የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
አባካኙ ልጅ የተሰኘው ሙዚቃዊ ፊልም በሸራተን አዲስ ለእይታ ቀረበ።
በዘማሪ ቤተልሔም ተዘራ የተዘጋጀው እና የተለያዩ ዘማሪዎችን ያካተተው ሙዚቃዊ ድራማ በሸራተን አዲስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ በቅቷል።
መርሃ ግብሩን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑት ቄስ ደረጄ ጀምበሩ በጸሎት እና በንግግር የከፈቱ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜዎች በወንጌል አማኞች ዘንድ በአመራርነት ያገለገሉ አገልጋዮች እንዲሁም ዘማሪዎች በስፍራው ተገኝተው ነበር።

ዘማሪት ሕሊና ዳዊት፣ መስፍን ጉቱ ፣ መጋቢ እንዳለ ወልደጊዮርጊስ፣ ዘማሪ ገዛኸኝ ሙሴ እና ሌሎችም ዘማሪዎች በስፍራ በመገኘት ጉባኤው በዝማሬ መርተዋል።
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ሙዚቀኞች እና ዘማሪዎች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አገልጋይ ረታ ጳውሎስም የዘማሪት ቤተልሔም ተዘራን የዝማሬ አገልግሎት እና አባካኙ ልጅ የተሰኘውን ሙዚቃዊ ድራማ አስመልክቶ ሙያዊ ዳሰሳ አቅርበዋል።
ባቀረቡትም ሙያዊ ዳሰሳ ዘማሪት ቤተ ልሔም ተዘራ በዜማ ድርሰት፣ በመዝሙር ጭብጥ እና በስነ ጽሁፋዊ ውበት የተዋጣላቸውን ዝማሬዎች እንዳደረሰች የተናገሩ ሲሆን ለእያንዳንዱ ዝማሬዎች የከፈለችውን ዋጋ አድንቀዋል።
የዘማሪት ቤተልሔም ተዘራን አጠቃላይ የዝማሬ ጉዞን አስመልክቶም አጠር ያለ ዶክመንተሪ ለእይታ ቀርቧል።
ከዚህም በተጨማሪ በአገልጋይ መንግስተ አብ የሚመራው የሊቪንግ ዊትነስ አገልግሎት ራዕይ የማካፈል መርሃ ግብር ተካሄዷል።

የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈሉት ቄስ ትዕግስቱ ሲሆኑ 2ኛ ሳሙኤል 14:14 ላይ የሚገኘውን ቃል በማንሳት እግዚአብሔር በሰዎች መጥፋት ደስተኛ እንዳልነ እና በምክሩ እንደሚያስብ የተናገሩ ሲሆን እኛም ለሰዎች እንደዚህ አይነት ልብ ሊኖረን እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመልካም ስራችን ለምድራችን ብርሃን እና ጨው መሆን ይጠበቅብናል በማለተ የተናገሩት አገልጋይ መንግስተዓብ እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚገባንን ነገር ከማድረግ በመቆጠባችን አማካኝነት በብዙ ወደ ኋላ ቀርተናል በማለት የተናገሩ ሲሆን ሁሉም አማኝ በጋራ ርብርብ በማድረግ በሃገራችን ለሚገኙ ደሆች እና አቅመ ደካሞች ማድረግ የሚቻለውን ነገር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
በሀገራችን እንዲሁም በወንጌል አማኞች ዘንድ በትልልቅ የአመራር ስፍራዎች ላይ በማገልግል ላደረጉት አስተዋጽዖ የምናውቃቸው ጋሽ ሽፈራው ወልደ ሚካኤል የሙሴን ታሪክ በማንሳት ከሚያለቅስ ሕጻን መሪ እናውጣ የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አባካኙ ልጅ የተሰኘው ሙዚቃዊ ፊልምም ለእይታ ቀርቧል።
በፕሮግራሙ ላይም የሊቪንግ ዊትነስ አገልግሎትን ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን ከዛም በኋላ በጋራ በተደረገ አምልኮ ተጠናቋል።
8👍1
የኢትዮጵያ ማህበረ ወንጌላውያን ማህበር በመትከል ማንሰራራት በሚል ርዕስ የችግኝ ተከላ አካሄደ።
ሐምሌ 5 ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በየካ ወረዳ 5 በአዲሱ ቤተመንግስት አከባቢ በተካሄደው የመትከል መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጽህፈት ቤተ ኃላፊ የሆኑት መጋቢ ጌተነት ለማ ተገኝተዋል።