EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
✔
137K subscribers
38.7K photos
471 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የፌዴራል ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች በብሔራዊ ቤተ - መንግሥት ሙዝየም ያደረጉት ጉብኝት - በምስል
👍13❤1
ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን 1ለ0 አሸነፈ
***************

ዛሬ በተካሄደው 13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን 1ለ0 አሸንፏል።

ለባህርዳር ከተማ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ጄሮም ፊሊፕ በ80ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአሁኑ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እየተጫወቱ ሲሆን የመጀመሪያውን መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜም ያለምንም ግብ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል ።

በላሉ ኢታላ
👍24❤2
መንግሥት የዜጎችን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው - አቶ አደም ፋራህ
***********************

መንግሥት የዜጎችን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ሱፐርቪዥን እና ድጋፍ ሥራዎች የልማት ተደራሽነትን በማስፋት ረገድ የላቀ ሚና እያበረከቱ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በተለያዩ ክልሎች ያከናወኗቸው የመስክ ምልከታዎች የአፈጻጸም ግምገማ የሪፖርት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ በክልሎች ከሪፖርት እና ግምገማ ባሻገር የሱፐርቪዥን እና ግብረ መልስ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ አደም ፋራህ አንስተዋል፡፡

ይህም የመንግሥት ኢኒሼቲቮች እና ፖሊሲዎች አፈጻጸምን በተግባር ለማየት እንዲሁም ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም በክልሎች መካከል የአፈጻጸም ልዩነቶችን በማጥበብ የዜጎች ፍትሃዊ የልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
👍43❤8