የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.4K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ዳይናሚክ ቸርች ፕላንቲንግ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመተባበር ለ22 አገልጋዮች ሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጠ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ዳይናሚክ ቸርች ፕላንቲንግ ኢንተንራሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ በመሆን ስልጠና ሲያዘጋጅ ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።

ከዚህ በፊት በመጀመሪያ ዙር በነበረው ስልጠና በሁለት ጊዜያት 22 አገልጋዮችን የቤተ ክርስቲያን ተከላን አስመልክቶ ስልጠና ሰጥቶ ነበር።
በሁለተኛ ዙር ላይ ባዘጋጀው ስልጠና ላይም ከዚህ በፊት የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና የወሰዱ 22 አገልጋዮች የተገኙ ሲሆን የአሁኑ ስልጠናም ትኩረቱን ያደረገው ደቀመዛሙርትን ማበራከት ላይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በዙም የተካሄደውን ስልጠና የሰጡትም የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና የሰጡት የዳይናሚክ ቸርች ፖላንቲንግ ኢንተርናሽናል መስራች አል ሚደልተን እና የአገልግሎቱ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ሜሪሌይ ነበሩ።

ከማለዳው 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12 ሰዓት በሳሮማሪያ ሆቴል ሐምሌ 16 የተካሄደው ስልጠና ደቀመዛሙርትን ከማፍራት ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ሀሳቦች የተነሱበት እንደሆነ ተገልጿል።

ዳይናሚክ ቸርች ፖላንቲንግ ኢንተርናሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ በመሆን ሁለት ዙር ስልጠናዎችን የሰጠ ሲሆን ከዚህም በኋላ ከአመራር ጋር በተያያዘ ሶስተኛ ዙር ስልጠና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የውጪ ግንኙነት ዘርፍ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
2
የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያኖች ማህበር የተመሰረተበት 21ኛ አመት በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ አከበረ።

የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያኖች ማህበር የተመሰረተበት 21ኛ አመት በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።

በሀገራችን በሁለንተናዊ አገልግሎቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያኖች ማህበር በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባደረገው የ21ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ ወጣት አገልጋዮች እና ዘማሪዎች በስፍራው ተገኝተዋል።

በማለዳ የተጀመረው መርሃግብሩ ልጆችን የማጫወት እንዲሁም ደም የመለገስ መርሃግብርን ያካተተ ነበር።
ከሰዓት የነበረው መርሃግብርም አምልኮ ፣ የእግዚአብሔር ቃል ፣ የማህበሩ ድጋፍ የማሰባሰቢያ የተካሄደበት ነበር።

አርቲስት ሀገረወይን አሰፋ መድረኩን በመምራት ያገለገለች ሲሆን የማህበሩ የክብር አምባሳደር የሆኑት አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝ በስፍራው በመገኘት የሰው ልጆችን ለማዳን ስለሰራው ስራ እግዚአብሔርን አመስግነዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በሀገራችን በወንጌል የቀደሙ አባታቾ እና እንደ ኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና እንደ ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ያሉ ተቋማት ወጣትቾን በሰፊ ልብ እንዲያግዟቸው ጥሪ አቅርበው አባቶች በወጣቶች ያዘኑበት ነገር ካለም ወጣቶችን በመወከል አባቶችን ይቅርታ ጠይቀዋል።

ከዚህም ባለፈ በስፍራው መነባነብ የቀረበ ሲሆን የምስራቅ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ወጣት መዘምራን ፣ ዘማሪ መስፍን ጉቱ እንዲሁም ፓስተር እንዳለ ወልደ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሌሎች በስፍራው በመገኘት ጉባኤውን በዝማሬ አገልግለዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ