በአሜሪካ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው እምነት እየጨመረ እንደመጣ ተገለጸ።
በቅርቡ በጋልአፕ ፖል የተደረገ ጥናት በአሜሪካ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ የነበራቸው እምነት ካለፉት አስርት አመታት በተለየ እየጨመረ መምጣቱን አመላክቷል።
በፈረጆቹ 2024 36 በመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን በቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ የሆነ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ይህም በ2022 ከነበረው 31 በመቶ የአምስት በመቶ እድገት ያሳየ ሆኖ ተገኝቷል።
ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ የተስተዋለው የመጀመሪያው እድገት ሲሆን ሴቶች፣ አፍላ ወጣቶች ፣ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን ድጋፍ እያሳዩ ካሉ አሜሪካውያን መካከል ይጠቀሳሉ።
በሃገሪቱ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ጥናቱ ሲያሳይ ለሪፐብሊካኖች ያለው ድጋፍ ከ49 በመቶ ወደ 64 በመቶ ያደገ ሲሆን በዴሞክራቶች ላይ አሜሪካውያን ያላቸው እምነት ደግሞ ከነበረበት ቀንሷል ፡ ለዚህም ዴሞክራቶች የሃይማኖት ተቋማትን በተመለከተ ያላቸው ጽንፍ የረገጠ አመለካከት እንደምክንያት ይነሳል።
በቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው እምነት እየጨመረ መምጣቱ እንዳለ ሆኖም በሀገሪቱ ቤተ ክርስቲያን ካላት ተዓማኒነት በላይ ትንንሽ ቢዝነሶች እና ወታደራዊ ተቋማት የበለጠ ተዓማኒነት አላቸው። ይህም በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን በግዜ ሂደት ያጣችውን ተዓማኒነት በማግኘት ላይ እንደሆነች ጥናቱ ያመላከተ ሲሆን ይህም በጊዜ ሂደት ውስጥ ማህበረሰብን የማነጽ ድርሻዋን ሊያሰፋው እንደሚችል ተነግሯል።
መረጃውን ከክርስቲያን ፖስት አገኘነው
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤3