የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.54K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የመጋቢ ዘማሪ አስፋው መለሰ "አንተን አልጣ እንጂ" 6ኛ የመዝሙር አልበም ተመረቀ።

ዘለግ ላሉ ጊዜያት በዝማሬዎቹ የሚታወቀው መጋቢ አስፋው መለሰ 6ኛውን የመዝሙር አልበም በይፋ አስመርቋል።

በማቴዎስ ወንጌል 6፥31 ላይ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀው የአልበሙ የምርቃትና የመዝሙር ድግስ ስነ ስርዓትም በልደታ ጉባኤ እግዚአብሄር ቤተክርስትያን በደማቅ ሁኔታ ተካሄዷል።

"አንተን አልጣ እንጂ" የተሰኘውን ሙሉ አልበም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት አመት እንደፈጀ የተገለጸ ሲሆን አልበሙ 11 መዝሙሮችን በውስጡ መያዙም ተነግሯል።

ዘማሪ አስፋው መለሰ ቀደም ሲልም ብዙ ዘመን ራራህልኝ ፣ በጅምር አይቀርም ፣ ትናንት ዛሬ አይደለም እና መሰል የአልበም ስራዎችንም ለወንጌል አማኙ ተደራሽ አድርጓል።

በፕሮግራም የቤተክርስቲያኗን አገልጋዩች ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የወንጌላውያን አማኞችም መታደማቸውን በማህበራዊ ሚድያ ላይ ይፋ የተደረጉ መረጃዎች አመላክተዋል።
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
5
የዘማሪ አዲሱ ዋዪማ 6ኛ የመዝሙር አልበም ለምርቃት በቃ።

በተለያዩ ጊዜያት በዝማሬዎቹ የሚታወቀው ዘማሪ አዲሱ ዋዪማ በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ 6ኛውን የመዝሙር አልበም በይፋ አስመርቋል።

የዘማሪ አዲሱ ዋዪማ የአፋን ኦሮሞ አልበም “በራ በራኮ” የሚሰኝ ሲሆን አልበሙ 13 መዝሙሮችን በውስጡ መያዙም ተነግሯል።

ዘማሪ አዲሱ ዋዪማ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከ20 አመታት በላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በታማኝነት በማገልገሉ የሚታወቅ ሲሆን በፕሮግራሙም የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ፕረዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ጨምሮ የቤተክርስቲያን አገልጋዩች እና ጥሪ የተደረገላቸው የወንጌላውያን አማኞችም ታድመዋል።

ዘማሪ አዲሱ ዋዪማ ቀደም ሲልም “ኢኝ ዳሬ ጎትኒ፣ ኡቱ ባድኔ ካናን ዱራ፣ አታሚን ጋላኒ ና ኢቲሳ”በተሰኙ የመዝሙር አልበሞችን ለወንጌል አማኙ ተደራሽ አድርጓል።

ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
7
የፉላኒ ታጣቂዎች በባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ባደረሱት ጥቃት የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢ እና አባል መገደላቸው ተገለጸ።
በባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን ሰኞ ከሰዓት በተደረገ የአምልኮ መርሃግብር ላይ ፤ በአባላት ላይ በተከፈተ ተኩስ አማካኝነት የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢ እና አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል ሕይወታቸው አልፏል።

ይህም ጥቃት የደረሰው በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ፤ ያሪቦሪ መንደር በቤጌ ባብቲስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው።

በቦታው የነበሩ ምስክሮች 20 የፉላኒ ታጣቂዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ የተናገሩ ሲሆን መጋቢውን እና አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባል ከመግደላቸውም ባለፈ አንዲት ሴትን አግተው መውሰዳቸውን አሳውቀዋል።

በናይጄሪያ ማዕከላዊ ክፍል ላይ በያዝነው ዓመት ከፍተኛ የሆነ የክርስቲያኖች ግድያ እየተሰተዋለ የሚገኝ ሲሆን በባለፈው ወር ብቻ የፉላኒ ታጣቂዎች 20 ክርስቲያኖች ገድለዋል።

በባለፉት 2 ወራት በፉላኒ ታጣቂዎች አማካኝነት ሕይወታቸን ያጡ ክርስቲያኖች ቁጥር ከ80 አልፏል።
የአከባቢው ባለስልጣን የሆኑት አማላዉ ሳሙኤል የተፈጠረውን ጥቃት ሰብዓዊነት የጎደለው ነው በማለት ያወገዙት ሲሆን ጥቃት አድራሾቹ በወድቅት እየመጡ ንጹሐን መግደላቸውን እና ጣሪያ ሸንቁሮ እስከመግባት ድረስ የሚያደርሱት ጥቃት ገደብ እንዳጣለት ተናግረዋል።


ናይጄሪያ እንደ ኦፕን ዶርስ 2025 ወርልድ ዋች ሊስት ደረጃ መሰረት በዓለማችን ክርስቲያኖች በመግደል አንደኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን በዓመቱ ውስጥ በዓለማችን ክርስቶስን በመከተላቸው ምክንያት ከተገደሉት 4,476 ሰዎች መካከል 3,100 የሚሆኑት የተገደሉት በናይጄርያ ነው።
የግድያውም መንስኤ ጽንፈኛ ሀይማኖታዊ አመለካከት እና ክርስቲያኖችን በማፈናቀል መሬታቸውን ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ይታመናል።
መረጃውን ከፕሪሚየር ክርስቲያን ኒውስ አገኘነው።

አማኑኤል ዴቢሶ ፤ ኢቫንጀሊካል ቲቪ