የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.47K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የጽዮን ከተማ ሰራዊት ቤተ ክርስቲያን ለ30 ቀናት ለማካሄድ ያቀደቸው የማህበራዊ ሚዳያ የቀጥታ ስርጭት የወንጌል ስርጭት ፕሮግራም መክፈቻ ፕሮራግራም በቤተ ክርስቲያኒቱ አዳራሽ ነሐሴ 1 ቀን በይፋ ተጀመሯል፡፡

ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ዩቱዩብ፣ ኢንስታግራም ፣ ዋትሳፕ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የሚደረገው ይሄ የወንጌል ስርጭት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ለመድረስ ያቀደ ሲሆን ብዙዎችንም በወንጌል እንደሚደርስ ይጠበቃል።
15👍2
በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ያሳስበናል! ሲሉ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ መግለጫ ሰጡ
በቅርቡ በየመን ባህር ላይ ህይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ከገለጹ በኋላ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡ በመቀጠል በደቡብ አፍሪካ ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ የሀገሪቱ ዜጎች እያደረሱ ያሉትን በደል እናወግዛለን ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኖች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሀፊ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ጸሀፊው በጽህፈት ቤታቸው ከካውንስሉ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ በተለይ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ በካውንስሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በኩል የላኩትን ብሶት ተንተርሰው እንደተናገሩት፡- ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካ ነጻነት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረጓ ዜጎቿ ተከብረው መኖር ሲገባቸው በተቃራኒው እየደረሰባቸው ያለው በደል ከሞራልም ከህግም አኳያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
አክለውም ይህንን አቤቱታቸውን በደብዳቤ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት እና በደቡብ አፍሪካ ለኢትዮጵያ ኤንባሲ፣ እዚህ ሀገር ውስጥም ለውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለማቅረብ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
ሙሉ ቃለ ምልልሱን በካውንስሉ ድምጽ ላይ ይከታተሉ፡፡
ተስፋዬ ካሳሁን
ለኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
7👍2
ያህዌ ያሪስ የወንጌል ዓለም ዓቀፍ ቤተ ክርስቲያን "ልባም ሴቶች" በሚል ከመላው የኢትዮጵያ ክልል ከተወጣጡ ሴቶች ጋር የጸሎትና የአንድነት ጊዜ አካሄደች።


‎ ነሀሴ 3/2017 ዓ.ም በያህዌ ያሪስ የወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን "ልባም ሴቶች" በሚል መሪ ቃል ከመላው የኢትዮጵያ ክልል ከተወጣጡ ሴቶች ጋር ስለ ሀገር ስለ አብያተክርስቲያናት፣ስለ አገልጋዮች እንዲሁም ለባለ ስልጣናት ጸሎት የተደረገ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የአንድነትና የጸሎት ጊዜ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ ኢየሱስ በጉድና ቱምሳ ሁለንተናዊ ማሰልጠኛ ተካሂዷል።

‎ያህዌ ያሪስ የወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን መስራችና ባለራዕይ ነቢይት አስቴር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ይህ በቤተክርስቲያኒቱ የመጀመሪያ ፕሮግራም መሆኑን አንስተው ልባም ሴት በቤተሰብ በቤተክርስቲያን በሀገር የታወጀውን ክፉ አዋጅ የምትሽር መሆኗን ተናግረዋል። ልባም ሴቶች ለሀገር ጉዳይ በተለይም ለሰላም አጥብቆ እንዲጸልዩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎በዚህም መርሐግብር ላይ ዘማሪት መክሊት ማሞ በዝማሬ ያገለገለች ሲሆን የአግዚአብሔርን ቃል ነቢያት መሳይ ታደሰ አካፍለዋል።

‎ያህዌ ያሪስ የወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ቤተክርስቲያንን በመትከል ወንጌልን ለሰው ልጆች ሁሉ እየደረሰች የምትገኝ ቤተክርስቲያን መሆኗ በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል ።

‎ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
👍2
ሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ከፎከስ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄደ።

ሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ከፎከስ ሚኒስትሪ ጋር በመተባበር ዛሬ ነሀሴ 3 2017 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂዷል።

በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የሄድዌይ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ፕሬዚደንት ሪቨረንድ ታሪኩ ገብሬ እንዲሁም የፎከስ ሚኒስትሪ ናሽናል ዳይሬክተር የሆኑት ሚልኪያስ ኢትቻ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር የተገኙ ሲሆን በዛሬው ቀን ሃምሳ ተማሪ ለሃምሳ ቀን የሚል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አስተባብረው ችግኞችን ተክለዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ተስፋኢየሱስ ፍቃዱ