የ #ኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ በግማሽ ዓመቱ ከዘጠኝ ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት በዲጂታል አማራጮች ማከናወኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶቹ በኩል ከዘጠኝ ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን አስታወቀ።
ይህም በባንኩ በኩል ከተከናወኑ ጠቅላላ ዝውውሮች እና ክፍያዎች 88 በመቶ ገደማ ድርሻ ይይዛል ተብሏል።
ይህ ውጤት ይፋ የተደረገው ባንኩ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ሲሆን፣ የስትራቴጂክ ዕቅድ እና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ወጋየሁ ገብረማርያም የባንኩን የስድስት ወራት ሪፖርት አቅርበዋል።
እንደ አቶ ወጋየሁ ገለጻ፣ በተያዘው ወቅት በዲጂታል መሠረተ-ልማቶች ከዘጠኝ ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም ከጠቅላላ የባንክ ግብይቱ 87.9 በመቶ ድርሻ አለው ብለዋል።
በባለፈው በጀት ዓመት ባንኩ በሀገሪቱ የዲጂታል ግብይት እና ክፍያ ውስጥ 73 በመቶ ድርሻ እንደነበረው የጠቀሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ በዚህ ዓመትም ባንኩ በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ዘርፍ ያለውን የበላይነት እንደሚያስቀጥል አመልክተዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ ይህ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ እና ይህም የደንበኞችን ተደራሽነትና የባንኩን የሥራ ቅልጥፍና በማሻሻሉ እንደሆነ ተናግረዋል።
በተያያዘም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ዓመቱ 36.19 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:- https://www.facebook.com/share/18CrfusYMv/

ተወርሶ የነበረው የሰብአዊ እርዳታ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) መመለሱን የ #ሶማሊያ መንግሥት አስታወቀ
የ #ሞቃዲሾ ወደብ ማስፋፊያ ሥራን ተከትሎ ከመጋዘን ተነስተው የነበሩ የረድኤት ቁሳቁሶች ለዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) መመለሳቸውን የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት ሰኞ ዕለት አስታወቀ።
የሀገሪቱ መንገስት ይህን ያስታወቀው፤ በሞቃዲሾ ወደብ የሚገኝ የአርዳታ ቁሳቁስ ማከማቻ "ፈርሷል" እንዲሁም "እርዳታ ተዘርፏል" የሚሉ ዘገባዎች ሲወጡ መቆየታቸውን ተከትሎ ነው።
የሶማሊያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ “ከመጋዘኑ ተነስተው የነበሩት ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ተመልሰዋል” ብሏል።
በመግለጫው አክሎም መንግሥት “ለተፈጠረው አሳዛኝ ሁኔታ ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስድ” ገልጿል።
የሶማሊያ ባለሥልጣናት በአሜሪካ የሚደገፍ መጋዘንን አፍርሰዋል እንዲሁም ለተረጂዎች የታሰበ 76 ሜትሪክ ቶን የምግብ እርዳታ “በሕገ-ወጥ መንገድ ወርሰዋል” ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መወንጀሉ ይታወሳል።
አሜሪካ ይህንን ድርጊት በመቃወም ለሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት የምትሰጠውን ሰብአዊ እርዳታ አግዳለች።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02msRDkGxipLBFfCG7vfy3viVwQxY3BFtBPyEMZg5TmJds2dASiLfbocVer3as1mUWl

ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በማልማት ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸው ተገለፀ
ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በማልማት ስራ የተደራጁ ማሕበራት ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን የአዲስ አበባ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሙላት ተገኘ በመዲናዋ ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በማልማት ሥራ ዙሪያ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት መሆኑን ጠቅሰው በዚህም ለበርካቶች የስራ እድል መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች ከ400 በላይ በሚሆኑ ማሕበራት በመደራጀት በዘርፉ ተሰማርተው ገቢ እያገኙ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ምክትል ዳይሬክተሩ፤ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ እነዚህ ማህበራት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆን ገቢ ማግኘታቸውን ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን ወደ አዲስ ምርት በመቀየር ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች የገበያ ትስስር እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የተለያዩ ደረቅ ቆሻሻዎች በወንዞች እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ እየተጣሉ አካባቢዎችን ሲበክሉ እንደነበር የገለጹት አቶ ሙላት፤ ነገር ግን የጽዳት ሥራ ከተጀመረ ወዲህ ደረቅ ቆሻሻዎች በአግባቡ የሚሰበሰቡበት እና አካባቢን የማይበክሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ተችሏል ብለዋል።

#ኢንተርፖል በመላው ዓለም ባካሄደው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ዘመቻ ከ3,700 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ
ኢንተርፖል ያስተባበረው ዓለም አቀፍ የሕገ-ወጥ የሰዎች አጋቾች እና አዘዋዋሪዎች መከላከያ ዘመቻ፣ ከ3,700 በላይ ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ማድረጉንና በዝውውር አደጋ ላይ የነበሩ ከ4,400 በላይ ሰዎችን ለመታደግ መቻሉን ተቋሙ ሰኞ ዕለት አስታውቋል።
ኢንተርፖል እንደገለጸው፣ ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 12 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ 14,000 የፖሊስ መኮንኖች "ሊበርቴራ 3" የተሰኘ ዘመቻ አካሂደዋል።
በ119 አገራት ውስጥ በተከናወነው በዚህ ኦፕሬሽን 3,744 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ 4,414 ለአደጋ ተጋላጭ የነበሩ ሰዎችን መታደግ መቻሉ ተጠቁሟል። በተጨማሪም በሕገ-ወጥ ደላሎች ሴራ ውስጥ የነበሩ 12,992 ሰዎች መለየታቸው ተገልጿል።
የተለያዩ አገራት ባለሥልጣናት ቢያንስ 720 አዳዲስ ምርመራዎችን መጀመራቸውን ተቋሙ ገልጿል። ዋና መሥሪያ ቤቱን በፈረንሳይ ያደረገው ኢንተርፖል፤ 196 የዓለም አገራት ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረት የፖሊስ ትብብርን በማጠናከር ድጋፍ ይሰጣል።
የኢንተርፖል ዋና ፀሐፊ ቫልዲሲ ኡርኩይዛ “የወንጀል መረቦች አዳዲስ መንገዶችን፣ ዲጂታል መድረኮችን እና ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመጠቀም ስልታቸውን እያቀያየሩ ይገኛሉ” ያሉ ሲሆን አክለውም “እነዚህን የወንጀል አሰራሮች መለየት የሕግ አስከባሪ አካላት ሊመጡ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድመው እንዲረዱ፣ የወንጀል መረቦችን ገና በጅምሩ እንዲበታትኑ እና ተጎጂዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲጠብቁ ያስችላቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:- https://www.facebook.com/share/17bgfwiyPT/

ዜና፡ የ #ትግራይና #አፋር ሕዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲ-ጉደም ከተማ ተካሄደ
በትግራይ እና በአፋር ሕዝቦች መካከል ያለውን አንድነት እና አብሮነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በትግራይ ክልል በአዲ-ጉደም ከተማ ተካሄደ። በኮንፈረንሱ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
እንደ ትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፣ ኮንፈረንሱ ትኩረቱን ያደረገው በትግራይ ክልል ሕንጣሎ ወረዳ በሚገኘው አራ-ዓለም ሰገዳ እና በአፋር ክልል አባዓላ ወረዳ ጋሌሶን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪዎች መካከል ሰላማዊ ግንኙነትን መፍጠር ላይ ነው ተብሏል። ይህም የሕዝብ ለሕዝብ ትብብር ለዘላቂ ሰላም መሠረት መሆኑ ተመልክቷል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ከላሊ ሐጋዚ፣ በትግራይና በአፋር ሕዝቦች መካከል ያለውን አንድነት አስፈላጊነት ገልጸው በሁሉም ዘርፎች ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
“ባለሥልጣናት ይመጣሉ ይሄዳሉ፤ ጎረቤትና ማኅበረሰብ ግን ዘላቂ ናቸው” ያሉት አስተዳዳሪው፣ ሰላምን ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላትን በጋራ መመከት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሕንጣሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጎይቶም ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ሁለቱ ማኅበረሰቦች በታሪክ በሰላም ሲኖሩ የቆዩ መሆናቸውንና አለመግባባቶችን በሽማግሌዎችና በጎረቤቶች አማካኝነት በውይይት እንደሚፈቱ ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=10496

Addis standard
የትግራይና አፋር ሕዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲ-ጉደም ከተማ ተካሄደ - Addis standard
መቀለ፣ ጥር 18፣ 2018 ዓ.ም፦ በትግራይ እና በአፋር ሕዝቦች መካከል ያለውን አንድነት እና አብሮነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በትግራይ ክልል በአዲ-ጉደም ከተማ ተካሄደ። በኮንፈረንሱ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። እንደ ትግራይ ክልል መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፣ ኮንፈረንሱ ትኩረቱን ያደረገው በትግራይ ክልል ሕንጣሎ…
የገንዘብ ሚኒስትሩ የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠየቁ፤ ከባንኩ ከፍተኛ አመራር ጋርም በኢኮኖሚ ማሻሻያው ዙሪያ መክረዋል
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከዳር ለማድረስ፣ ከዓለም ባንክ የሚደረገላት የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቋን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ውይይቱ የተካሄደው ትናንት ጥር 18/2018 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና በዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዌንካይ ዣንግ መካከል ነው።
በውይይታቸውም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ መንግሥት እያከናወነ ስላለው የማሻሻያ ፕሮግራም ለዣንግ ገለጻ አድርገዋል። የዚህ ማሻሻያ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በግል ዘርፉ ወደሚመራ የኢኮኖሚ ሥርዓት ማሸጋገር እንደሆነም አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ በተጨማሪም የኢኮኖሚ ዕድገት ምንጮችን ለማስፋት፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ እና የቱሪዝም ዘርፎችን ለማነቃቃት፣ እንዲሁም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚደረግ የተሻለ ትስስር ቀጣናዊ ውህደትን ለማጠናከር የታቀዱ ዕቅዶች ላይ ገለፃ አድርገዋል።
አቶ አህመድ ሽዴ፣ የዓለም ባንክ በዋና ዋና የልማት ዘርፎች ላይ ለሚያደርገው "ከፍተኛ ድጋፍ" ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል። አክለውም ባንኩ የኢትዮጵያን የማሻሻያ ሥራዎች እና ለልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት በማስቀጠል ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:- https://www.facebook.com/share/1CLXCv6zRA/

የ #አሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የአቭዬሽን ኤክስፖ ጎበኙ
የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው እና የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የአቭዬሽን ኤክስፖ መጎብኘታቸውን መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።
በኢትዮጵያ በኩል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጉብኝቱ መሳተፋቸውም ተገልጿል።
በዚህ ኤክስፖ አየር ኃይልን ጨምሮ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ፣መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ፣ የመከላከያ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችም አለም አቀፍ ደርጅቶች ምርቶቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል ተብሏል።
በኤክስፖው የቀረቡት ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ስኬት የሚያሳዩ ስለመሆናቸው መከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል።
የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው ከጉብኝቱ በኋላ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀበባል ምስጋና አቅርበው፤ ኢትዮጵያ በመገኘታቸው ክብር እንደሚሠማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጠልም ተናግረዋል።
የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን በበኩላቸው ለቀጠናው ሰላም በተለይም እንደ አልሸባብ እና አይኤስኤስ ያሉ ሽብረተኞችን ለመከላከል እና ለመደምሰስ በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ዝውውር እና በሰው መነገድ ወንጀል በተሳተፉ 28 ተከሳሾች ላይ ክስ መሰረተ
የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ 1 ሺህ 8 መቶ የሚሆኑ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ በከባድ የሰው ልጅ መነገድ እና በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል በተሳተፉ 28 ተከሳሾች ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ክስ መመስረቱን ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ተከሳሾቹ የተደራጀ የወንጀል ቡድን በመመስረት ሰዎችን በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለማሻገር በማታለል እጅግ አሰቃቂ ለሆነ እንግልት እና ዝርፊያ ዳርገዋል ተብሏል።
የዐቃቤ ሕግ ክስ፣ ተከሳሾቹ በስራቸው ሌሎች ደላሎችን በመመልመል ሰዎችን የተሻለ ኑሮ እንደሚያገኙ በማሳመን ወደ ባህርዳር እና ጎንደር በመላክ በኩል ወደ ሱዳን ድንበር በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያወጡ መቆየታቸውን ያመለክታል።
ተጎጂዎቹ የኢትዮጵያን ድንበር ካለፉ በኋላ በሊቢያ በሚገኙ መጋዘኖች ውስጥ እንዲታጎሩ በማድረግ፣ በሕይወት ለመቆየት ብቻ የሚበቃ ምግብ እየተሰጣቸው ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ከፍተኛ ገንዘብ ሲጠየቅባቸው እንደነበር ተገልጿል።
ገንዘብ በፍጥነት መክፈል ያልቻሉ ተጎጂዎች እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እየተደበደቡና እየተሰቃዩ ምስላቸው በቪዲዮ ተቀርጾ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመላክ ከፍተኛ ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ክሱ ያሳያል።
በዚህ የወንጀል ሰንሰለት ውስጥ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ተከሳሾች ብቻ በባንክ ሂሳባቸው ከሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰባቸው መረጋገጡን የዐቃቤ ህግ ክስ ተመላክቷል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02nkdyiZa84kQ3YrMt29gntKtF5aBQskWZECkFbipqt9cYFNf7zW4sgwe1fLbbsUppl

#ኢትዮጵያና #አሜሪካ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገለፀ
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አርኤም አንደርሰንን በቢሯቸው ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኢንጂነር አይሻ በዚሁ ወቅት ሁለቱ ሀገራት ከዚህ በፊት የቆየ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ አሁን ላይ እያደገ የመጣውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲና ወታደራዊ ግንኙነት ወደላቀ ስታራቴጂካዊ የሥራ አጋርነት በማሳደግ የሁለቱን ሀገራት እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በሰላምና በፀጥታ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልፀው፤ የሁለቱንም ሀገራት ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ እና ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አርኤም አንደርሰን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ለማክበር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ታሪክን ለማሰላሰልና የወደፊት ትብብርን ለማጠናከር ትርጉም ያለው አጋጣሚ እንደሆነ ገልፀዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኢትዮጵያ አየር ኃይል አከባበር ላይ ለመገኘትና ለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንደገና ለማየትም ዕድል እንደሰጣቸው በመግለጫቸው ላይ ጠቁመዋል፡፡
በተለይም የጋራ ቀጠናዊ የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የአጋርነት ዕድሎችን ለመጠቀም እንዲሁም የሁለቱን አገሮች ግንኙነት እንደገና ለማጠናከር ትልቅ አጋጣሚ መፍጠሩን መናገራቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ: https://www.facebook.com/share/1C1JPYK1q3/

ዜና: በኢትዮጵያ በወርቅ ማልማት ተግባር የተሰማራው የካናዳው አላይድ ጎልድ በ4 ቢሊዮን ዶላር ለቻይናው ዚጂን ጎልድ ሊሸጥ ነው
በኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የካናዳው የወርቅ ማዕድን ኩባንያ አላይድ ጎልድ በቻይናው ዚጂን ጎልድ ኢንተርናሽናል መገዛቱን ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል። ግዥው በሙሉ በጥሬ ገንዘብ የሚፈጸም ሲሆን፣ ዋጋውም በግምት 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው ተብሏል።
በሆንግ ኮንግ የአክሲዮን ገበያ የተመዘገበው ዚጂን ጎልድ ኢንተርናሽናል፣ አላይድ ጎልድን በ5.5 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር (4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር) ለመግዛት ተስማምቷል። ፋይናንሺያል ታይምስ እንደዘገበው፣ ይህ ግዢ ሊፈጸም የቻለው የወርቅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ፣ በማዕድን ዘርፉ ውስጥ ያሉ ኩባንያዎች እርስ በርስ በመጣመር አቅማቸውን እያጠናከሩ በመሆናቸው ነው።
አላይድ ጎልድ በኢትዮጵያ፣ በማሊ እና በኮትዲቩዋር የማዕድን ማውጣት ሥራዎች አሉት። ኩባንያው በስምምነቱ መደሰቱን የገለጸ ሲሆን፣ በዚህ ግዢ የአንድ አክሲዮን ዋጋ 44 የካናዳ ዶላር እንዲሆን ተደርጓል። ይህም ስምምነቱ ከመታወቁ በፊት ከነበረው የ30 ቀናት አማካይ የአክሲዮን ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ ጭማሪ አለው ተብሏል።
ይህ የዋጋ መናር የወርቅ ዋጋ በዓለም ገበያ በመጨመሩ ምክንያት ባለሀብቶች በማዕድን ሀብቶች ላይ ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ማደጉን ያሳያል።
ተጨማሪ ለማንበብ:- https://www.facebook.com/share/1FBCWxygmK/

#ዘመን_ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 106 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገለፀ
ዘመን ባንክ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ አጠቃላይ ሀብቱን 106 ቢሊዮን ብር ማድረሱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ዘበነ አስታወቁ።
ባንኩ በዚሁ የመንፈቀ ዓመት ጊዜ ውስጥ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ 80 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ይህም ባንኩ የተረጋጋ ዕድገትና ጠንካራ የደንበኞች አመኔታ እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ እንደተገለፀው፣ ባንኩ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታሉንም ወደ 14 ቢሊዮን ብር አሳድጓል።
አቶ ደረጀ አፈፃፀሙን ሲያብራሩ “ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲወዳደር የዘንድሮው የላቀና ስኬታማ የሥራ ጊዜ ያሳለፍንበት ነበር” ብለዋል።
የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር በበኩላቸው፣ ለተመዘገበው ውጤት ለአመራሩና ለሠራተኞች ምስጋና አቅርበው፤ ቦርዱ በሁለተኛው ግማሽ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ አሳስቧል።
የባንኩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት በዚህ ውይይት ላይ፣ የተመዘገበው ስኬት የባንኩን ደንበኛ ተኮር አገልግሎትና ጥንቃቄ የተሞላበት የፋይናንስ አስተዳደር የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጿል።

ዜና፡ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ3,400 በላይ #ኢትዮጵያውያን ከ #ሳዑዲ–ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ 3,422 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህም ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሀገር የተመለሱ ዜጎችን ቁጥር 45,093 አድርሶታል።
ሚኒስቴሩ በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ተመላሾቹ በ14 መደበኛ በረራዎች የገቡ ሲሆን፣ ስብጥራቸውም 3,337 ወንዶች፣ 82 ሴቶች እና ሦስት ሕፃናትን ያካተተ ነው። ከእነዚህም መካከል 72 የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው የተመለከተ ሲሆን፣ ይህም የተመላሾችን ተጋላጭነት እንደሚያሳይ ተገልጿል።
ይህ መጠነ ሰፊ ዜጎችን የመመለስ ዘመቻ በሳዑዲ ዓረቢያ በከባድ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 70,000 ዜጎችን ለመመለስ በመጋቢት 2016 ዓ.ም የተጀመረው መርሃ-ግብር አካል መሆኑ ተገልጿል።
ይህ መርሃ-ግብር እንዲጀመር ምክንያት የሆነው በሳዑዲ ዓረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚፈጸሙ አሰቃቂ በደሎች ሪፖርቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው ነው። ሂዩማን ራይትስ ዎች በነሐሴ 2015 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት፣ ከየካቲት 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በሳዑዲ ኃይሎች መገደላቸውን አስፍሯል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=10501

ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ3,400 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 20/ 2018 ዓ.ም፦ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ 3,422 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህም ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሀገር የተመለሱ ዜጎችን ቁጥር 45,093 አድርሶታል። ሚኒስቴሩ በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ተመላሾቹ በ14 መደበኛ በረራዎች የገቡ ሲሆን፣ ስብጥራቸውም 3,337…
#ጣሊያን ሁለተኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ የፊታችን የካቲት 6 በ #አዲስ_አበባ ታካሂዳለች
ጣሊያን ሁለተኛውን የጣሊያን-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ፣ በመጪው የካቲት 6/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደምታካሂድ የሀገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጃ ሜሎኒ በዓመቱ የመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንዳስታወቁት፤ ሁለተኛው የጣሊያን-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በዓመቱ የመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ እንዳስታወቁት፤ ጉባኤው ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር የሚካሄድ ሲሆን፣ ከአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በሕብረቱ መንግሥታትና የሀገራት መሪዎች ጉባኤ ዋዜማ ላይ ይከናወናል።
የጉባኤው ፕሮግራም አካል በመሆን፣ በክብር እንግድነት ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ፣ የካቲት 7 ጠዋት በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።
የጉባኤው ዓላማ ጣሊያን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ማጠናከርና እ.ኤ.አ. በጥር 2024 በሮም ይፋ የተደረገውን የ "ማቴ እቅድ" (Mattei Plan) ግቦች ማሳካት መሆኑን መግለጫው ጠቁሟል።
ዕቅዱ በጣሊያን እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ሥርዓት ያለው ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አጋርነትን ለማሳደግ ያለመ ነው።
ጉባኤው በ "ማቴ ዕቅድ" ዋና ዋና ዓላማዎች ላይ በመመሥረት እንደ ዘላቂ ልማት፣ መሠረተ ልማት፣ ኢነርጂ፣ ትምህርትና ሥልጠና፣ ጤና ጥበቃ እና ግብርና ባሉ ዘርፎች ላይ ትብብርን በማሳደግ ላይ እንደሚያተኩር የጣሊያን መንግሥት ገልጿል።
ተጨማሪ ለማንበብ:- https://www.facebook.com/share/14WRuHoREp2/

ዜና፡ ምርጫ ቦርድ ለስምንት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅሬታ በሰጠው ምላሽ የዲጂታል ምዝገባው “ቴክኒካዊ እንጂ ፖለቲካዊ” ተፅዕኖ እንደሌለው ገለጸ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስምንት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ፣ የቀረቡት ቅሬታዎች “ሕጉንና አሠራሩን ካለመረዳት የመነጩ” ናቸው ሲል ዝርዝር ማብራሪያ ሰጠ።
ስምንት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትላንት ጥር 15 ቀን 2018 ዓም ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ገና በዕጩዎች ምዝገባ ጅምሮ ላይ ሳለ "ሰላማዊውን የፖለቲካ ምህዳር የሚያጨልሙ ተግዳሮቶች" እያጋጠሟቸዉ እንደሚገኝ አስታውቀው፣ ምርጫው "አሳታፊ፣ ሐቀኛ እና ተዓማኒ ሊሆን እንደማይችል" ማሳሰባቸው ይታወሳል።
ፓርቲዎቹ እንደሚሉት፣ ቦርዱ የዲጂታል ቴክኖሎጂ የምዝገባ ሥርዓት በቴክኒክ ደረጃ የመፈተሽ ዕድል አልተሰጣቸውም። በተጨማሪም በምዝገባ ወቅት እንደ መስፈርት የቀረቡት የልደት ምስክር ወረቀት እና የዓይን እማኝ ማቅረብ፣ በተለይ ከከተማ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ፈጽሞ የማይታሰቡ እና ተቃዋሚዎችን ከፉክክር ሜዳው ለማውጣት የታቀዱ “የፖለቲካ ሴራዎች” ናቸው ብለዋል።
ቦርዱ ባወጣው መግለጫ፣ የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓቱ ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሲቪል ማኅበራት ጋር በተደረገ ምክክር የበለጸገ መሆኑን ገልጿል። በዲጂታል የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ላይ የቀረቡትን ተግዳሮቶች አስመልክቶ፣ ሥርዓቱ ፓርቲዎችን ከውጫዊ ተፅዕኖ ነፃ ለማድረግና አሠራሩን ለማዘመን የተዘረጋ መሆኑን አስታውቋል።
https://addisstandard.com/amharic-election2026/?p=1216

Ethiopian Election 2026
ዜና፡ ምርጫ ቦርድ ለስምንት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅሬታ በሰጠው ምላሽ የዲጂታል ምዝገባው “ቴክኒካዊ እንጂ ፖለቲካዊ” ተፅዕኖ እንደሌለው ገለጸ - Ethiopian Election 2026
አዲስ አበባ፣ ጥር 20/ 2018 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስምንት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ፣ የቀረቡት ቅሬታዎች “ሕጉንና አሠራሩን ካለመረዳት የመነጩ” ናቸው ሲል ዝርዝር ማብራሪያ ሰጠ። ስምንት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትላንት ጥር 15 ቀን 2018 ዓም ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ገና በዕጩዎች ምዝገባ ጅምሮ ላይ ሳለ “ሰላማዊውን የፖለቲካ…
የ #ሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘውን #አል_ሲሊክ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተዋጊዎች ማስለቀቁን አስታወቀ
የሱዳን ጦር ሀይል (SAF) ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በብሉ ናይል ግዛት የሚገኘውን አል-ሲሊክ የተባለ ስትራቴጂካዊ ስፍራን፣ ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ።
አናዶሉ የዜና ወኪል ቅዳሜና እሁድ የተካሄደውን ከባድ ውጊያ ተከትሎ የሱዳን ጦር 4ኛ ክፍለ ጦር ሰኞ ዕለት ያወጣውን መግለጫ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፣ አካባቢውን “በታቀደ ወታደራዊ ኦፕሬሽን” መቆጣጠሩንና በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተዋጊዎች ላይ ከፍተኛ የሰውና የንብረት ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።
ክፍለ ጦሩ አክሎም፣ በውጊያው ወቅት በአብዱልአዚዝ አል-ሂሉ የሚመራው የሱዳን ሕዝባዊ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) ተዋጊዎችም መመታታቸውን ገልጿል።
እስካሁን ድረስ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወይም ከሱዳን ሕዝባዊ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን ወገን የተሰጠ መግለጫ የለም።
ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተሰማው፣ ባለፈው እሁድ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና የሱዳን ሕዝባዊ ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን ኃይሎች ከደቡብ ሱዳን ግዛት በመነሳት በብሉ ናይል አካባቢ በሚገኙ አል-ሲሊክ እና ሚልካን ላይ ሰፊ ጥቃት መክፈታቸውን መዘገቡን ተከትሎ ነው።
የሱዳን ባለሥልጣናት ጥቃቱን "የውጭ ወረራ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ደቡብ ሱዳን ግዛቷ ለአጥቂዎቹ ማሰልጠኛ እና ወታደራዊ መሣሪያ ማስተላለፊያ እንዲሆን ፈቅዳለች ሲሉ ከሰዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:- https://www.facebook.com/share/14UTjiPhzrv/