የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቤተክርስቲያን #በአርቴፊሻል #ኢንተለጀንት #ማምለክ #ጀመረች

በጀርመን አንዲት ቤተ ክርስቲያን በአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ የተመራ አምልኮ መርሃ ግብር መደረጉን ተሰምቷል።
ዎርዚ ኒውስ እንዳስነበበው፥ በደቡብ ምስራቃዊ ጀርመን የባቫርያ ግዛት ኑረምበርግ ከተማ የምትገኝ አንዲት የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ናት የአምልኮ መርሃ ግብሩን ሙሉ በሙሉ በአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ የተፈበረከ አምልኮን ያካሄደችው።
አርብ አርብ ለሚካሄደው የአምልኮ መርሃ ግብር ማስታወቂያ ያዩ ሰዎችም በገፍ ወደ አምልኮ አዳራሹ ከ1 ሰዓት በፊት በመምጣት ተሰልፈው ተስተውለዋል ነው የተባለው።

ChatGPT chatbot በሚባለው AI የተመራው የ45 ደቂቃ ፕሮግራም ከ300 በላይ ሰዎች መሳተፋቸውም ተሰምቷል።

ፕሮግራሙ የተለመዱትን የጸሎት፥ መዝሙር፥ ቅዳሴ እና የባርኮት ጊዜ መርቷል።
በሰው ምትክ አቫታር የሚባሉ በሰው ምስል የሚሰራ ሰው መሰል ገጸባህሪ ፕሮግራሙን መርቶታል። አግራሞትን የሚያጭረው ደግሞ አባታችን ሆይ የሚለው የፕሮግራም ማሳረጊያ ጸሎት ጋር ሲደርስ አንድ አንዶች ምቾት እንደነሳቸው መግለጻቸው ነው።

አስተባባሪዎቹ በAI እዚያው መድረክ ላይ የተቀናበረ መዝሙርም መለቀቁን ተናግረዋል።

AI በእለቱ የእምነት መግለጫ ሲመራ፥ ሲባርክም ነበረ። የበረከቱ ወቅት እንደ ሰው እጅ የሚያነሳ አቫተር ቢጠበቅም እንደ ጉርድ ፎቶ ከወገብ በላይ ብቻ ያለው ገጸባህሪ ባርኮት ሲያደርግ ነበረ።
ይሄ ዜና የተሰማው በሺዎች የሚቆጠሩ ተመራማሪዎች AI የሚፈጥረው አደጋ ብዙ ስለሆነ ቢያንስ ለ6 ወራት ገደብ ይጣልበት ሲሉ ፊርማ አሰባስበዋል። የትዊተር ባለቤት እውቁ ኢሎን መስክ ከፈራሚዎቹ መካከል ነው።

እንደኔ ብዙ ጥያቄ ያላቹ ኮሜንት ላይ እየገባቹ አስቀምጡ፥ AI ይመልሰው ይሆናል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/J-5Jkn5axcI
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍3