EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.7K photos
471 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በቻይናዋ ቲቤት ግዛት ውስጥ በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር 126 ደረሰ
***************

በቻይና በሂማላያ ተራሮች ስር በምትገኘው ቲቤት ግዛት ውስጥ በተከሰተው በዚህ ከባድ የርዕደ መሬት አደጋ ምክንያት በርካቶች አሁንም የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።

በሬክተር ስኬል 6.8 የተለካው የርዕደ መሬት አደጋ በግዛቷ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከተከሰቱት መሰል አደጋዎች እጅግ የከፋው ስለመሆኑ ተገልጿል።

ርዕደ መሬቱ ከቲቤት አልፎም እስከ ጎረቤት ቡትሀን፣ ህንድ እና ናፓል ድረስ ዘልቆ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል ነው የተባለው።

ርዕደ መሬቱ ከተከሰተ በኋላ በፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ ነዋሪዎችን ለማውጣት በቦታው የነበረው ከባድ ቅዝቃዜ ትልቅ ፈተና ደቅኖ ነበር።

በዚህም እስካሁን ቢያንስ 126 ሰዎች መሞታቸው እና 188 ደግሞ መጎዳታቸው ተዘግቧል።

800 ሺህ ሰዎች እንደሚኖሩባት በምትገመተው የቲቤቷ ሺጋሴ ግዛት ቢያንስ 3 ሺህ ቤቶች መውደማቸውን የመጀመሪያ ዙር ቆጠራ አመላክቷል።

ቀሪ የአደጋው ሰለባዎችን ለመታደግ ከ1 ሺህ 800 በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና 1 ሺህ 600 ገደማ ወታደሮች አደጋው ወደተከሰተበት ግዛት ተሰማርተዋል።

መንግሥት ለአደጋው ተጋላጭ የሆኑ 30 ሺህ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ተጎጂዎችን የመታደጉ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን እና የነፍስ አድን ስራው በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
👍194
ማስታወቂያ
****
ሬስ ማይክሮ ፋይናንስ እና ሁድ ሁድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመተባበር የተመቻቸ ብድር
👍151
የነዳጅ ዋጋ በኢትዮጵያ
***********

ግሎባል ፔትሮል ፕራይስ የተባለው ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ አቅራቢ በድረ-ገጹ ኢትዮጵያን ነዳጅ በዝቅተኛ ዋጋ በመሸጥ ከአፍሪካ ሀገራት በ8ኛ ደረጃ፣ ከዓለም በ28ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል።

ድረ-ገጹ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወቅታዊ የነዳጅ ዋጋን እየሰበሰበ የሚያሰፍር እና ከነዳጅ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና ጥናታዊ ጽሑፎችን የሚያሰራጭ ነው። በዚሁ መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የቤንዚን ዋጋ በአማካይ $1.23 (የአሜሪካ ዶላር) እንደሆነ ጠቅሶ፤ የቤንዚን ዋጋ በኢኮኖሚ በአደጉ ሀገራት ዝቅተኛ እንዲሆን የሚጠበቅ ቢሆንም፣ በተቃራኒው ግን በዝቅተኛ ዋጋ የሚሸጡ ታዳጊ ሀገራት ናቸው ይለናል።

በድረ-ገጹ አሁን ባለው ወቅታዊ የነዳጅ ዋጋ ከኢትዮጵያ ቀድመው የሰፈሩት በአብዛኛው የእስያ ነዳጅ አምራች ሀገራት ናቸው። በዚህ መሰረት በዓለም ዝቀተኛ ዋጋ የቆረጠችው ኢራን ስትሆን፤ አንድ ሊትር ቤንዚን በ$0.0229 ለሕዝቧ ታቀርባለች። በሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሊቢያ እና ቬኒዙዌላ በዚሁ ቅደም ተከተል በ$0.030 እና በ$0.035 ያቀርባሉ።

ኢትዮጵያ 150 የዓለም ሀገራት ከሚያቀርቡበት ዝቅ ባለው በ$0.805 ለማቅረብ ዋጋ መቁረጧን መረጃው ያሳያል። ድረ-ገጹ ባሰፈረው መረጃ መሰረት በዓለም በከፍተኛ ዋጋ ነዳጅ በማቅረብ ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀጡት ሀገራት ሆንግኮንግ ($3.369)፣ አይስላንድ ($2.233) እና ሞናኮ ($2.203) ናቸው።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0xEd89woHZBUnVaVrjDGZV6qt8d7BzGaeXBE2wz9fyN9hq5ZZznXFuKHy5bCMMUwil
👍34👎115
በአዲስ አበባ የሚሰሩ ባንኮች ብሔራዊ መታወቂያን አስገዳጅ ያደረጉት ለጊዜው ለአዲስ ተመዝጋቢ ደንበኞች ብቻ ነው፦ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም
**********

በአዲስ አበባ በተለያዩ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ ግዴታ እየሆነ ስለመምጣቱ ይነገራል።

ለአብነትም በአዲስ አበባ የሚሰሩ ባንኮች አገልግሎት ለመስጠት ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን አስገዳጅ ማድረጋቸው መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ አስገዳጅ የተደረገው በሁሉም የባንክ ተገልጋዮች ላይ አለመሆኑ ተገልጿል።

በመዲናዋ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ አስገዳጅ የተደረገው ለጊዜው ለአዲስ ተመዝጋቢ ደንበኞች ብቻ መሆኑን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርዓያሥላሴ ገልፀዋል።

ብሔራዊ መታወቂያ በሂደት በሁሉም ተቋማት አስገዳጅ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመው፤ ያም ቢሆን አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ምዝገባው እየተካሄደ በመሆኑ መታወቂያውን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደማይሆን ነው አቶ ዮዳሔ ከኢቢሲ የአዲስ ቀን የሀገር ጉዳይ ዝግጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንደ ግለሰብ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ለመካተት እንዲሁም ከተለያየ ወንጀል እና መጭበርበር ለመጠበቅ እንደሚያስችልም ነው ኃላፊው የጠቆሙት።

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም የግለሰቦችን መረጃ በጥንቃቄ እንደሚይዝና ለሌሎች አሳልፎ እንደማይሰጥም ነው ያረጋገጡት።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid023RH91taqMoqzcmpDaryW3B6hA6GEY9vSDBUQjwzSmkvCxyMEvxwsuXkE1r4ptFmql
👍161👎1
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ የለውጥ ሥራዎች አዳዲስ ሀብቶችን መፍጠር ተችሏል፦ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
*********

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ የለውጥ ሥስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

የስልጠና ተቋማቱ ዜጎች ሀብት የሚፈጥር የሥራ ሃሳብ አመንጪ እና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋማቱ የክህሎት ልማትን በማጎልበት ለኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂነትና ሥራ አጥነት ቅነሳ አስፈላጊ እንደሆኑም ሚኒስትሯ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ለክህሎት ልማት ደግሞ የስልጠና ተቋማትን ማመዘን፣ መሠረተ ልማት ማሟላትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ስራዎች ማከናወን ይጠይቃል ብለዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ የለውጥ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል።

በዚህም ተቋማቱ የሚያወጧቸውን ተማሪዎች ሀብት ፈጣሪ የሥራ ሃሳብ አመንጪና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ ነው ብለዋል።

በቀጣይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በዚህ ቅኝት እንዲሰሩና ተደራሽነታቸው እንዲሰፋ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

ይህም ዝንባሌና መክሊት ያላቸው ዜጎች ሥራ መፍጠር እንዲችሉ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት።
👍151
ምክር ቤቱ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሚቀርብለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል
*********

6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ጉባዔው፥ የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓትን ለመደንገግ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል።

በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
👍305
የሀገራዊ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ እና ግምገማ ቡድኖች መሪዎች ግኝቶቻቸውን አቀረቡ
***********************

የሀገራዊ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ እና ግምገማ ቡድኖች መሪዎች ግምገማዎቻቸውን እና ግኝቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለ አፈፃፀም ግምገማ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል።

ይኽን ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የተመራ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ዛሬ ተካሂዷል።

በስብሰባው ላይ የመስክ ምልከታ እና ግምገማ ቡድኖች መሪዎች ግምገማዎቻቸውን እና ግኝቶቻቸውን ማቅረባቸው ታውቋል፡፡

ይኽ የሱፐርቪዥን እና የግብረመልስ ሂደት ሰፋ ያለው ሥርዓትን የማጠናከር ተግባር አካል ሲሆን አፈፃፀሞችን በዞን እና ወረዳ ደረጃ በመመልከት ክፍተቶችን መለየትን አላማ ማድረጉንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የማኀበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
👍197