ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ከዚህ በታች ባስቀመጥነው ማስፈንጠሪያ ተመርታችሁ google form ላይ ያሉትን ጥያቄዎችን እንድትመልሱ በትሕትና እንጠይቃለን። እግዚአብሔር ከፈቀደ ደግሞ የመልሳችሁን ፍሬ በቅርቡ ታዩታላችሁ።
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe-O-CqWimZ7fAo6rfa5vbc7cvO0_OgzLn-aCVPXtikuFUcvw/viewform?usp=header
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe-O-CqWimZ7fAo6rfa5vbc7cvO0_OgzLn-aCVPXtikuFUcvw/viewform?usp=header
Google Docs
ከታች ያሉት ጥያቄዎች ለአገልግሎት ተፈልገው በመሆኑ እባክዎ ጥያቄዎቹን በታማኝነት ይመልሱ፤ የእርስዎን መልስ ከአዘጋጁ በቀር ማንም አያየውም፤ አለመመለስ የሚፈልጉት ጥያቄ ካለ የመዝለል ሙሉ መብት አልዎ።
❤32💯1
"በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ፣ ከነቢያት ማኅበር ሁሉ ጋራ ወደኔ ነይ፡፡ ካንደበታቸው የወጣውን የምስጋናሽን ኃይለ ቃል ልብ ታስደርጊልኝ ዘንድ፡፡ ድንግል ሆይ፣ የቃልን ካንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአስተማሩ፣ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ሐዋርያት ጋራ ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ፣ በሥጋቸው የልጅሽን መከራ ከተሸከሙ የሰማዕትነታቸውን ደም ከተቀቡ ሰማዕታት፣ እርሳቸው ሁለት ልሳን ያለው ሰይፍ የሚታጠቁ ድል የሚነሱ የንጉሥ ሠራዊት ናቸው፡፡ ከርሳቸው ማኅበር ጋራ ደግሞ በረድኤት ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ በማመንዘር እድፍ ልብሳቸውን ካላሳደፉ፣ ለመንፈስም ማደሪያ ከሆኑ ንጹሓን ደናግል ማኅበር ጋራ ወደኔ ነዪ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!
❤306🙏20🥰15🕊6🔥3😍3
በላይ በሰማይ ከወርቅ እና ውድ ከሆኑ ማዕድናት ይልቅ የከበረውን የጽድቅ አክሊል የሚያቀዳጀው እና የማያልፈውን ርስት የሚያወርሰው ጌታ፣ በምድር ግን በነዳያን አድሮ ሲለምን እና የእኛን ድቃቂ ሳንቲም ደጅ ሲጠና እናገኘዋለን፡፡ በኋላ በምጽአት ደግሞ ‹‹ተርቤ አላበላችሁኝምና፣ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፣ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝምና፣ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፣ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና›› ብሎ ሲወቅስ እንሰማዋለን፡፡
‹‹ስለ ለምን ታሳድደኛለህ?›› የሚለው የክርስቶስ ጥያቄ ከሳውል ወደ እኛ ሲዞር ‹‹ስለ ምን ታስርበኛለህ?››፣ ‹‹ስለ ምን ታሳርዘኛለህ?›› የሚል መልክ ይዞ ይመጣል፡፡ ክርስቶስ በሳውል ብቻ አይደለም የተሳደደው፣ ምጽዋትን በማያውቁ በእኛ አጫጭር እጆች ምክንያት ይራባል፤ በስስታምነታችንም ዕርቃን ይወጣል፡፡ ‹‹ለምን ታስርበኛለህ?›› ሲለን እንደ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ሆይ ማን ነህ?›› ማለትስ ይከጅለን ይሆን? የሚያሳዝነው ግን ይህ አላዋቂነት እኛ ጋር ሲደርስ አለመሥራቱ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም እኛ ‹‹ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት›› ብሎ ባስተማረው በክርስቶስ ቃል በምታምን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንኖር የሐዲስ ኪዳን ምእመናን ነን፡፡(ማቴ 25)
ቅዱስ ጳውሎስ፣ ገጽ: 119
መጽሐፉን በአዲስ አበባ ደግሞ አምስት ኪሎ አካባቢ በሰርዲኖን፣ ብራና፣ አርጋኖን፣ ባኮስ መጻሕፍት መደብር እንዲሁም በሁሉም የጃፋር መጻሕፍት መደብር ያገኙታል።
መልካም የሱባኤ እና የንባብ ሳምንት ይሁንልን!

❤140🙏8👏5👍3🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“ርኩሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች“
መልካም ሱባኤ!!!
መልካም ሱባኤ!!!
❤173🙏21👍2