የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.23K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#እግዚአብሔር_በአደጋው_ህይወታቸውን_ላጡ_ቤተሰቦች_መጽናናት_ይስጣቸው

ነሃሴ 11/2013ዓ.ም በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ ላይ በደረሰው አደጋ የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት እጅግ ማዘኑን እገልጻለሁ።

የተፈጠረው አደጋ አሳዛኝ ቢሆንም ለምን ሆነ አንልም ይልቁንም በመላው አለም የምትገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ በአደጋው የተጎዱ ቤተሰቦችን ልናጽናናቸው እና ከጎናቸው ልንሆን ይገባል።

የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በተቻለን መጠን አንድነታችንን ለመግለጽ 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ድጋፍ የምናደርግ ሲሆን ሌሎቻችን በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀአገር ውጪ የምትገኙ ይህንን አደጋ የሰማቹ በተቀመጡ ድጋፍ የማድረጊያ አማራጮች በመጠቀም ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ጭምር ትልቅ ስራ የሰራች እና ለብዙዎች በረከት የሆነች ቤተክርስቲያን ነች።

እግዚአብሔር በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናት ይስጣቸው እያልኩኝ ለሚደርሰው ማንኛውም ነገር ጸሎት አስፈላጊ ስለሆነ ሁላችንም በጸሎታችን እናስባቸው።

እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባረክ። አመሰግናለው

መጋቢ እሸቱ ወርቄ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት