የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
አስቸኳይ መልዕክት ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መስራች አባል የሆነችው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መዋቅር ስር በጅማ ዞን ሰጠማ ወረዳ ጋቲራ ከተማ የምትገኘው ማህበረ ምዕመናን ላይ ለእምነቱ ጭፍን ጥላቻ ባላቸው አካላት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ።
መንግስት እነዚህን ግለሰቦች ለህግ በማቅረብ አስፈላጊውን ቅጣት በመስጠት ያፈረሱትን የጸሎት ቤት በአስገዳጅነት እንዲሰሩ በማድረግ እና ጭፍን ሐይማኖታዊ ጥላቻቸውን በምዕመኖቻችን ሕይወት ላይ ተግባራዊ ባደረጉ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ ወስዶ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ።
🙏15👍93
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አሜሪካን አገር ከሚገኘው ወርድ ኦፍ ላይፍ አሴምብሊስ ኦፍ ጋድ ቤተክርስቲያ ጋር በመተባበር 213 የቤተክርስቲያን መሪዎች ለውጣዊ አመራር (transformational leadership) በሚል ርእስ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው:: ስልጠናው የቤተክርስትያን መሪዎች እግዚአብሔር የሰጣቸውን የመሪነት ፀጋ በእውቀት በታገዘ ማንነት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስታጥቅ ሲሆን ለሁለት ቀናት መጋቢት 10-11 2017 ዓ.ም. በሳሮ ማሪያ ሆቴል የሚሰጥ ይሆናል::
👍206🙏1