆረጠ መድኃኒታችንም በማይጠፋ አክሊል ጋረደው ነፍሶቻቸውንም በታላቅ ክብር ከእርሱ ጋር አሳደገ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
17
ቂርቆስ አንጌቤናይ
@Ethiopian_Orthodox
"ቂርቆስ አንጌቤናይ"
ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ (፪)
አንጌቤናይ ወልደ አንጌቤናይት(፪)

ገና በሦስት ዓመት ወንጌልን ሰብከኻል
ስለ ጌታ ፍቅር ቆመህ መስክረሃል
እኔ ክርስቲያን ነኝ ብለህ ስትናገር
ቅድቲቷ እናትህ ተደስታ ነበር
       አዝ= = = = =
ስለ ክርስትና መከራ ቢያበዙ
ጦርና ጋሻውን ሰይፍንም ቢመዙ
በእምነትህ ጸናህ ያለመደራደር
ከንጉሥ ፊት ስትቆም አስረውህ የፊጥኝ
       አዝ= = = = =
ነበልባለ እሳትን በአንተ ላይ ቢያነዱ
ውኃው የሚያጓራ እንደ ነጎድጓዱ
ቅድስቲቷ እናትህ ኢየሉጣም ፈርታ
ጸለይክላት ቂርቆስ ልቧ እንዲበረታ
       አዝ= = = = =
እኔ ቅርንጫፍ ነኝ እናትህን ብትላት
ስለ እናትህ ብለህ ጽናትን አድላት
ብለህ በለመንከው በጸለይከው ጸሎት
ዳግም እናትህን በእምነት ወለድካት
       አዝ= = = = =
ከእሳት ነጎድጓድ ድምጹ ከሚያስፈራው
ከሚንተከተከው ፍል ውኃ ከሆነው
ከእናትህ ጋራ ብትገቡ ከእሳቱ
ገብርኤል ሲመጣ ሁሉም ሆነ ከንቱ
      አዝ= = = = =
መዳንህን አይቶ ንጉሡ አፈረ
ፍጹም በመናደድ ልብሱን ተረተረ
ወታደሩን ጠርቶ አንገትህን ሰየፈው
ከቅዱሳን ሕብረት ነፍስህን ደመረው

©በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ውሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
32🙏5🥰3👍1
ጥር ፲፰
ዝርወተ አፅሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ


ጥር ዐስራ ስምንት በዚች ቀን የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ አፅሙ ተቃጥሎ ተደቁሶ የተበተነበት ነው፡፡

ይኸውም ሰባ ነገሥታት ማሰቃየት በሰለቻቸው ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አውጥተው ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት ንጉሥ ዱድያኖስ አዘዘ፡፡ አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረግፉት ድረስ እንዲህ አደረጉበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከስቃይ ብዛት የተነሳ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ሥጋውንም በሙሉ በእሳት አቃጠሉት አመድም ሆነ፡፡

ከሐዲው ንጉሥ ዱዲያኖስ የተቃጠለውን የሥጋውን አመድ አፍሰው በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ወስደው ምዕመናን ራሩን አመዱን እንኳን እንዳያገኙት በነፋስ እንዲዘሩት አዘዘ፡፡ ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ማለት ነው፡፡ ወታደሮቹም የሥጋውን አመድ በተራራ ላይ ነስንሰው የተመለሱበት፣ የሥጋው አመድ ያረፈበት ዕፅዋት ሁሉ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ያሉበት፣ ጌታችን ከመላእክት ጋር ተገልጦ አራቱን የምድር ነፋሳትንም የቅዱስ ጊዮርጊስ የሥጋውን ትቢያ እንዲሰበስብ አዝዞ "የኔ ሆይ! የመረጥኩህ ወዳጄ ጊዮርጊስ ከሞት ተነሥ አትፍራ፤ እኔ አዝዤሀለሁና" ሲል ኀያሉን ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠራው። ያን ጊዜ ልዑል ንዑድ ጊዮርጊስም ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሽራ ምንም ሕማም ሳይኖርበት ተነሣ።

መድኃኒታችንም ባረከው። "አትፍራ፤ ይኸንን ከሀዲ ንጉሥም እስክታሳፍረው ድረስ እኔ አጸናሀለሁ። 'ከእንዲህስ ወዲህ አምላኩ ከእጃችን ሊያድነው አይችልም' እንዳይሉ እነዚህን ከሐድያን ነገሥታትና የረከሱ ጣዖታቸውን ታሳፍራቸው ዘንድ ተነሣና ወደ አገር ውጣ፤ ሰላሜ ለዘለዓለም ከአንተ ጋር ይሁን።" አለው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ተናግሮ ሳመው። በፍጹም ምስጋናም ወደ ሰማይ ዐረገ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጌታችን ይህንንም ቃል ኪዳን የተቀበለበት ቀን ነው፡፡

አምላካችን ከሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት ይክፈለን! ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንዲሁም ሐገራችን ኢትዮጵያን ሰማዕቱ ከፈተና ይጠብቅልን! አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
23😇2😍1🤗1
Audio
"ጊዮርጊስ በዚያች ቀን"
ጊዮርጊስ በዚያች ቀን ከፈተናው አንፃር
ስለሃይማኖቱ የታየው ምን ነበር

ያመነውን አምላክ አላውቀውም እንዲል
በሥልጣን በገንዘብ እርሱን ለመሸንገል
የዱዲያኖስ ጭፍሮች ነገር ሲያሴሩበት
ልቡናው ምን አለ ሲቀርብ ለመሥዋዕት

ስገድ ባሉት ጊዜ ሰው ለሠራው ምስል
ትዝ አለው ጊዮርጊስ የአምላኩ ሕያው ቃል
ከሠለስቱ ደቂቅ ከዳንኤል ጋር
በእሳት ነበልባል ውስጥ ተአምር ሲሠራ

ቂርቆስ ኢየሉጣን ከመቃጠል ዋጅቶ
ያቀዘቀዘውን ፍሉን ውኃ አጥፍቶ
አስታውሷል ጊዮርጊስ ያንን ኃያል ጌታ
መስቀል መሸከሙን በዚያች ጎሎጎታ

ጴጥሮስና ጳውሎስ አባቶቹን መስሎ
ሞትን አሸነፈ በእምነት ተጋድሎ
እንድንጸና በእምነት ይህችን ዓለም ንቀን
በሰማዕቱ ምልጃ አምላክ ይጠብቀን

©በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
42😇3👏1😍1