የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.23K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#እግዚአብሔር_መፅናናትን_እንዲያበዛላችሁ_ፀሎታችን_ነዉ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ እና በአከባቢዉ ማህበረሰብ ላይ በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ በህይወት እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት እጅግ ማዘናችንን እንገልጻለን።

በትላንትናው እለት በጣለው ከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ህይወታቸውን ላጡ እና ንብረቶቻቸው ለወደመባቸው አካላት ካውንስሉ መጽናናትን ይመኛል።

ስለሆነም ሁላችሁም የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አባላት ቤተእምነቶች፤ ሚኒስትሪዎች እና አገልጋዮች በሙሉ ከሴሚናሪው እና ጉዳት ከደረሰባቸው አካላት ጉን በጸሎታችሁ እና ልዩ ልዩ ድጋፍ በማድረግ አብራችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና ለተጎጂ ቤተሰቦች እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲያበዛላችሁ ፀሎታችን ነዉ

1 ተሰ. 4፥13-18

ቄስ ደረጀ ጀምበሩ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጠቅላይ ፀሐፊ