ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስቸለውን ስምምነት ተፈራረመ።
መሰረቱን በናይሮቢ ኬንያ ያደረገው ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናል በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሁለንተናዊ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም ከአጸደ ሕጻናት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ተማሪዎችን ለማስተማር እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።
እናም በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በካውንስሉ ጽህፈት ቤት ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ላይም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን በመወከል የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሓፊ የሆኑት ቄስ ደረጄ ጀምበሩ ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናልን በመወከል ደግሞ የአገልግሎቱ መስራች አባል እና ስራ አስኪያጅ ሜሪ ዋቹካ ካማሁ ፊርማቸውን አኑረዋል።
በቆሬ አከባቢ ትምህርት ቤቶችን ለመጀመር ያቀደው አገልግሎቱ የሚገነባቸው ትምህርት ቤቶች ጥራት ካለው የትምህርት አሰጣጥ ባለፈ የምገባ እና የሕክምና ክትትል አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።
ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ ለመስራት ያቀዳቸው ስራዎች በተለያዩ የሀገራችን ክፍል ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤8👍5
የጽዮን ከተማ ሰራዊት ቤተ ክርስቲያን ለ30 ቀናት ለማካሄድ ያቀደቸው የማህበራዊ ሚዳያ የቀጥታ ስርጭት የወንጌል ስርጭት ፕሮግራም መክፈቻ ፕሮራግራም በቤተ ክርስቲያኒቱ አዳራሽ ነሐሴ 1 ቀን በይፋ ተጀመሯል፡፡
ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ዩቱዩብ፣ ኢንስታግራም ፣ ዋትሳፕ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የሚደረገው ይሄ የወንጌል ስርጭት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ለመድረስ ያቀደ ሲሆን ብዙዎችንም በወንጌል እንደሚደርስ ይጠበቃል።

❤15👍2
በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ያሳስበናል! ሲሉ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ መግለጫ ሰጡ
በቅርቡ በየመን ባህር ላይ ህይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ከገለጹ በኋላ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡ በመቀጠል በደቡብ አፍሪካ ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ የሀገሪቱ ዜጎች እያደረሱ ያሉትን በደል እናወግዛለን ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኖች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሀፊ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ጸሀፊው በጽህፈት ቤታቸው ከካውንስሉ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ በተለይ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን፣ በካውንስሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በኩል የላኩትን ብሶት ተንተርሰው እንደተናገሩት፡- ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካ ነጻነት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረጓ ዜጎቿ ተከብረው መኖር ሲገባቸው በተቃራኒው እየደረሰባቸው ያለው በደል ከሞራልም ከህግም አኳያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
አክለውም ይህንን አቤቱታቸውን በደብዳቤ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት እና በደቡብ አፍሪካ ለኢትዮጵያ ኤንባሲ፣ እዚህ ሀገር ውስጥም ለውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለማቅረብ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
ሙሉ ቃለ ምልልሱን በካውንስሉ ድምጽ ላይ ይከታተሉ፡፡
ተስፋዬ ካሳሁን
ለኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን

❤8👍2