Dn Abel Kassahun Mekuria
15.3K subscribers
538 photos
48 videos
1 file
846 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።

ይወዳጁን

ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW
Download Telegram
የተባለው ሰዓት ለእርስዎ አመቺ ነው?
Anonymous Poll
79%
አዎ ይመቸኛል
7%
አይመቸኝም
14%
ሰዓቱ ቢስተካከል
25👍11🙏4👏3
ሰላም እንዴት አመሻችሁ ክቡራን፣

ከዚህ በፊት የዕብራውያን መልእክት ሐተታ ትምህርታት ጀምረን ለዐሥር ክፍላት መማራችን ይታወቃል። ይሁን እንጂ ትምህርቱ ይሰጥ የነበረበት ሰዓት ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ላሉ ብዙም አመቺ ስላልነበር የሰዓት ማስተካከያ ቢደረግ የሚሉ አስተያየቶች ሲደርሱን ቆይተዋል። በዚህ መሠረት የonline ትምሀ‍እርቱን በኢትዮጵያ አቆጣጠር አርብ ከምሽቱ 4:00 እስከ 5:00 ድረስ ለማድረግ አስበናል።

ከላይ ባስቀመጥነው poll ላይ የተባለው ሰዓት የሚመች መሆኑን እና አለመሆኑን እንድትገልጹልን እንዲሁም ተጨማሪ የሰዓት ማስተካከያ አስተያየት ካላችሁም ሐሳባችሁን በcomment section እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን!

=) ትምህርቱ እዚሁ Telegram Channel ላይ በlive stream ነው የሚሰጠው።
🙏77👍2619👏2
ሰላም እንዴት ቆያችሁ፣

በብዙዎቻችሁ ድምፅ መሠረት “የዕብራውያን መልእክት ሐተታ” ትምህርታችን አርብ ከምሽቱ 4:00-5:00 ባለው እንዲደረግ ተወስኗል። ስለዚህም ነገ የካቲት 21 ልክ 4፡00 ሰዓት ላይ ትምህርታችንን የምንጀምር ይሆናል። ትምህርቱ ከክፍል አንድ ጀምሮ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህ ቀደም የመማር ዕድል ላልነበራቸው ምንም የሚያመልጣቸው ነገር አይኖርም። እስከ ክፍል ዐሥር የተማሩትም ቢሆኑ አቀራረቡ እና ይዘቱ ካለፈው ይልቅ ሰፋ ስለሚል የተሻለ ተጠቃሚዎች ያደርጋቸዋል።

እስከዚያው ትምህርቱ የሚተላለፍበትን ይህን የTelegram Channel link ለብዙዎች እያጋራን እንቆይ።

“ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ” መዝ 119:162


https://tttttt.me/Dnabel
147👍42🙏17👏6👌2
“እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ” 2 ጴጥ 3:15

ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://tttttt.me/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

ለአማራጭ እንዲሆን የzoom meeting የተዘጋጀ ሲሆን፣ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1
155👍52🙏12🥰5
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድር ነው? እንዴትስ እናንብብ?
62👍18👌2
Audio
148🙏42🥰16🔥6👍4👏2
+++ የጀማሪ ጠባይ +++

መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል። አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ። የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል። ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።

የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም። ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል። መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው። መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል። አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ።"

ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?" እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም። ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም። ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።

ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል። ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል። "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው። ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።

ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ። እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሰኔ 22፣ 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
288🙏53👍39👏8🥰6
ለጥያቄ እና አንዳንድ የሚለቀቁ Documents ለማግኘት ይህን chat group ይወዳጁ።

https://tttttt.me/+M68QBLoXQfpmOTVk
👍2211
+++ "ለዚህ መች ጸለይን?" +++

በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰባዊ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲረዳ የተቋቋመ የካህናት (የቀሳውስት) ጉባኤ ነበረ። የቀድሞው የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳም ይህን ስብስብ እንዲቀላቀሉ ለአባ ሚካኤል ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት የዚህ ጉባኤ አባል ሆኑ። ታዲያ አንድ ቀን አባ ሚካኤልን ጨምሮ የጉባኤው የበላይ ኃላፊ የሆኑት ጳጳስና ሌሎችም ካህናት የተጣሉ ባልና ሚስትን ሊያስታርቁ ተሰበሰቡ። ይሁን እንጂ የባልና የሚስትየው ጠብ እንዲህ በቀላሉ ሊበርድ የሚችል አልነበረምና ጳጳሱም ሆኑ ቀሳውስቱም ሁለቱን ለማስማማት ብዙ ቢጥሩም ግን አልተሳካላቸውም።

በስተመጨረሻም ጳጳሱ ወደ አባ ሚካኤል እየጠቆሙ "አባ ሚካኤል ለምን ዝም ብለው ተቀመጡ? እስኪ እርሶ ይሻላል ብለው የሚያስቡትን ይንገሩን?" አሏቸው። አባ ሚካኤልም "ብፁዕነትዎ፣ እንጸልይበት!" አሉ። ጳጳሱም "ይህን ጉባኤ ከመጀመራችን በፊት እኮ ጸልየናል" ቢሏቸው አባ ሚካኤል "አዎን አባታችን፤ ለዚህ ችግር ግን አልጸለይንም" አሉ። ከዚያ ሁሉም ለጸሎት ተነሡ። በጳጳሱ ፈቃድ በአቡነ ሚካኤል መሪነት ጸሎት አደረጉ። ጸሎቱ እንዳለቀም እነዚያ የተጣሉት ባልና ሚስት ክርክራቸውን ሁሉ ትተው በጉባኤው ፊት በፍቅር ተቃቀፉ። ሰላም አወረዱ። ይህን ጊዜ ከቀሳውስቱ አንዱ "አባታችን ከመጀመሪያ እንዲህ ቢሉን ምን ነበር?! አሳረፉን እኮ" ብለው ጉባኤውን ፈገግ አሰኙት።

እኛስ ያልጸለይንባቸው ስንት ችሮች አሉብን?

ብዙ ቋጠሮ የሚፈታው ግን በብዙዎች የሚረሳው ትልቁ መፍትሔ፣ ጸሎት!!!

(አባ ሚካኤል ኢብራሂም (1899-1975) የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ለበርካታ ዓመታት በትጋት ያገለገሉና እጅግ የሚያስቀና የጸሎት ሕይወት የነበራቸው አባት ናቸው።)


ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
አዲስ አበባ
240👍31🙏24🥰9🔥2
ሰላም እንዴት ቆያችሁ፣

ያለፈው ሳምንት የመግቢያ ትምህርታችን እንዴት ነበር? እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቀጣይ ሁለተኛውን ክፍል ነገ አርብ የካቲት 28 ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ እንማራለን።

ትምህርቱ የሚተላለፍበትን ይህን የTelegram Channel link ለብዙዎች በማጋራት የቃለ እግዚአብሔሩ ተሳታፊ ያድርጉ።

“ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ” መዝ 119:162


https://tttttt.me/Dnabel
84👍23🙏9
"ስላንቺም የተነገረው ፍጹም ምስጋና ሁሉ በምስጋናሽ ባሕር ጥልቅነት ዘንድ እንደ ጠብታ ነው።... የምስጋና ዘውድ በራስሽ ላይ ነው። የጽድቅ ጋሻም አንቺን ይከባል።... ሳላቋርጥ አመሰግንሽ ዘንድ የኪሩቤልን አፍ፣ የሱራፌልን ልሳን ብቀበል፤...የሰሎሞንን ጥበብ ብነሣ፣ የልቡናዬም አጽቅ ቢሰፋ እስከ ባሕር ቢዘረጋም፣ የቃሌም ቡቃያ እስከ ቀላይ ድረስ ቢጠልቅ በዚህ ውዳሴሽን ለመፈጸም አልችልም"

የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት፣ የስሟም አጠራር ከአፉ ከማይጠፋ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገኘ የምስጋና ቃል

https://tttttt.me/Dnabel
223👍16🙏14🥰4
ክፍል ሁለት ትምህርታችንን ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://tttttt.me/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1
👍4336🙏3
Live stream scheduled for
ትምህርቱን ከመጀመራችን በፊት ለክለሳ የሚረዳ መመዘኛ ተዘጋጅቷል። መልሳችሁን በcomment section ላይ 1 2 እያላችሁ በአጭሩ አስቀምጡ። (ሙሉውን ያገኘ ይሸለማል)

1 በሐዋርያት ሥራ የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ የሚጀምረው ከስተኛው ምዕራፍ ነው ?

2 ሳውል ክርስቲያኖችን ያሳድ የነበረው ከጥላቻ የተነሣ ነው?

3 ሳውል በደማስቆ እንዴት ሊያምን ቻለ ?

4 ሳውልን ያጠመቀው ካህን ማን ይባላል ?

5 የቅዱስ ጳውሎስ ሮማዊነት ምን ጠቀመው?

6 በአሳዳጅነት ተጀምሮ በተሳዳጅነት የሚፈጸመው የጳውሎስ ታሪክ ለእኛ ምን መልእክት አለው?
🙏43👍146
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
“ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል፡ አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ”

ኢሳ 49:14-16
231👍15🙏11🤔3