የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.47K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢቫንጀልየም ሚሸን ኢትዮጵያ ''ከቢጫ ወደ አረንጓዴ'' በሚል መርሐ ግብር በአዳማ የስልጠና እና የምክክር ጊዜ አደረገ።

ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደቡብ አዳማ ክልል የኢቫንጀልየም ሚሺን ኢትዮጵያ በመሐል አዳማ አጥቢያ ከ44 አጥቢያ ከመጡ የሚሸኑ አገልጋዮች እና የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር የትምህርት እና የምክክር ጊዜ አካሄዷል።

ይህ መርሐ ግብር “ከቢጫ ወደ አረንጓዴ” በሚል ርዕሰ የተደረገ ሲሆን በዕለቱም መጋቢ ዳመነ ደጉ “የሙሴ መሪነት እና አገልግሎት በሚል የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።

በመርሀግብሩ ላይም የክልሉ ዋና ጻሐፊ መጋቢ ሻሾ ቱሉ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ በመጥቀስ “ወንጌል በሚሸነሪዎች አማካኝነት በብዙ ዋጋ መክፈል ወደ እኛ ዘመን መጥቶአልና እኛም ዋጋ ከፍለን እናገልግል።” ካሉ በኃላም “ እኛም ቤተክርስቲያናችንን እንወቅ” የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የክልሉ የሚሸን አሰተባባሪ የሆኑት መጋቢ ብዙአየሁ ተሊላ “ከቢጫ ወደ አረንጓዴ” የሚለውን መርሐ ግብር እና በሚሸኑ በክልል እና በአጥቢያ ደረጃ እየተሰራ ስላለው ሰፊ የሆነ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለጉባኤው ገለጻ ካደረጉ በኃላ በቀረበው መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ምክክርና በቀጣይነት በተሻለ ሁኔታ ሊሰራበት የሚቻልበትን የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የፋይናንስ እና አስተዳደር መምሪያ ዓመታዊ የሥልጠና እና የምክክር ስብሰባውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጽሕፈት ቤት አካሄደ።

በመርሃ ግብሩም ከሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሲኖዶሶች የመጡ የፋይናንስና አስተዳደር ሀላፊዎች፣ የሲኖዶሶቹ ፀሐፊዎች፣ የጋራ ፕሮግራሞች የፋይናንስ ሀላፊዎች ተካፍለዋል።

የቤተ ክርስቲያን የፋይናንስ እና አስተዳደር መምሪያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰብለ አሰፋ እንደገለፁት የምክክሩ ዓላማ የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ ሥርዓትና የሀብት አስተዳደር ደረጃውን ጠብቆ እንዲቀጥል፣ ቤተ ከርስቲያን የምትጠቀማቸውን የፋይናንስ ሥርዓቶች መተግበራቸውን ማረጋገጥ እና ባሳለፍነው የበጀት ዓመት የተስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ ለመምከር መሆኑን ገልፀዋል። አንክሮት በመስጠትም ለውጤታማ የፋይናንስ ሥርዓት ክፍሎቹ የውስጥ ቁጥጥር ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በተያያዘ መልኩ አጠቃላይ የኦዲት ሪፖርት(Summurized Audit Report)፣ የ2026 በጀት ዝግችት(2026 Budget Proposal) ፣ የሂሳብ ሪፖርት(Financial Report) ፣ የውስጥ ቁጥጥር(Internal Come control) እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሥልጠናዎች እና ምክክሮች ተካሂደዋል።

በስብሰባውም ተጋባዥ ተናጋሪ የነበሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ የጡረታ ቦርድ፣ የኢንቨስትመንት እና ኢንሹራንስ ኮምሽን ኮምሽነር የሆኑት አቶ ገመችስ ማቴዎስ "በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት(Inflation) እና መደረግ በሚገባቸው ጥንቃቄዎችና ግብረ መልሶች" ዙሪያ ሰፊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
4
የኦድዮ ወይም በድምጽ የተዘጋጀ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ስርጭት በስደተኛ ጣብያዎች መከናወኑ ተገለፀ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በአሶሳ ዞን ሦስት ዋና ዋና የስደተኛ ካምፖች የሚገኙ ሲሆን በባምባሲ፣ በሸርቆሌ እና በጾሬ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ካምፖች በዋነኛነት ከጎረቤት ሀገራት በተለይም በደቡብ ሱዳን በተከሰተው ግጭት እና አለመረጋጋት የተሰደዱ ስደተኞች ያስጠለሉ ናቸው።

ሐምሌ 8 እና 9 /2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ከእነዚህ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለተመረጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች በሸርቆሌ በግሎባል ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስለ “እምነት በመስማት ይመጣል” ፕሮጀክት አገልግሎት እና አተገባበር ስልጠና ሰጥቷል።

በዚህ ስልጠና ላይ ከደቡብ ሱዳን፥ ከኡጋንዳ እና ከኮንጎ በጣብያው የተጠለሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋይ ስደተኞች የተሳተፉ ሲሆን በስልጠናው ላይ በእንግሊዘኛ፥ በአረብኛ፥ በመባን እና ኑኤር ቋንቋዎች የተዘጋጀ የአዲስ ኪዳን በድምጽ የማድመጫ መሳሪያዎች እና ወንጌል በፊልም የማሳያ ፕሮጀክተር መታደሉን ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።


ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
በዩናይትድ ኪንግደም የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን በጎዳና ላይ መስበክ እንዳትችል ወጥቶ የነበረውን ሕግ ማስቀረት መቻሏ ተገለጸ።

በምዕራብ ለንደን የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ባለችበት አከባቢ በጎዳናዎች ላይ ወንጌል መናገር እንዳትችል የሚያዝ መመሪያ በአከባቢው አስተዳደር ይፋ ተደርጎ ነበር።
የኢንግላን ኮከብ የእግር ኳስ ተጫዋች የሆነው ቡካዮ ሳካ ይገለገልባት የነበረችው የኪንግስቦሮ ቤተ ክርስቲያን በለንደን የሂሊንግደን አስተዳደር የሕዝብ ቦታዎች ጥበቃ ትዕዛዝ በማስተላለፉ ነበር በአስተዳደሩ ላይ ክስ የመሰረተችው። ከአስተዳደሩ የወጣው መመሪያ ሐይማኖታዊ ተቋማት በሕዝብ ቦታዎች ላይ የድምጽ ማጉያዎችን እንዳይጠቀሙ፣ በራሪ ወረቀቶችን እንዳይሰጡ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በአደባባይ ይዘው እንዳይወጡ የሚያግድ ነበር።


የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ይህ መመሪያ ይፋ እንደተደረገ ያወቁት በጸሎት ሕብረታቸው ላይ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን በጎዳና ላይ ወንጌል ሲናገሩ ቢያዙ እስከ 1000 ፓውንድ ድረስ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል መስማታቸው እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል። እናም መመሪያው “ጨቋኝ” ነው በማለት የተናገሩ ሲሆን ወንጌልን ለሌሎች ማጋራታቸውን እንደወንጀል መውሰዱ ተገቢ እንዳልሆነም ተናግረዋል።

ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመሩት መጋቢ ቱንዴ ባሎገን ለቴሌግራፍ “ወንጌልን ለሌሎች መናገር እንደ ክርስቲያን እምነትን የመግለጫ ዋና መሳሪያ ነው። እናም የወጡት መመሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ እንደታዘዝነው ማህበረሰባችንን ከመውደድ እንድንቆጠብ ከማስፈራራቱም ባለፈ ማድረጋችንን ወንጀል ያደርገዋል “ በማለት ተናግረዋል።

“በሕጋዊ መንገድ መመሪያዎችን ከመጋፈጥ ሌላ አማራጭ ማግኘት አልቻልንም። እናም መመሪያዎቹ እኛን ብቻ ሳይሆን በቦሮ የሚገኙ ሌሎች ቤተ ክርስቲያናት ላይም የሚያሳድረው ተጽዕኖ አሳስቦን ነበር። ከዚህም ባለፈ እንደዚህ አይነት መመሪያዎች በመላው ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ክርስቲያኖች ነጻነት ላይ ገደብ ሊያስቀምጥ የሚችል እንደሆነ ተገንዝበናል።” በማለት ተናግረዋል።


በሕግ በኩል ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያግዝ የቆየው ክርስቲያን ሌጋል ሴንተር ፤ መመሪያው ይፋ በተደረገ ማግስት የተወሰኑ ክርስቲያኖች በጎዳና ላይ ወንጌል እየሰበኩ በሚገኙበት ፖሊሶች ቀርበው ሕግ እየጣሱ መሆናቸውን እና ካላቆሙም የገንዘብ ቅጣት እንደሚገጥማቸው እንደነገሯቸው አሳውቋል።


ከዛም ባለፈ “ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ እና የነገስታት ንጉስ ነው።” የሚል ጽሁፍ የያዙ መልዕክቶቻቸውን ከሕዝብ እይታ ገለል እንዲያደርጉ ነግረዋቸው ነበር። ለሕዝብ እንዳይደርሱ ከተደረጉ መሳሪያዎችም መካከል “እግዚአብሔርን እንዴት አውቀዋለሁ?” እና “ክርስትና ምንድን ነው? የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ?” የሚል ርዕስ የያዙ በራሪ ወረቀቶች ይገኙበታል።


የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠበቃዎችም መመሪያው የአውሮፓን የሰብዓዊ መብት ኮንቬንሽን የሚጥስ እንደሆነ በመጥቀስ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተከራክረዋል። እናም በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በክርስቲያን ሌጋል ሴንተር በጋራ በተደረገው ጥረት አማካኝነት የወጣው መመሪያ እንዲሻሻል እና የጎዳና ስብከት ላይ የወጣው ገደብ እንዲነሳ ተደርጓል።

መጋቢ ባሎጐን በበኩላቸው በሕጉ መሻሻል እረፍት እንደተሰማቸው የተናገሩ ሲሆን “ዓላማችን በአከባቢያችን ለሚገኙ ነዋሪዎች ተስፋን እና የእግዚአብሔርን ፍቅር ማጋራት ነው። ለማህበርሰባችን የምናደርገው ነገር መደገፍ እንጂ መታፈን የለበትም ።” ሲሉ ተናግረዋል።

የክርስቲያን ሌጋል ሴንተር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አንድሪያ ዊሊያምስ “የክርስቲያኖች የጎዳና ላይ ስብከት በዩናይትድ ኪንግደም ረዥም እና የተከበረ ታሪክ አለው። እናም ሰሚዎች በሚሰሙት ሀሳብ ተስማሙም አልተስማሙም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል።” በማለት ተናግረዋል።

የአከባቢው ባለስልጣናት በበኩላቸው የመመሪያው አላማ ክርስቲያኖችን ያለመ ሳይሆን ፈቃድ ያልተሰጣቸው መርሀግብሮች እና የከተማዋን ሰላም የሚረብሹ ነገሮችን ለማስቆም ያለመ ነው በማለት አስተባብሏል።

ከዚህም ባለፈ የአከባቢው ካውንስል ለቤተ ክርስቲያኒቱ 20,000 ፓውንድ ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።
መረጃውን ከፕሪሚየር ክርስቲያን ኒውስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ አማኑኤል ዴቢሶ
12👍1
ኢንተርዲኖሚኒሸናል የስነ መለኮት ኮሌጅ ለ12ኛ ዙር ክርስቲያናዊ ማማከር በሚል ርዕሰ ስልጠና እየተሰጠ ነው ።


ኢንተርዲኖሚኒሸናል የስነ መለኮት ኮሌጅ ለ12ኛ ዙር የማማከር አገልግሎት ስልጠና የሰጠ ሲሆን በ2017 ብቻ ለ3ኛ ዙር እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ ሰልጠና ላይ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ የመጡ ከ150 በላይ ለሆኑ ለቤተክርስቲያን መሪዎች፣ መጋቢያን እና ለማማከር አገልጋዮች ከሐምሌ16-18 ቀን 2017 ዓ.ም በተቀባ ቃል ቤተክርስቲያን ስልጠናውን በመውሰድ ላይ ናቸው።

ከወጪ ሀገር በመጡት ለ32 አመት በማማከርና በሚሽን ላይ በሚሰሩት በዶ/ር ራቪ ዳንኤል ስልጠናው እየተሰጠ ነው።

የኮሌጁ ደይሬክተር ዶ/ር ታምራት ወርቁ ይህን ስልጠና ለየት የሚያደርገው ክርስቲያናዊ ማማከር ፣ማማከር ምንድነወ ፣በተለይም በቤተክርስቲያን ምን የማማከር ጉደዮች አሉ? በሚሉ አሳቦች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተናግረዋል።ዳይሬክተሩ አክለውም ስልጠናው በቀጣይነትም የሚቀጥል እንደሆነም ገልፀዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች ለኢሻኒጀሊካል ቴለቪዥን እንደተናገሩት ለግል ሕይወታቸውና በቤተክርስቲያን ውስጥ ላላቸው አገልግሎት ሰዎችን ለማገዝ ጠቃሚ የሆነ ስልጠና እንደሆነ አንስተዋል።

ኢንተርዲኖሚኔሽናል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ በኢሻንጀሊካል ኢንተርዲኖሚኔሸናል እንተርናሽናል ሚኒስትሪ ስር የሚሰራ ኮሌጅ ሲሆን ሚኒስትሪው በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በመመዝገብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2