የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.41K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አማኑኤል ብርሃንና ህይወት ቤ/ክ ከተለያዩ አጥቢያዎች ለተወጣጡ አገልጋዮች ስልጠና ሰጠች።

ከተመሰረተች 26 ዓመታትን ያስቆጠረችው ቤተክርስቲያንኗ ባለፉት 10 ቀናትም በአራቱ ቀጠናዎቿ ማለትም በዶኒ ፣በአለምጤና ፣ በአርቤጎና እና በሻሸመኔ ቀጠና ዙሪያ ላሉ የአጥቢያ አገልጋዮች ስልጠናውን ስትሰጥ ቆይታለች።

በአሁኑ ሰዓትም የኢትዮጵያ አማኑኤል ብርሃንና ህይወት ቤ/ክ በአራቱም አቅጣጫ ሰባት ቀጠናዎችና 48 አጥቢያዎች እንዳሉዋት ተገልጿል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይም ሐምሌ 25 እና 26 በሻሸመኔ አጥቢያ የወንጌል ስርጭት ጊዜ የተደረገ ሲሆን በተናጠል በተደረገ የወንጌል ስርጭትም 408 ሰዎች ወንጌልን የሰሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል 12ቱ ጌታን ሲቀበሉ 14ቱ ደግሞ በንሰሀ መመለሳቸው ተነግሯል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም በጀማ ስብከት 2500 የሚጠጉ የከተማው ነዋሪዎች ወንጌልን ሲሰሙ 17 አዳዲስ ሰዎች ደግሞ የውሀ ጥምቀት መውሰዳቸውንም ከቤተክርስቲያኗ የደረሰን መረጃ ያሳያል ።

መረጃውን ከማህበራዊ ትስስር አገኘነው

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ" ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ ከደቡብ አፍሪካ ።

የደቡብ አፍሪካ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አስቸኳይ የጾም እና ጸሎት ጥሪ አቅርቧል።

የወንጌል አብሳሪዎች አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በጁሃንስበርግ መሪ እና የካውንስሉ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ እንደገለጹት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያዩ ቡድኖች ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጸው ነገሮች እንዲስተካከሉ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ ብለዋል።

ዶ/ር ብርሃኑ በመልዕክታቸው በአሁኑ ሰዓት ዱዱላ የተባለ ቡድን ስደተኞችን የማይገቡ ዶክመንቶችን በመጠየቅ እያሰቸገረ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም እዛው የተወለዱ እና ያደጉ ልጆች ሲማሩም ይሁን ትምህርት ተምረውም ከጨረሱ በኋላ ስራ ለማግኘት በመቸገር ከፍተኛ ስንለቦናዊ ጫና እያደረባቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

እግዚአብሔርን አምነን ፊታችንን ወደ እርሱ በማድረግ ያለውን ችግር በእርሱ ፊት እንቅረብ በማለት በፈረንጆቹ ኦገስት 5-7 / 2025 ወይም ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም ድረስ በጾም እና ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ጸሎት እንዲቀርብ ጥሪ አቅርበዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
🔥2