የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.47K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአለም አቀፉ የሚሽን ማህበር ጉባኤ ላይ የእውቅና ሽልማት አገኘች።

በመካከለኛው አሜሪካ ሁንዱራስ እየተካሄደ በሚገኘውና ሁለተኛ ሳምንቱን በያዘው የአለም አቀፍ ሚሽን ማህበር (IMA) ጉባኤ እየተሳተፈች የምትገኘው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በመድረኩ በወንጌል ተልዕኮ እያከናወነች ላለው እንቅስቃሴና ከአሞር ቪንቪንቴ ቤተክርስቲያን ጋር ላላት አጋርነት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላታል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በመወከል በስፍራው የሚገኙት የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ሽልማቱን ሲቀበሉ "ይህ እውቅና ክርስቶስን ለመስበክ እና መንግስቱን በማህበረሰቦች መካከል ለመገንባት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ግሩም ማስታወሻ ነው።" ሲሉ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም አለም አቀፉ የሚሽን ማህበር ለወንጌል ስራ እንድንነቃቃ እያደረገ ስላለው አስተዋጽኦ አመሰግናለሁ ብለዋል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተለያየ አለም የሚገኙ አብያተክርስቲያናት በተካተቱበት አለም አቀፍ የሚሽን ማህበር (IMA) መስራች አባል መሆኗ ይታወቃል።
መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
3👍1
ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሺፕ ለ10 ተከታታይ ቀናት ለታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ሰጠ።


ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሺፕ ከሚሰጣቸው ስልጠናዎች መካከል CYIA (Christian Youth In Action/የክርስቲያን ወጣት ታላቅ ስራ) አንዱ ሲሆን ይህ ስልጠና በክረምት ወራት ለ10 ተከታታይ ቀናት ለታዳጊ ወጣቶች የሚሰጥ ሲሆን በዚህ አመት ደብረዘይት በተካሄደው ስልጠና ላይ የሰለጠኑ ተማሪዎች ብዛት 104 መሆኑ ተግልጾዋል።

ከነዚህም መካከል 23 የሚሆኑ የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ተመርቀዋል። በዚህ የአስር ቀን ቆይታ ሰልጣኝ ተማሪዎች ለአምስት ቀናት ልጆችን በተለያዩ ቤተክርስቲያናት ላይ አስተምረዋል። እንዲሁም የጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት አድርገዋል።

በአጠቃላይ 3130 የሚሆኑ ልጆች ወንጌልን የሰሙ ሲሆን 590 የሚሆኑ ልጆች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኛቸው አድርገው ተቀብለዋል።

በምርቃቱ ላይ ተማሪዎች በዚህ ስልጠና ሕይወታቸው እንዴት እንደተለወጠ ምስክርነት ሰጥተዋል።በተጨማሪም ወደ ሃገራቸውም ሄደው ወንጌልን በደንብ እንዲሰሩና እንዲያገለግሉ በቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የልጆች አገልግሎት መሪ በሆኑት ፓስተር ማርቆስ በፀሎት ተባርከው ተሸኝተዋል።

መረጃውን ከቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሺፕ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ