የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.47K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት የደንብ ማሻሻያን በተመለከተ ስብሰባ ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተመሰረተው በ2004 ዓ.ም ሲሆን ተቋሙ ከምስረታው ጀምሮ 7 አባል የሃይማኖት ተቋማትን በማቀፍ ለከተማችን ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።


የመስራች አባላት ቁጥር ከሰባት ወደ አምስት እንዲቀንስ እንዲሁም የስራ አመራር ቦርድ ከሰባት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ይህንንም ተከትሎ የዛሬው እለት የተካሄደው መርሃግብር ለቀድሞ የአዲስ አበባ የቦርድ አመራሮች ሰላምታ ለመስጠት እንዲሁም ለአዳዲስ የቦርድ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ለማድረግ የተዘጋጀ ነው።

የአጭር ጊዜ እቅድን በተመለከተ ከሌሎች የሀይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ ተቀራርቦ ስለመስራት እንዲሁም የተለያዩ ሀሳቦች በውይይቱ ላይ ተነስተው ነበር። ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋምት ጉባኤ መጋቢ ታምራት አበጋዝም የክፍለ ከተማና የወረዳ የመንግስት መዋቅሮች በየደረጃው ላሉ የሀይማኖት ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርጉ መሰራት እንዳለበት በጉባዔው መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

በቀጣዩ ጊዜያትም የረዥም ጊዜ እቅዶች እንደተያዙ እና በቀጣይ እንደሚሰራበት በካሳንቺስም ደግሞ የእምነት ተቋማት መገንቢያ ቦታ ከመንግስት እንደተሰጠ ገልጸዋል።

የአፈጻጸሙንም አቅጣጫ በተመለከተ በሚጠኑ ጥናቶች በተቻለ መጠን የሁሉም ሐይማኖት ተቋማት እሴቶች እና ተሳትፎ በተጠበቀ መንገድ ስለመስራት የተቋማት ነጻነትን ስለመጠበቅ ፤ የተቋሙን ዓላማ መሰረት አድርጎ መስራት ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተውበታል።

ክቡር ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደተናገሩት አዲስ አበባ ልዩ የሚያደርጋት የብዙ ሐይማኖት ተቋማት ባለቤት መሆኗ ነው።
የትኩረት አቅጣጫውም ስለሰላም ስኬት ግንባታ ስነምግባር እና ሞራል እሴት ግንባታ ማህበራዊ ሀላፊነትን ስለመወጣት እንዲሁም ስለአከባቢ ጥበቃ እንደሚሰራበት በጉባኤው ላይ ተነግሯል።

ማህበራዊ ቀውስን ለማስቀረት ከሚደረጉ ስራዎች ላይ በቀጣዩ ጊዜ በሰፊው መሰራት እንደሚጠበቅበት በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውስንል የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት መጋቢ አሸብር ከተማ በስብሰባው ላይ በተነሱ ሀሳቦች ደስታቸውን ገልጸዋል።


በስብሰባው ላይ ከተገኙት ታላላቅ የእምነት አባቶች መካከል ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀዲያ የስልጤና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ሼኽ ሡልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፣ ፓስተር አሽብር ከተማ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፣ አባ ጴጥርስ በርጋ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አ/አ ሀገረ ስብከት ሃላፊ ፣ ፓስተር ተሰማ ደሳለኝ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት የአ/አ ክልል ፕሬዚዳንት ይገኙበታል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ፡ ቃልኪዳን እንዳለ
5
“መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመራር” “Biblical Leadership” በሚል ስያሜ 3ኛ ዙር የሥልጠና መርሐ ግብር ተጀመረ

በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር እና በእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ትብብር ተግባራዊ እየተደረገ ባለው ፕሮጀክት የተዘጋጀው ሦስተኛው ዙር የሥልጠና መርሐ ግብር ተጀመረ።

በስልጠናው ላይ ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሆኑ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፥ ከሕግ ባለሙያዎች፥ ከከፍተኛ ትምህር ተቋማት፥ ከህክምና ሙያ ዘርፍ፥ ከምህንድስና ሙያ ዘርፍ እና ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ መሪዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

እኤአ 2023 ዓ.ም ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ተዋቅሮ እየተሰጠ ያለው ይህ ስልጠና “Catalyzing Leaders” በሚል ርዕስ የሚካሄድ ሲሆን ዓላማውም በተለያየ ደረጃ እና ሙያ ላይ የሚገኙ መሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በመጠቀም ለተሻለና ውጤታማ መሪ እንዲሆኑ መደገፍ ለዚህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በግብአትነት እንዲጠቀሙ ማበረታታት መሆኑ ተግልጾዋል።

በስልጠናው ላይ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለቸው መምህራንና የምርምር ባለሙያዎች በአሰልጣኝነት እየተሳተፉ ይገኛል።

መረጃው የኢትዮጵያ መጽሃፍ ቅዱስ ማህበር ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ ቤተልሔም ደረጄ
12🙏3🔥2