የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ማህበረ ወንጌላውያን ማህበር በመትከል ማንሰራራት በሚል ርዕስ የችግኝ ተከላ አካሄደ።
ሐምሌ 5 ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በየካ ወረዳ 5 በአዲሱ ቤተመንግስት አከባቢ በተካሄደው የመትከል መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጽህፈት ቤተ ኃላፊ የሆኑት መጋቢ ጌተነት ለማ ተገኝተዋል።
ኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ከ396 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ሐምሌ 5፣ 2017 ዓ.ም ኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ለ7ተኛ ዙር በዲፕሎማ፣ በዲግሪ፣ በማስተርስ እና ፕ ኤች ዲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሀፍ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፣ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ የሴሚናሪው ሴኔት፣ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የተመራቂ ቤተስቦች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

የኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዘካሪያስ አዱኛ የእንኳን ደህና መጣችሁና የእንኳን ደስ አለቸው ንግግር አድርገዋል። በንግግራችውም ኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ከተቋቋመ10 አመታትን ያስቆጠረ መሆኑን አንስተው በኢትዮጵያ ከ80 በላይ ካንፓሶሶች እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ወደ 11 የሚጠጉ ካምፓሶች በመክፈት እያስተማረ የሚገኝና እንዲሁም በኦላይን ፕላት ፎርም በተለያዩ መርሀግብሮች እያስተማረ መሆኑን ጠቅሷል።

የሴሚናሪው የቦርድ ፕሬዝዳንት ፓስትር ሰለሞን ባናቲ በበኩላቸው ሴሚናሪው ለቤተክርስቲያን ብቁ የሆኑ አገልጋዮችን እያፈራ እንደሆነ በማንሳት ተመራቂ ተማሪዎች በታማኝነት እና በትጋት እንዲሰሩና ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ምክትል ፕሬዚደንት መጋቢ ሰንበቶ በሼም በበኩላቸው ይህ ታሪካዊ ቀን ነው እግዚአብሔር ስለሰጠን ቀን እናመሰግናለን በማለት፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ እንደ ሀገር የተማረ ሀይል እንደሚያስፈልግ እና ለዚህም ተመራቂዎቹ ትልቅ ሀይል መሆናቸው ተናግረው ማሳሰቢያንም አክለውበታል።

የእለቱ የክብር እንግደ ሆነው የተሰየሙት የአዲስ አበባ ሐይማኖት ተቋም ጉባኤ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ “የእንኳን ደስያላችሁ ንግግር አቅርበዋል። በንግግራቸውም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብዙ መሪዎች፣ ብዙ አገልጋዮች፣ ብዙ አስተማሪዎች፣ ብዙ ሚሽነሪዎች ያስፈልጉናል፤ እናንተ ደግሞ ለዚህ ተሰጥታችሁናልና እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ትጋታችሁ በነገር ሁሉ ይቀጥል ሲሉ በእግዚአብሔር ቃል መክረዋል።

የኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ሴኔትም በትምህርታቸውና በጥናትና ምርምር ሥራ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ እና ሜዳልያ ሽልማት አበርክቷል።
4