የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ያህዌ ያሪስ የወንጌል ዓለም ዓቀፍ ቤተ ክርስቲያን "ልባም ሴቶች" በሚል ከመላው የኢትዮጵያ ክልል ከተወጣጡ ሴቶች ጋር የጸሎትና የአንድነት ጊዜ አካሄደች።


‎ ነሀሴ 3/2017 ዓ.ም በያህዌ ያሪስ የወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን "ልባም ሴቶች" በሚል መሪ ቃል ከመላው የኢትዮጵያ ክልል ከተወጣጡ ሴቶች ጋር ስለ ሀገር ስለ አብያተክርስቲያናት፣ስለ አገልጋዮች እንዲሁም ለባለ ስልጣናት ጸሎት የተደረገ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የአንድነትና የጸሎት ጊዜ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ በጉድና ቱምሳ ሁለንተናዊ ማሰልጠኛ ተካሂዷል።

‎ያህዌ ያሪስ የወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን መስራችና ባለራዕይ ነቢይት አስቴር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ይህ በቤተክርስቲያኒቱ የመጀመሪያ ፕሮግራም መሆኑን አንስተው ልባም ሴት በቤተሰብ በቤተክርስቲያን በሀገር የታወጀውን ክፉ አዋጅ የምትሽር መሆኗን ተናግረዋል። ልባም ሴቶች ለሀገር ጉዳይ በተለይም ለሰላም አጥብቆ እንዲጸልዩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎በዚህም መርሐግብር ላይ ዘማሪት መክሊት ማሞ በዝማሬ ያገለገለች ሲሆን የአግዚአብሔርን ቃል ነቢያት መሳይ ታደሰ አካፍለዋል።

‎ያህዌ ያሪስ የወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ቤተክርስቲያንን በመትከል ወንጌልን ለሰው ልጆች ሁሉ እየደረሰች የምትገኝ ቤተክርስቲያን መሆኗ በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል ።

‎ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
👍2
ሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ከፎከስ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄደ።

ሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ከፎከስ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር ዛሬ ነሀሴ 3 2017 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂዷል።

በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ፕሬዚደንት ሪቨረንድ ታሪኩ ገብሬ እንዲሁም የፎከስ ሚኒስትሪ ናሽናል ዳይሬክተር የሆኑት ሚልኪያስ ኢትቻ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር የተገኙ ሲሆን በዛሬው ቀን ሃምሳ ተማሪ ለሃምሳ ቀን የሚል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አስተባብረው ችግኞችን ተክለዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ተስፋኢየሱስ ፍቃዱ
ሰሜንን ለኢየሱስ አገልግሎት ከቢሊግራሃም ኢቫንጀሊስትክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በአማራ ክልል አንጾኪያ እና ገምዛ ወረዳ የሶስት ቀናት ስልጠና ሰጠ።

ሰሜንን ለኢየሱስ አገልግሎት ላለፉት 15 ዓመታት በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል ማለትም በአፋር ክልል፣ በአማራ ክልል፣ በትግራይ ክልል እንዲሁም ከሀገር ውጪ በኤርትራ የሚገኙ ወገኖችን በወንጌል ለመድረስ የሚሰራ አገልግሎት እንደሆነ የአገልግሎቱ አስተባባሪ የሆኑት ወንጌላዊ አለምዬ አሰፋ ያስረዳሉ።


ከሐምሌ 25 እስ 27 የተደረገው ስልጠና ከቢሊግራሃም አሶሴሽን ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን በማሰልጠኑ ላይም ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ወንደም ሰለሞን እና ወንድም አስልፍ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ወንጌላዊ አለምዬ አሰፋም ወንጌል ስርጭት አስለምክቶ ስልጠና ሰጥተዋል።


በስፍራውም ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የመጡ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ስልጠናው በተሳካ መንገድ እንዲሄድ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያደረጉትን ቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽንን እና የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዋና ቢሮን አመስግነዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ