የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
11 የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የልማት ድርጅቶች ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የ713 ሚሊዮን ብር የሰብዓዊ እርዳታ ፕሮጀክት ይፈ አደረጉ።

በአማራ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች ለተቸገሩ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ለመስጠት 11 የሀገር በቀል ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት የልማት ድርጅቶች ከኮምፓሽን ኢንተርናሽሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የ713 ሚሊየን ብር ሰብዓዊ እርዳታ ፕሮጀክት መጀመራቸውን አሥታወቅዋል። ይህ ፕሮጀክት በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው ከ200,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ያቀርባል። ይህ አዲስ ፕሮጀክት ወሳኝ የሆኑ የምግብ ፣ የጤና ፣ የንጽሕና እና የመጠለያ ቁሳቁሶችን በማቅረብ የሕይወት አድን ድጋፍ ይሰጣል።

ፕሮጀክቱ በሶስቱ ክልሎች በሰብዓዊ እርዳታ ፣ በምግብ ስርጭት እና በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ማገገም ላይ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለማጠናከር ያለመ ነው። በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት የመንግስት ተወካሆች ፣ የሲቪል ማህበርሰብ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የሚድያ ባለ ድርሽ አካላት ተገኝተዋል።

የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ደሳለኝ በስፍራው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ኮምፓሽን ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ለብዙዎች ተስፋ መለምለም ምክንያት ሆኗል። የሃይማኖት የዘር እና የጸታ ልየታ ሳያደርግ በመስራት ተኪ የሌለው ተቋም ነው። የተጀመረው ስራ ስኬታማ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽዖ ማድረግ ይጠበቅብናል። ይህንን እርዳታ ለረጂዎች ስናስተላልፍ እኛም እናንተ ነን በሚል የፍቅር ስሜት መሆን አለበት።” በማለት ተናግረዋል።

በስፍራ ተገኝተው ስለኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ፤ ስለ እሴቶቹ ፤ ስለሰራቸው ስራዎች እና ዛሬ ይፋ ስለተደረገው ፕሮጀክት ማብራሪያ የሰጡት ደሞ የኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ጸሃይወጣ ታደሰ ናቸው።

በንግግራቸውም “ርህራሄ የእሴቶቻችን መሰረት እና የስራችን ዋና መርህ ነው። እናም ለተጎዱ እና ለተቸገሩ ወገኖች አቅም የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ የርህራሄ መገለጫ ነው። በዛሬው ቀን ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ለዘላቂ መፍትሔ ያላሰለሰ ጥረት መደረግ እንዳለበት የሚያሳስብ ነው።” በማለት ተናግረዋል።
አክለውም የኮምፓሽን ዋነኛ ትኩረት በዘላቂነት ላይ የተመሰረተ የልጆች ሁለንተናዊ እድገት ልማት እንደሆነ ያነሱ ሲሆን “የኮምፓሽን የልማት ስራ የተመሰረተው አጋር ተቋማትን አቅማቸውን በማጎልበት የአከባቢያቸውን ልዩ ፍላጎት እንዲረዱ እና ምላሽ እንዲሰጡ በማገዝ ላይ ነው። በድህነት ውስጥ የተወለዱም ሆነ ያደጉ ልጆች ልብ ውስጥ ድህነት እንዳይወለድ ማድረግ ይቻላል ይገባልም።” በማለት ተናግረዋል።

አጋር አካላት ለፕሮጀክቱ ስኬት ማድረግ የሚችሉትን በሙሉ እንዲያደርጉ ጥሪ ባቀረቡበት ንግግራቸውም የመንግስት አካላት እያደረጉት ያለው የላቀ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። ወንድም ታገል ማቴዎስ የ11ዱን የልማት ተቋማት እና የታሰበውን ፕሮጀክት አስመልክቶ አጠር ያለ ሪፖርት አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንን በመወከል የተገኙት አቶ ኢብራሂም ሰኢድ በበኩላችው ዘላቂ መፍትሔ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል። ከገንዘብ ሚኒስቴር በስፍራው የተገኙት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አስማረ “የእምነት ተቋማት ሀገርን ለመርዳት በዚህ መልኩ ሲሰሩ ማየት በጣም አስደሳች እና ልብ የሚነካ ነው።” በማለት ተናግረዋል።

ይህ ዝግጅት የፕሮጀክቱን ይፋዊ ጅማሬ ከማብሰሩ በተጨማሪ ተባባሪ አካላት በቀጣይ የትብብር ስራዎችን ላይ እንዲወያዩበት አስችሏል፡፡

በሲቪል ማህበርሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ስር በሕጋዊነት የተመዘገቡት 11 የሀገር በቀል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የልማት ድርጅቶች ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተገኘውን የገንዘብ ድጋፍ በመጠቀም ፕሮጀክቱን በጋር የሚተገብሩ ሲሆን ይህም ለተቸገሩ ማህበረሰቦች ወሳኝ እፎይታ እንደሚሰጥ ተገልጿል። እነዚህ የልማት ድርጅቶች ከአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በተጨማሪ በመላ አገሪቱ ለዓመታት ሁለንታዊ የልማት መርሃ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ አማኑኤል ዴቢሶ
ስካይላይት ሆቴል ፡ አዲስ አበባ
👍1
በቀጣና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን “የተዘጋጀ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሊደርሺፕ ትራንስፎሜሽን ሚኒስትሪ ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያን ለተወጣጡ ወጣት መሪዎች ሴሚናሪ ተካሄደ።

በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን “አንድ የተዘጋጀ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሊደርሺፕ ትራንስፎርሜሽን ሚኒስትሪ ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ለተወጣጡ ወጣት መሪዎች ሴሚናሪ ተካሂዷል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት መጋቢ ዳንኤል ሲሆኑ እንዲሁም በእለቱ ወጣትነት እግዚአብሔር ለሀገር እና ለቤተ ክርስቲያን ለለውጥ እና ለተሃድሶ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረው የወጣትነት ጊዜ በምን አይነት መንገድ መያዝ እንዳለበት አስተምረዋል።

መጋቢ ዳንኤል ወጣትነት በሰዎች እድሜ ውስጥ ወርቃማ የእድሜ ክልል እንደመሆኑ ወጣትነትን በሚገባ ለመጠቀም እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማወቅ መትጋት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ቄስ ትዕግስቱ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 1 ላይ ከሚገኘው ክፍል ላይ በመነሳት ወጣቶች እንዴት ራሳቸውን ከሀጥያት ማራቅ እንዳለባቸው አስተምረዋል።

በከሰዓቱ ፕሮግራምም ላይ ወንድም ለማ ደገፋ ጥሪ ፣ ብቃት ፣ ስብዕና እና ተግባራት በተሰኙ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ትምርህትን ሰጥተዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቃልኪዳን እንዳለ