EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
133K subscribers
43.2K photos
483 videos
80 files
13.7K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ክንዱ የማይታጠፈው የጀግኖች አምባ!

እስቲ ለአፍታ ቆም ብለን እናስብ፤ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የጸጥታና የሉዓላዊነት ምሽግ ምን ያህል ጠንካራ ነው? የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዛሬ የተረከበውን ሀገራዊ አደራ ታሪክን በሚቀይር የልህቀት ከፍታ ላይ አድርሶታል::

እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት እና በጽኑ ኩራት የሚያስደምመው ይህ ተቋም፣ በጥልቅ ሪፎርም ዳግም የተወለደ የሉዓላዊነታችን ሕያው ምሽግ ነው
25👍5👏3🔥2
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የ6ኛ 5 ዓመት 3ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በሁለት ቀናት ቆይታው ‎የክልሉን መንግሥት የአስፈጻሚ አካላት፤ የምክር ቤት ጽ/ቤት፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ አፈጻጸም ይገመግማል::


‎በተጨማሪም የክልሉን የ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ በጀትን ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል
5👍4
የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ሐምሌ 18፣ 2018 ዓ.ም

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
2
ከድንበር ባሻገር የተዘረጋ የሰላም ድልድይ፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር

ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ የታሪክ ገጽ ላይ አዲስ የብርሃን ጭረት እየፈጠረ ያለ ታላቅ ሕዝባዊ ክስተት ነው::

ይህ ሒደት የቀደሙ አለመግባባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በሠለጠነ መንገድ ለመፍታት የተወጠነ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ልጆችን በሀገራዊ ፍቅር ያገናኘ ታላቅ ድልድይ ነው
👏112
ኤርትራ ለግብጽ ውለታ ለመክፈል የከፋፈለቻቸው አፋሮች ስጋት

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ ግብጽ የውጭ ፖሊሲዋን ዋነኛ ማዕከል ያደረገችው ኢትዮጵያን የባሕር በር አልባ ማድረግ እና የዓባይ ወንዝን በበላይነት መቆጣጠር ላይ ነው::

ለዚህ የረዥም ጊዜ የጥፋት ዓላማዋም ኤርትራን እንደ ዋነኛ መሣሪያ ስትጠቀምባት ኖራለች
9😢1
“ኢትዮጵያ ፈተና ቢበዛባትም ፈተናን በመሰባበር የማለፍ ተፈጥሮ ያላት ሀገር ናት” - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ሆለታ በሚገኘው የአካዳሚው ግቢ ያሠለጠናቸውን 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ይገኛል::

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ “ኢትዮጵያ ፈተና ቢበዛባትም ፈተናን በመሰባበር የማለፍ ተፈጥሮ ያላት ሀገር ናት” ብለዋል
23👏5🙏1🤗1
በምርጫ ማግስት ጠንካራ መንግሥት ብለን የጀመርነው ጉዞ ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል:- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው::

በምክር ቤቱ በጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል
👍63🙏2
ኢትዮጵያውያን የወደፊቱን ዕጣ ፈንታቸውን እና መዳረሻቸውን በራሳቸው ጥበብ እና ዕውቀት ይቀርጻሉ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆኑትን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርትአፕ ሠልጣኞች አስመርቃለች::

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አማካኝነት የሠለጠኑትን የሀገራችንን የመጀመሪያዎቹን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ስታርትአፕ ሠልጣኞች አስመርቀዋል
11👏2
“ማሸነፍ ቋንቋው የሆነ፤ የአፍሪካ ኩራት፤ የኢትዮጵያ መከታ፤ ለነጻነት የደም ዋጋ የሚከፍል ማነው? ተብሎ ቢጠየቅ፣ ዓለም ሁሉ ተስማምቶ ‘የኢትዮጵያ ወታደር ነው’ ማለቱ አይቀርም”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
14👍4👏2🤣2
በምክክር ሂደቱ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በስፋት እያንጸባረቁ ነው - ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

እየተካሄደ ያለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት እጅግ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስታወቁ፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ ስለ ጉባኤው ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፣ በቅድሚያ ስለ አጠቃላይ የምክክር ሂደቱ እና ሊኖሩ ስለሚገባቸው የምክክር ሥነ-ምግባሮች ላይ ግልጽ አቅጣጫ ከተያዘ በኋላ በአሁን ሰዓት በቀጥታ ወደ ዋናው የምክክር መድረክ ተገብቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ምክክሩ በየቡድኑ በስፋት እየተካሄደ እንደሚገኝ የገለጹት ፕሮፌሰር መስፍን፣ በአሥር አባላት በተዋቀሩ ቡድኖች ተካሂዶ የተጠናቀረው ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሀምሳ አባላት ላሏቸው ቡድኖች መቅረብ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
እነዚህ የሀምሳ አባላት ስብስቦችም የቀረበላቸውን ሀሳብ በደንብ ካብላሉ በኋላ ለ250ዎቹ ቡድኖች የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ይህ የምክክር ሰንሰለታዊ ሂደትም በተመሳሳይ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡
በጉባኤው ጅማሮ ላይ ተሳታፊዎች ምንም ዓይነት ሀሳብ ሳይደብቁ በግልጽ እያወጡ እና በስፋት እየተነጋገሩበት መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ በዚህም አጠቃላይ የምክክሩ ሂደት በሚፈለገው መንገድ እና በጥሩ ሁኔታ እየተጓዘ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
አክለውም በዚህ መስተጋብር ውስጥ ውይይቱ በተቀመጠለት አቅጣጫ እንዲጓዝ በማድረግ ረገድ የአመካካሪዎች ሚና እጅግ የጎላ እና ትልቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በለሚ ታደሰ
15
በምክክር መድረኩ የተለያዩ አካላት ፍትሐዊ ውክልና አግኝተዋል - የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ የምክክሩ ሒደት ላይ የተሳታፊዎች አደረጃጀት ፍትሐዊነትን የተላበሰ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አረጋግጠዋል::

በቡድን ድልድሉ ወቅት የተፈጠሩ ክፍተቶችን በቴክኖሎጂ በማረም በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የተመጣጠነ ውክልና እንዲኖራቸው ተደርጓል
14🔥5
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 በጀት 85 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ ፀደቀ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛው ዙር 5ኛ የሥራ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤው የክልሉ የ2019 በጀት 85 ቢሊዮን 774 ሚሊዮን 12 ሺህ 25 ብር ሆኖ እንዲፀድቅ በሙሉ ድምፅ ወስኗል::

የበጀት ድልድልም ለክልል ማዕከል መሥሪያ ቤቶች መደበኛ እና የካፒታል - 7ቢሊዮን 527ሚሊዮን 155 ሺህ 180 ብር፣ ለዞኖች እና ለከተማ አስተዳደሮች ጥቅል በጀት -70 ቢሊዮን 592 ሚሊዮን 656 ሺህ 845 ብር፣ ለክልላዊ ፕሮግራም - 6 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር፣ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ - 984 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር፣ ለመጠባበቂያ - 170 ሚሊዮን ብር፤ ጠቅላላ ድምር - 85 ቢሊዮን 774 ሚሊዮን 12 ሺህ 25 ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል
5
የአረንጓዴ ዐሻራ የተገኙ ስኬቶችን የማስፋት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ

በአረንጓዴ ዐሻራ የተገኙ ስኬቶችን በማስፋት የምግብ ሉዓለዊነትን ለማረጋገጥ እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ለመቀነ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ አስታውቀዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሯ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ በማጃንግ ዞን አስጀምረዋል፡፡

በየዓመቱ እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ በክልሉ የደን ሽፋን እንዲጨምር እንዲሁም የአፈር መሸርሸር አደጋ እንዲቀንስ እና ምርት እና ምርታማነት እንዲሻሻል ማስቻሉን ወ/ሮ አለሚቱ ገልጸዋል፡፡
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ለምግብነት መዋል በመጀመራቸው የማኅበረሰቡ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዲሻሻል አስተዋፅዖ ማበርከቱንም ጠቁመዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬትን ለማስቀጠል በክልሉ ለምግብነት እና ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚውሉ የፍራፍሬ እና የአትክልት ችግኞች በስፋት እየተተከሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
ማኅበረሰቡም ችግኞችን በመትከል እና በመንከባከብ የጀመረውን ተሳትፎ በማጠናከር በአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል ይጠበቅበታል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሯ አሳስበዋል፡፡
የጋምቤላ ክልል እርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ኡሞድ በበኩላቸው በክልሉ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር የተፈጥሮ ሀብቱን በዘላቂነት ማልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

በሚፍታህ አብዱልቃድር
8👍5
“ሀገራዊ ምክክር ፍቱን የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የእኛን እና የመጪውን ትውልድ ዕጣ ፈንታ እና የወደፊት ተስፋ ሙሉ በሙሉ የሚወስን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጭምር ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
6🙏5
ለቀይ ባሕር የተከፈሉ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በቃል ኪዳን ሀገራት አሸናፊነት ሲጠናቀቅና ፋሺስት ጣሊያን ስትሸነፍ የኢትዮጵያ አርበኞችና የእንግሊዝ ጦር ጣሊያንን ከኢትዮጵያ ጠራርገው አስወጡ::

በዚህ ወቅት አፄ ኃይለ ሥላሴ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር በመቀላቀል የሀገራችንን የባሕር በር ለማስመለስ ፈጣን እና ሰፊ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ጀመሩ
👏18👍2😢1
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በበጀት ዓመቱ 89 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርቧል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ለክለሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት ዓመቱ 89 ኩንታል ወርቅ ተመርቶ ወደ ብሔራዊ ባንክ መላኩን ተናግረዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ በዓመቱ 1.6 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር በመሸፈን ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
ለ360 ሺህ 86 ዜጎች የብሔራዊ ድጂታል መታወቂያ የተሰጠ ሲሆን፣ 37 ሺህ 795 ዜጎች የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና መውሰዳቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
ሁለት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ 3 ተጨመማሪ የመሶብ ማዕከላት ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ርዕሰ መስተዳደር አሻድሊ ሃሰን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በማጠናከር ባለፉት ዓመታ የተተከሉትን ጨምሮ በክልሉ ከ450 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል፡፡
በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና፣ በንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በከተማ ልማትና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንድሁም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተሰፋ ሰጪ ሥራዎች መከናወናቸውን ርዕሰ ምተዳደሩ ገልጸዋል፡፡
በጀማል አህመድ
17👍3
ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ከማንኛውም ወገንተኝነት ነጻ እንዲሆን ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው - ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስካሁን ያለውን ሂደት በማስመልከት ዛሬ በሰጠው መግለጫ አጠቃላይ አካሄዱ ውጤታማና አዋጭ መሆኑን አስታውቋል::

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በመግለጫቸው እንዳሉት፣ በምክክር መድረኩ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ የትኛውም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ሃይማኖት በሌላው ላይ ጫና እንዳያሳድር እና ሂደቱ ወደ አንድ ወገን እንዳያዘነብል ፍትሃዊ አሠራር እየተከተልን እንገኛለን ብለዋል
13🤣4😢1
ኢትዮጵያ እንዴት ወደብ-አልባ ሆነች? ሴራ እና የሀገር ክህደት

ኢትዮጵያ እንዴት ወደብ-አልባ ሆነች? ሴራ እና የሀገር ክህደት
ኢትዮጵያ እንዴት ወደብ-አልባ ሆነች? የ1983 ዓ.ም የሥልጣን ሽግግር ኢትዮጵያን ከባሕር በር በማራቅ ሀገርን ለማያቋርጥ የደኅንነት ስጋት ያጋለጠበት ወቅት ነበር::

የኢትዮጵያ ወደብ-አልባ መሆን ድንገተኛ የታሪክ አጋጣሚ ሳይሆን፣ በወቅቱ ሥልጣን በያዙት የሕወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች ሆን ተብሎ የተፈጸመ፣ ሕጋዊ መሠረት የሌለው ውሳኔ ውጤት ነው
👍107🤩1
ኢትዮ ቴሌኮም እና የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ግብርን በቴሌ ብር ለመሰብሰብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮ ቴሌኮም አና የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በባሕርዳር ከተማ ተፈራርመዋል::

ስምምነቱ፣ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ግብርን በቴሌ ብር እንዲሰበስብ የሚያስችለው ነው
12🤣4
ፓን-አፍሪካዊ ኃይል የሆነው የመደመር ትውልድ

ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት በመሆን የፓን-አፍሪካኒዝም እሳቤ ተፈጥሯዊ ጉልበት ሆና ቆይታለች::

አውሮፓውያን አህጉሪቱን ለመቀራመት ሲነሡ፣ ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የቆመች እና ሥልጣኔን ያጣጣመች ዕድሜ ጠገብ ሀገር ናት
👍153
ኢትዮጵያ የምትፈልገው ባሕርን እንጂ ጠላትነትን አይደለም

130 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት፣ በኢኮኖሚ እና በሕዝብ ቁጥር የቀጣናው ግዙፍ የሆነችው ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ በባሕር በር እጦት ብቻ ታንቃ እንድትቀጥል በዙሪያዋ የተዘረጋው ስውር የጂኦ-ፖለቲካ ድር እውነታው ምንድን ነው?
በአሁኑ ወቅት ግብፅ እና ሻዕቢያ ከሌሎች ኃይሎች ጋር በመሆን በአንድ አጀንዳ ላይ ስትራቴጂያዊ ውህደት ፈጥረዋል::

ይኸውም ኢትዮጵያ በምንም ተዓምር ወደ ባሕር እንዳትደርስ ማድረግ የሚል ነው
15👍8🔥3