የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.47K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢቫንጀልየም ሚሸን ኢትዮጵያ ''ከቢጫ ወደ አረንጓዴ'' በሚል መርሐ ግብር በአዳማ የስልጠና እና የምክክር ጊዜ አደረገ።

ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደቡብ አዳማ ክልል የኢቫንጀልየም ሚሺን ኢትዮጵያ በመሐል አዳማ አጥቢያ ከ44 አጥቢያ ከመጡ የሚሸኑ አገልጋዮች እና የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር የትምህርት እና የምክክር ጊዜ አካሄዷል።

ይህ መርሐ ግብር “ከቢጫ ወደ አረንጓዴ” በሚል ርዕሰ የተደረገ ሲሆን በዕለቱም መጋቢ ዳመነ ደጉ “የሙሴ መሪነት እና አገልግሎት በሚል የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።

በመርሀግብሩ ላይም የክልሉ ዋና ጻሐፊ መጋቢ ሻሾ ቱሉ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ በመጥቀስ “ወንጌል በሚሸነሪዎች አማካኝነት በብዙ ዋጋ መክፈል ወደ እኛ ዘመን መጥቶአልና እኛም ዋጋ ከፍለን እናገልግል።” ካሉ በኃላም “ እኛም ቤተክርስቲያናችንን እንወቅ” የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የክልሉ የሚሸን አሰተባባሪ የሆኑት መጋቢ ብዙአየሁ ተሊላ “ከቢጫ ወደ አረንጓዴ” የሚለውን መርሐ ግብር እና በሚሸኑ በክልል እና በአጥቢያ ደረጃ እየተሰራ ስላለው ሰፊ የሆነ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ለጉባኤው ገለጻ ካደረጉ በኃላ በቀረበው መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ምክክርና በቀጣይነት በተሻለ ሁኔታ ሊሰራበት የሚቻልበትን የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2