የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.3K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከሪል_ላይፍ_ሚኒስትሪ_ጋር በመተባበር ከተለያየ አብያተክርስቲያናት ህብረት ለተወጣጡ አገልጋዮች #ደቀመዝሙር_አድራጊ_ቤተክርስቲያን_ሚናዋ_ምንድነዉ? በሚል ርዕስ #ስልጠና_ተሰጠ። ስልጠናዉ ግንቦት 16 እና 17 ቀን 2015ዓ/ም የሚከናወን ሲሆን ዛሬ በተጀመረዉ የስልጠና ጊዜ የካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ክፍል ሃላፊ ፓስተር ስንሻት ተካ ፕሮግራሙን በፀሎት አስጀምረዋል። የካዉንስሉ ፅህፈት ቤት ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ደቀመዝሙር ለማድረግ መጀመሪያ ደቀመዝሙር መሆን ያስፈልጋል ሌሎቹን ደቀመዝሙር ለማድረግ ደግሞ መትጋት ያስፈልጋል” ብለዋል። ከሪል ላይፍ ሚኒስትሪ የመጡ አገልጋዮች ጥናታዊ ፅሁፎችን በማቅረብ ስልጠናዉን የሰጡ ሲሆን ስልጠናዉ ግንቦት 17 ቀን 2015ዓ/ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፦https://youtu.be/tv9Rkx0HuiU
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!