የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ ኃላፊዎችና አገልጋዮች በቂርቆስ ክፍለከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ ኃላፊዎችና አገልጋዮች በቂርቆስ ክፍለከተማ ፒኮክ መናፈሻ ግቢ ውስጥ በመገኘት ጉርጓዶችን በመቆፈር በቤተክርስቲያኒቱ የተገዙ ችግኞችን ተክለዋል።
በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት የቤተክርስቲያኒቱ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ገመቹ ደበሎ "ተፈጥሮን እንድንከባከብ እንድንጠብቅና እንድናበጅ ቃሉ ይናገራል" በማለት የገለጹ ሲሆን የቤተክርስቲያናችን መሪዎችና አገልጋዮችም ምዕመኑን በማስተባበር በዚህ ክረምት ችግኞችን በአካባቢያቸው እንዲተክሉ አበረታተዋል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 01 የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገለታ መኸዲ በበኩላቸው "መሠረተ ክርስቶስ ሁልጊዜም ከጎናችን ነች" በማለት በሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በመሳተፏ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በስፍራውም ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት የመምሪያ ኃላፊዎችና የቢሮው ሰራተኞች በፕሮግራሙ ላይ መሳተፋቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።
መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቲቪ