የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በቀጣና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን “የተዘጋጀ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሊደርሺፕ ትራንስፎሜሽን ሚኒስትሪ ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያን ለተወጣጡ ወጣት መሪዎች ሴሚናሪ ተካሄደ።

በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን “አንድ የተዘጋጀ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሊደርሺፕ ትራንስፎርሜሽን ሚኒስትሪ ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ለተወጣጡ ወጣት መሪዎች ሴሚናሪ ተካሂዷል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት መጋቢ ዳንኤል ሲሆኑ እንዲሁም በእለቱ ወጣትነት እግዚአብሔር ለሀገር እና ለቤተ ክርስቲያን ለለውጥ እና ለተሃድሶ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረው የወጣትነት ጊዜ በምን አይነት መንገድ መያዝ እንዳለበት አስተምረዋል።

መጋቢ ዳንኤል ወጣትነት በሰዎች እድሜ ውስጥ ወርቃማ የእድሜ ክልል እንደመሆኑ ወጣትነትን በሚገባ ለመጠቀም እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማወቅ መትጋት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ቄስ ትዕግስቱ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 1 ላይ ከሚገኘው ክፍል ላይ በመነሳት ወጣቶች እንዴት ራሳቸውን ከሀጥያት ማራቅ እንዳለባቸው አስተምረዋል።

በከሰዓቱ ፕሮግራምም ላይ ወንድም ለማ ደገፋ ጥሪ ፣ ብቃት ፣ ስብዕና እና ተግባራት በተሰኙ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ትምርህትን ሰጥተዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቃልኪዳን እንዳለ
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የወንጌል መስካሪዎች የአንድነት ፕሮግራም ተካሄደ።

ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም በሴሚሲ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው የወንጌላውያን እና የወንጌል መስካሪ አገልጋዮች የአንድነት ፕሮግራም ላይ 118 አገልጋዮች ተገኝተዋል። በዘማሪ አላምረው ኢያሱ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኳል።

በመቀጠል በክልሉ የወጣቶች ቤተሰብ አገልግሎት ፣ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ሃላፊ በሆኑት በመጋቢ ኤልያስ አየለ "መቼ እንደ ሐዋርያቶችሁ" በሚል ርዕስ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አቅርበዋል።

የፕሮግራሙ አላማ አመቱን ሙሉ ወንጌልን ሲሰብኩ የቆዩትን አገልጋዮች ጌታ ስለረዳቸው ለማመስገን እና ለማበረታታት መሆኑን ታውቋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
3
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለሲኖዶሶች የመንፈሳዊ መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ።


የኢ/ወ/ቤ/መ/ኢ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለመማር ማስተማር ሂደት እና ለአገልጋዮች የሚረዱ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤጊ ግዳሚ ሲኖዶስ (ቤጊ): ለቦረናና አካባቢው ሲኖዶስ (ያቤሎ): ለአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ (አዶላ ወዩ) በድጋፍ መልክ አበርክቷል። መጽሐፍቶቹም በየሲኖዶሶቹ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት እና ምዕመናን አገልግሎት የሚውሉ መሆኑ ተገልጿል።

የመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያኒቱ ድጋፍ ያደረጉትን ተቋማትን ማለትም ራፊኪ ፋውንዴሽን (Rafiki Foundation) ፣ ሉተራን ሄሪቴጅ(Lutheran Heritage Foundation) እና ሌሎችንም በማመስገን ፣ መጽሐፍቶቹን ለቤተክርስቲያኒቱ ሴሚናሪዎች ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች ፣ እና ማ/ምዕመናን ጥቅም እንደሚውል እና ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን ድጋፍ የማድረጉ ስራ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ