የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢቫንጀልየም ሚሸን ኢትዮጵያ ''ከቢጫ ወደ አረንጓዴ'' በሚል መርሐ ግብር በአዳማ የስልጠና እና የምክክር ጊዜ አደረገ።

ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደቡብ አዳማ ክልል የኢቫንጀልየም ሚሺን ኢትዮጵያ በመሐል አዳማ አጥቢያ ከ44 አጥቢያ ከመጡ የሚሸኑ አገልጋዮች እና የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር የትምህርት እና የምክክር ጊዜ አካሄዷል።

ይህ መርሐ ግብር “ከቢጫ ወደ አረንጓዴ” በሚል ርዕሰ የተደረገ ሲሆን በዕለቱም መጋቢ ዳመነ ደጉ “የሙሴ መሪነት እና አገልግሎት በሚል የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።

በመርሀግብሩ ላይም የክልሉ ዋና ጻሐፊ መጋቢ ሻሾ ቱሉ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ በመጥቀስ “ወንጌል በሚሸነሪዎች አማካኝነት በብዙ ዋጋ መክፈል ወደ እኛ ዘመን መጥቶአልና እኛም ዋጋ ከፍለን እናገልግል።” ካሉ በኃላም “ እኛም ቤተክርስቲያናችንን እንወቅ” የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የክልሉ የሚሸን አሰተባባሪ የሆኑት መጋቢ ብዙአየሁ ተሊላ “ከቢጫ ወደ አረንጓዴ” የሚለውን መርሐ ግብር እና በሚሸኑ በክልል እና በአጥቢያ ደረጃ እየተሰራ ስላለው ሰፊ የሆነ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለጉባኤው ገለጻ ካደረጉ በኃላ በቀረበው መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ምክክርና በቀጣይነት በተሻለ ሁኔታ ሊሰራበት የሚቻልበትን የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የፋይናንስ እና አስተዳደር መምሪያ ዓመታዊ የሥልጠና እና የምክክር ስብሰባውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ጽሕፈት ቤት አካሄደ።

በመርሃ ግብሩም ከሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሲኖዶሶች የመጡ የፋይናንስና አስተዳደር ሀላፊዎች፣ የሲኖዶሶቹ ፀሐፊዎች፣ የጋራ ፕሮግራሞች የፋይናንስ ሀላፊዎች ተካፍለዋል።

የቤተ ክርስቲያን የፋይናንስ እና አስተዳደር መምሪያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰብለ አሰፋ እንደገለፁት የምክክሩ ዓላማ የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ ሥርዓትና የሀብት አስተዳደር ደረጃውን ጠብቆ እንዲቀጥል፣ ቤተ ከርስቲያን የምትጠቀማቸውን የፋይናንስ ሥርዓቶች መተግበራቸውን ማረጋገጥ እና ባሳለፍነው የበጀት ዓመት የተስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ ለመምከር መሆኑን ገልፀዋል። አንክሮት በመስጠትም ለውጤታማ የፋይናንስ ሥርዓት ክፍሎቹ የውስጥ ቁጥጥር ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በተያያዘ መልኩ አጠቃላይ የኦዲት ሪፖርት(Summurized Audit Report)፣ የ2026 በጀት ዝግችት(2026 Budget Proposal) ፣ የሂሳብ ሪፖርት(Financial Report) ፣ የውስጥ ቁጥጥር(Internal Come control) እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሥልጠናዎች እና ምክክሮች ተካሂደዋል።

በስብሰባውም ተጋባዥ ተናጋሪ የነበሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ የጡረታ ቦርድ፣ የኢንቨስትመንት እና ኢንሹራንስ ኮምሽን ኮምሽነር የሆኑት አቶ ገመችስ ማቴዎስ "በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት(Inflation) እና መደረግ በሚገባቸው ጥንቃቄዎችና ግብረ መልሶች" ዙሪያ ሰፊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
4