በኢትዮጵያ አማኑኤል ህብረት የሥነ መለኮት ኮሌጅ የሐረር ቅርነጫፍ ከሶስት አመት በላይ በዲግሪ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 53 ተማሪዎችን አስመረቀ።
ኮሌጁ ሐምሌ 20/2017 ዓ/ም በመጽሐፍ ቅዱስ ስነ መለኮት ዘርፍ ተቀብሎ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለምረቃ ያበቃ ሲሆን ከአንድ ቤተ እምነት ቅጥር አልፎ በመውጣት በልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት እያገለግሉ ያሉ በርካታ አገልጋዮችንም ጭምር ተቀብሎ በማስተማር ላይ ያለ ኮሌጅ ነው ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም ኮሌጁ የአገልጋዮችን ህብረት በማጠናከር ረገድ በከተማ ውስጥ ላሉ ለአብያተ ክርስቲያናት በረከት የሆነ ኮሌጅ መሆኑም ተነግሯል።
በሐረር አማኑኤል ህብረት ቤተ ክርስቲያን በተካሄደው በዚህ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ እንደተገለፀውም ቤተክርስቲያኗ በዲግሪ መርሀግብር ተማሪዎችን ስታስመርቅ በምስራቁ ኢትዮጵያ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም ተገልጾዋል።
በዕለቱም የሐረር አማኑኤል ዋና መጋቢ ሲሳይ ታፈሰ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለተመራቂዎች አስተላልፈዋል።
የአገር አቀፉ የስነመለኮት ኮሌጅ ዲን የሆኑት መጋቢ ተስፋዬ ሽብሩና የኢትዮጵያ አማኑኤል የቤተ እምነቱ ፕሬዘዳንት መጋቢ ጌታሁን ታደሰ በተገኙበት የምረቃው ስነ ስርአት የተከናወነ ሲሆን በመጋቢ ጌታሁን ታደሰ በኩል የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ተሰብኳል።
በተጨማሪም ተመራቂ ተማሪዎች የነበራቸውን የትምህርት አመታት የመፅሃፍ ቅዱስ እውቀትን የገበዩበት እና እርስ በእርስም ቤተሰባዊ ህብረት ያጠናከሩትበት እንደነበረም ገልፀዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ

❤2
ኪንግደም ፓሽን ሰሚናሪ በጅማ ዞን ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ። ተስፋ ኢየሱስ ፍቃዱ
ኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ በጅማ ከተማ፣ በጌጣ-ሸዋና በአኮ በዲግሪና በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 62 ተማሪዎች የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የጅማ ከተማ ቦርድ ም/ሰብሳቢ መጋቢ ጸጋዬ ደፋርን ጨምሮ በርካታ ተጋባዥ የአብያተክርስቲያናት መሪዎችና አገልጋዮች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በጅማ ቤቴል መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሴሚናሪው ለ9ኛ ዙር ብቁ ናቸው ብሎ ያሰባቸውን 62 ተማሪዎችን በይፋ ያስመረቀም ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በዲግሪ 44 በድፕሎማ ደግሞ 22 ተማሪዎችን አስመርቋል።
በወንጌል ተልዕኮና ዓቃቤ እምነት ትምህርት ቤትነት የሚታወቀው ኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ በአሁኑ ሰዓትም በሀገር ውስጥ ያሉትን 80 ካንፓሶች ጨምሮ ፣ በምስራቅ አፍሪካና በኦለይን እንዲሁም ከከተማ ወጣ ያሉ ቦታወችን በመድረስና አብያተክርስትያናትን ለታላቁ ተልዕኮና ለእቀበተ እምነት ስራም በማስታጠቅ እየሰራም እንደሚገኝም የሴሚናሪ የስራ አመራር ቦርዶች ተነግሯል።
የኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ ፕሬዘዳንት ዶክተር ዘካሪያስ አዱኛ እንደተናገሩትም ሴሚናሪው ከዚህ ቀደም በእንግሊዝኛ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋች እያሰለጠነ፣ በርካታ ተማሪዎችን እያፈራ እንደሚገኝ በመጥቀስ ብቁ የሆኑ አገልጋዮችን ለቤተክርስቲያንና ለእግዚአብሔር መንግስት እያበረከተ ያለ ከፍተኛ የስነ-መለኮት ተቋም መሆኑንም በማንሳት ለወደፊትም እንደ ጅማ ባሉት አከባቢዎች ላይ በስነመለኮት ትምህርት ብቻ ሳይሆን በስልጠና እና በወንጌል ስርጭትም ረገድ እንደሚገባ ልንሰራ ይገባናልም ብሏል።
በመርሀ ግብሩ ላይም የሴሚናሪው ፕርሪንሲፓል ዶክተር ጋዲሳ መንገሻ ኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ ለቤተክርስቲያን አገልጋዮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን እየተጋ ያለ ተቋም መሆኑንም በማንሳት ሴሚናሪው ከዲፕሎማ እስከ ፒ ኤች ዲ ደረጃ ድረስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ መሆኑንም ጠቅሷል።
በምረቃ መርሐግብሩ ላይም ኪንግደም ፓሽን ሰሚናሪ በወንጌል አገልግሎት እድሚያቸውን ለጨረሱትና ለወንጌል ስራ ብዙ መስዋዕትነት በመክፈል የጌታን ወንጌል ላገለገሉትም ለቄስ ዘውዴ ዳቃ እውቅና በመስጠት አመስግነዋል። በመጨረሻም ሴሚናሪው ከፍተኛ ነጥብ ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት አበርክቷል።
መረጃውን ኪንግደም ፓሽን ሰሚናሪ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ አገኘነው።

❤2🔥1