የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ፕሮጄክት ዜሮ የተሰኘ የወንጌል ተልእኮ እቅድ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በይፋ ተከፈተ
ኢትዮጵያን እስከ መጪው 2030 ድረስ በወንጌል ያልተደረሱ ህዝቦችን በሙሉ ለመድረስ እቅዱን ከመላው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት በመጡ መሪዎች በተገኙበት በይፋ አስጀምሯል፡፡
በእለቱ በቀረበው መረጃ መሰረት በአለም ላይ 3.43 ቢሊዮን በኢትዮጵያ ደግሞ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በላይ ጨርሶ ወንጌል ያልሰማ ህዝብ እንዳለ ተነግሯል፡፡ በመሆኑም ይህንን ህዝብ ሚሽነሪዎችን በማሰማራት እስከ መጪው 2030 ድረስ ማለትም በአምስት አመታት ጊዜ በወንጌል እንዲደረሱ ለማድረግ ዝርዝር እቅዱን አቅርቧል፡፡
ፕሮጄክት ዜሮ የሚለውን ስያሜ ለምን እንደተጠቀሙ በተሰጠው ማብራሪያ በተጠቀሰው አመት ወንጌል ያልሰማ ሰው ቁጥር 0 እንዲሆን አስበን ተነስተናል በማለት የፕሮጄክቱ ዋና አስተባባሪ ፓስተር ሽመልስ ደጀኔ ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡
በጉባኤው መክፈቻበዝማሬ ወንድም ረታ ጳውሎስ ዝማሬ ያገለገለ ሲሆን፣ በመቀጠል በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ ማእረግ የመንፈሳዊ እና የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ፓስተር ይልማ ዋቄ የእግዚአብሔርን ቃል በወንጌል ተልእኮ ላይ አተኩረው አቅርበዋል፡፡
በመቀጠል የሆርን ኦፍ አፍሪካ ሚሽነሪ ተቋም እህት ወለላ እቅዱ ሁለት ምእራፍ እንዳለው አስረድተው በሚቀጥሉት አምስት ወራት ከጉባኤው በሚቋቋም የቴክኒክ ቡድን ጥናት እና የሚሽነሪዎችን ስልጠና እንደሚደረግ ጠቅሰው ጥናቱ የሚያመጣውን ውጤት ተከትሎ በሁለተኛው ምእራፍ ደግሞ ጥናቱ በሚያመላክታቸው ቦታዎች የሚገኙ ቤተ እምነቶችን በመጠቀም የወንጌል ተልእኮውን በተግባር ለማዋል እንደታቀደ ተናግረዋል፡፡
ወንድም በቀለ ቀጥለው እንደተናገሩት በተለይ በዚህ ስራ ላይ ሰፊ አቅሙን እየተጠቀመ ያለውን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ሚሽነሪ ተቋምን አድናቆት ሰጥተው በወንጌል ያልተደረሱትን አስቦና አቅዶ መስራት ለቤተክርስቲያን ዋነኛ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከእቅዱ በኋላ ተሳታፊዎቹ በቡድን በመሆን ጥልቅ ውይይት በማድረግ በየግላቸው የደረሱበትን ድምዳሜ እንደ ግብአት ለእቅዱ አስረክበዋል፡፡

ለኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
ተስፋዬ ካሳሁን
ከኢንተር ሌግዠሪ አዲስ
5
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ሴቶች ፤ ሕጻናት እና መሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በቅንጅት በመስራቱ እውቅና ተሰጠው።

የአ.አ.ሴ.ሕ.ማ.ጉ.ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በቅንጅት ለመስራት ያቀዳቸው ተግባራት አፈፃፀምና እና በ2018 በጀት ዓመት በቅንጅት ለመስራት ባቀዳቸው ተግባራት ላይ በቅንጅት ከሚሰሩት ሴክተሮች ጋር የግምገማ ውይይት አድርጓል፡፡

የቅንጅት አሰራር እቅድ አፈፃፀም ግምገማውን የመሩት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በበጀት ዓመቱ አቅደን ላሳካናቸው ዘርፍ ተሻጋሪ ተግባራት በቅንጅት አብረውን የሰሩ ሴክተሮች የጎላ ሚና ተወጥተዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም ቢሮው በአብዛኛው ስራዎቹ ዘርፍ ተሻጋሪ በመሆናቸው ከሚመለከታቸው ሴክተር ተቋማት ጋር በቅንጅት አቅዶ መስራትን በልዩ ትኩረት እየሰራበት እንደሚገኝና አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ተናግረዋል፡፡

በቅንጅታዊ አሰራር የእቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ እቅድ ያቀረቡት የቢሮው የስታንዳርዳይዘሽን ዝግጅት እና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሲሳይ በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራት አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰው፤ በቀጣይ በሁሉም ተግባራት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በርብርብ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የአዲስ አበባ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤን በመወከል የሴቶች እና ወጣቶች መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ራምላ ከድር የተሳተፉ ሲሆን የሴክተር ተቋማት አመራሮችና ተወካዮች ቢሮው ለቅንጅትዊ አሰራር የሰጠው ትኩረት በጋራ የሚሰሩ ስራዎች በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀሙ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልፀው፤ ለ2018 በጀት ዓመት የታቀዱ ተግባራት ለማሳካት በተሻለ ርብርብ እና መናበብ እንደሚሰሩ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡

በግምገማዊ ውይይቱ ሴክተሮች በ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም በነበራቸው ተሳትፎና አፈፃፀም ልክ በጣም ከፍተኛ፣ ከፍተኛና አጥጋቢ በሚል የእውቅናና ምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡

መረጃው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
👍2