#ፌዴራል_ፖሊስ በዋናው መስሪያ ቤቱ ያደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል አስመረቀ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በዋናው መስሪያ ቤቱ ያደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል በትናንትናው እለት ስራ አስጀመረ። በተጨማሪም ኮማንድ ኮንትሮል ያለው ዘመናዊ መንገድ የሚዘጋ ተሸከርካሪም ተመርቆ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል ተብሏል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከሉ አዲስ የገቡት ድሮኖች ከከተማ ፀጥታ ቁጥጥር ባሻገር የቦርደር ሴኪዩሪቲን ጨምሮ የኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችል ዕድል የሚፈጥሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ በሀገሪቱ ፖሊስ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነው የድሮን ቴክኖሎጂ ማዕከል፤ ወጣት የፖሊስ ኦፊሰሮች የቴክኖሎጂ ስልጠና አግኝተው የተሻለ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈጠረ ነው ሲል ጠቅሰው አሁን ላይ በተቋሙ ያለው የድሮን አቅም በፖሊስ የወንጀል መከላከል ሰርቪላንስ እና የምርመራ ስራ ከፍተኛ እገዛ አለው ብለዋል።
በተጨማሪም እንደ አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ያሉ መድረኮች ሲኖሩ ለተወሰነ ጊዜ መንገዶችን ዘግቶ ቪአይፒዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል የራሱ የሆነ ኮማንድ ኮንትሮል ያለው ዘመናዊ ሮድ ብሎክ (መንገድ የሚዘጋ) ተሸከርካሪም ተመርቆ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል ተብሏል፡፡
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02zdynN9ckoLC9nzty6Z7BKVzhYzUyNmLLrgGkp55imWx7BrvfJKGJcNLjgR8fAXAzl

ምርጫ ቦርድ የአሰራር ሂደት ላይ ግልፅኝነት ለማስፈን እንዲያግዝ የምርጫ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ እንዲጸድቅ መከረ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርዱ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ማሻሻያ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ቦርዱ አዋጆች ሁሉንም አሳታፊ እና ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት አመቺ እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
“የአዋጁ ማሻሻያም ቦርዱ ይበልጥ ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ፍትሐዊ እና ታማኝ እንዲሆን እንደሚያስችለው” አክለው ገልጸዋል ሲል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።
ቦርዱ “ዓለም ዓቀፍ የአሰራር መለኪያዎችን ያሟሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ አሠራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ” መሆኑንም ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። ይህም የምርጫ ቦርድ የአሰራር ሂደት ላይ ግልፅኝነት ለማስፈን እንደሚያግዝ አመላክተዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2019 የተደነገገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ህወሐትን ጨምሮ የታገዱ ፓርቲዎችን ዳግም ህጋዊ ሆነው እንዲመዘገቡ ለማስቻል ባሳለፍነው አመት ግንቦት ወር መሻሻሉ ይታወቃል።

ዜና፡ #ኢትዮጵያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 “አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት” እንዳጋጠማት ሂማን ራይትስ ዎች አስታወቀ
አለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆሪቋሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ኢትዮጵያ “መጠነ ሰፊ ግጭቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት እገዳዎች” ማስተናገዷን በመጥቀስ የሰብዓዊ መብት ሁኔታውን “አስከፊ” ሲል ገልጾታል።
ድርጅቱ አዲስ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፤ ግጭት ባለበት አካባቢዎች እና በሀገሪቱ ሌሎች ስፍራዎች በመንግስት የጸጥታ አካላት፣ በሚሊሻዎች እና በታጣቂ ቡድኖች ከባድ ጥሰቶችን መፈፀማቸውን አመልክቷል። በተለይም በአማራ ክልል ያለው ግጭት አሳሳቢ መሆኑን ገልጾ በመንግስት የጸጥታ አካላት እና በፋኖ ታጣቂዎች “የጦር ወንጀል” ድርጊቶች መፈጸማቸውን ገልጿል።
ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6533

Addis standard
ኢትዮጵያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 “አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት” እንዳጋጠማት ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታወቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 9/ 2017 ዓ/ም፦ አለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆሪቋሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ኢትዮጵያ “መጠነ ሰፊ ግጭቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት እገዳዎች” ማስተናገዷን በመጥቀስ የሰብዓዊ መብት ሁኔታውን “አስከፊ” ሲል ገልጾታል። ድርጅቱ አዲስ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፤ ግጭት ባለበት አካባቢዎች እና በሀገሪቱ ሌሎች ስፍራዎች በመንግስት የጸጥታ አካላት፣ በሚሊሻዎች…
ዜና፡ #ኢትዮጵያ በ #አፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷን ሲፒጄ ገለጸ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷንና በእስር ላይ ካሉ ስድስት ጋዜጠኞች መካከል አምስቱ የሞት ቅጣት ሊያስከትል የሚችል የ"ሽብርተኝነት" ክስ ተመስርቶባቸዋል ሲል የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ትናንት ሐሙስ ዕለት ይፋ ባደረገው የ2024 የጋዜጠኞች እስር ሪፖርት አስታውቋል።
የእስር እርምጃዎቹ የተወሰዱት በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት ጋር የሚገጣጠም መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ፤ ባለሥልጣናቱ "የጦር መሣሪያ የታጠቁ ቡድኖችን እና ደጋፊዎቻቸውን" ለማጥፋት በሚያደርጉት ዘመቻ "ሲቪሎችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ ምሁራንን እና ጋዜጠኞችን" ዒላማ አድርገዋል ብሏል።
ሲፒጄ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋዜጠኞችን ለማሰር "ብዙውን ጊዜ ግልጽ ያልሆኑ የሽብርተኝነት ወይም የጽንፈኝነት ክሶችን" ይጠቀማሉ።
ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6538

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷን ሲፒጄ ገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 9/ 2017 ዓ/ም፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷንና በእስር ላይ ካሉ ስድስት ጋዜጠኞች መካከል አምስቱ የሞት ቅጣት ሊያስከትል የሚችል የ”ሽብርተኝነት” ክስ ተመስርቶባቸዋል ሲል የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ትናንት ሐሙስ ዕለት ይፋ ባደረገው የ2024 የጋዜጠኞች እስር ሪፖርት አስታውቋል። ስድስተኛው ጋዜጠኛ ዬሺሃሳብ አበራ በአማራ…
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 250 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እንዲለቀቅ የሚያስችል ግምገማን አጸደቀ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በአራት አመታት የተራዘመ ብድር ለ #ኢትዮጵያ ለመስጠት ከፈቀደው የ3.4 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ሁለተኛው ዙር የ250 ሚሊየን ዶላር ብድር እንዲለቀቅ የሚያስችል ግምገማን አጸደቀ።
ቦርዱ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፋይናንስ ፕሮግራም ሁለተኛ ግምገማ ያደረገ ሲሆን ይህም 250 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እንዲለቀቅ መንገድ ከፋች ነው ተብሏል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሪፎርም ፕሮግራሙ ከታሰበው የተሻለ ውጤት እንዳስመዘገበ መሆኑን እና የዋጋ ግሽበት ጫና እንደሚጨምር የተገመተው እለመከሰቱን ገልጿል።
በተጨማሪም ጠንካራ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከታቀደው በበለጠ ፍጥነት እያደገ እንደሚገኝ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋር 3.4 ቢሊዮን ዶላር ለአራት ዓመታት የሚቆይ የፋይናንስ ድጋፍ ፕሮግራም ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል። የመጀመሪያው 345 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም መለቀቁ ይታወሳል።
ስምምነቱ ላይ የተደረሰው ኢትዮጵያ ገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት መከተልን ጨምሮ ሰፋፊ የሆኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ማድረጓን ተከትሎ ሲሆን የብድር ስምምነቱ የሀገሪቱን የዕዳ አወቃቀር ለማሻሻል እንደሚያግዛት ተመላክቷል።
==
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ዕውቅና ይሰጡኛል በሚል #ሶማሊላንድ አይኗን ወደ #አሜሪካ መለሰች
ለ #ኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ለመስጠት እና በምላሹም ዕውቅና ለማግኘት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈርማ የነበረችው ሶማሊላንድ ወደ አሜሪካ እያማተረች ነው።
በርካታ ሶማሊላንዳውያን ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለባለፉት 33 ዓመታት ሶማሊላንድ ስትናፍቀው የነበረውን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ አገር ዕውቅና የማግኘት ህልሟን እውን ያደርጉታል በሚል ተስፋን ሰንቀዋል።
ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በተደረሰው የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና አገኛለሁ የሚል ተስፋ ነበራት። ሆኖም በዚህ የመግባባቢያ ስምምነት ቁርሾ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያና ሶማሊያ በቅርቡ ልዩነታቸውን ለመፍታት በአንካራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የመግባቢያ ስምምነቱ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።
ከሶማሊያ ባለሥልጣናት በኩል ይህ የመግባቢያ ስምምነት እንደተሻረ ቢናገሩም ኢትዮጵያ በይፋ ያለችው ነገር የለም።
"ዶናልድ አዳኛችን ነው። ብልህ እና የተግባር ሰው ነው። አምላክ አሜሪካን ይባርክ" ስትል የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነችው አይሻ ኢስማኤል ዕውቅና እናገኛለን በሚል ተስፋ ድምጿ በደስታ ተሞልቶ ለቢቢሲ ተናግራለች።
በሶማሊላንድ መዲና ሐርጌሳ ነዋሪ ለሆነችው አይሻ ይህ ዕውቅና የማግኘት ተስፋ ደስታን የሚያመጣ ቢሆንም በተቃራኒው ለሞቃዲሾ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ትላለች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cy4mme0j8jmo

የ #እስራኤል ካቢኔ የጋዛውን ተኩስ አቁም ስምምነት አጸደቀ
የእስራኤል ካቢኔ የጋዛውን ተኩስ አቁም ስምምነት በ24 ድጋፍ በ8 ተቃውሞ አጸደቀ። 15 ወራቱ ያቆጠረውን የእስራኤል እና ሀማስ ታጣቂዎች ጦርነት ያስቆማል የተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት ለ6 ሰአታት ከፈጅ ውይይት በኋላ ጸድቋል።
በእስራኤል ጥምር መንግስት ውስጥ የገንዘብ ሚኒስትሩ እና የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ስምምነቱን አጥበቀው ከተቃወሙ የካቤኔ አባላቶች መካከል ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ታጋቾች የሚመለሱበትን እና የጋዛው ጦርነት የሚቆምበትን የተኩስ አቁም ስምምነት መንግስት አጽድቋል ሲል አስታውቋል፡፡
የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰበት ረቡዕ ጀምሮ በጋዛ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ከፍተኛ ጥቃቶችን ማድረሳቸውን ቀጥለዋል መባሉን አላይን ዘግቧል፡፡
ምንም እንኳን ስምምነቱ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢጠበቅም ቅዳሜ ማለዳ የእስራኤል የአየር ጥቃት ከካን ዮኒስ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ማዋሲ አካባቢ በሚገኝ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ አምስት ሰዎችን መግደሉን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

#ህወሓት ጠቅላል ጉባዔ እንዲያካሂድ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ቀነ ገደብ እንደማይቀበልና መንግስት"የ #ፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ እንዳይተገበር እንቅፋት መሆኑን” ገለጸ
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ የ #ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ጠቅላል ጉባዔ እንዲያካሂድ ቀነ ገደብ መሰጠቱን እንደማይቀበል አስታወቀ።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ያደረገው ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ “ ህወሓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔ ዛሬ ይሁን ነገ አይቀበልም" ሲል ገልጿል።
ህወሓት ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም “በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ” መመዝገቡ ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።
ይሁን እንጂ ቦርዱ ፓርቲው ለጠቅላላ ጉባዔው ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ምንም ምልክት እንደሌለው ገልጾ፣ በቦርዱ የተላለፉትን ውሳኔዎች በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ሕጉን መሠረት ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02UWHpn6EVweTnUkLskJMSmz2x4L6QcktuPPMCeRF2xZ8LUV5T7uhzAUkBMGexu9HRl

ካለፈው አመት የመጀመሪያ አጋማሽ ጋር ሲነጻጸር 59 በመቶ ብልጫ ያለው ገቢ ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና ተገኘ
በያዝነው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ለውጭ ገበያ ከቀረበ 204 ሺህ 206 ነጥብ 63 ቶን የቡና ምርት 908 ነጥብ 47 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ ሻፊ ኡመር ዛሬ በሰጡት መግለጫ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገቢ ደረጃ የ337 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 59 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል።
አፈጻጸሙም የ86 ሺህ 251 ነጥብ 17 ቶን ወይም 73 በመቶ ብልጫ አለው ማለታቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡
በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ 133 ሺህ 63 ነጥብ 49 ቶን የቡና ምርት በመላክ 714 ነጥብ 99 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ንዑስ ዘርፍ ለማግኘት የታቀደውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ገቢ ለማሳካት ዝርዝር ዓመታዊ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱንም አመላክተዋል፡፡

ዜና: “#በህወሓት አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” - አቡነ ማትያስ
በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል የሚያጨልም ነው ሲሉ #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጻጻስ የሆኑት አቡነ ማትያስ ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና ለግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ገለጹ።
“ሁኔታዎች ከግዜ ወደ ግዜ እየከፋ፤ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል ሊያጠፋ ወደሚችል ሁኔታ እያመራ ይገኛል፤ ይህንን እያየን ዝምታን መምረጥ በሰውና በፈጣሪ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ይህንን የምክር ደብዳቤ ለመጻፍ ተገድጃለሁ” ብለዋል።
ፓትርያርኩ በደብዳቤያቸው ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለመወያየት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካላቸው በመጠቆም ደብዳቤውን ለመጻፈ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
“በእልክ እኔ እሻላለሁ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን፣ እኔ ብቻ ነኝ ለህዝብ የማስበው በሚል በተፈጠረው ውስብስብ ችግር የሚያዝን እንጂ የሚደሰት ህዝብ የለም” ሲሉ ጠቁመዋል።
“በአመራሩ መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዳይበቃ በአንድነት ተስማምቶ ሲኖር በነበረው ህዝብ መካከልም ተጽእኖው እየወረደ ይገኛል” ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6542

“በህወሓት አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” - አቡነ ማትያስ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 12/2017 ዓ.ም፡- በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል የሚያጨልም ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጻጻስ የሆኑት አቡነ ማትያስ ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና ለግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ገለጹ። “ሁኔታዎች ከግዜ ወደ ግዜ እየከፋ፤ የተገኘችውን…
ዜና፡ በ#አፋር ክልል አርብቶ አደሮች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አለመሆናቸው ተገለጸ፤ ባለሥልጣናቱ በግዴታ ለማስለቀቅ አቅደዋል ተብሏል
በአፋር እና በ#ኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት፤ "በአዋሽ እና ዱሌቻ ወረዳዎች ያሉ የተወሰኑ ነዋሪዎች በተለይም ከብቶቻቸው እና ንብረታቸው ላይ ስጋት ያላቸው የአርብቶ አድር ማህበረሰቦች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አይደሉም" ሲል ገልጸ።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት መሠረት፤ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አደጋ ካለባቸው አካባቢዎች ለማስወጣት አስገዳጅ እርምጃዎችን ለመውሰድ እያሰበ ነው።
ከአያኤኤሲ ክላስተር አስተባባሪዎች እና አጋሮች ድጋፍ በተዘጋጀው አዲስ መረጃ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት፤ በኦሮሚያ ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰቱ ባሉበት አካባቢዎች የፀጥታ ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6544

በአፋር ክልል አርብቶ አደሮች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አለመሆናቸው ተገለጸ፤ ባለሥልጣናቱ በግዴታ ለማስለቀቅ አቅደዋል ተብሏል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 12/ 2017 ዓ.ም፦ በአፋር እና በኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት፤ “በአዋሽ እና ዱሌቻ ወረዳዎች ያሉ የተወሰኑ ነዋሪዎች በተለይም ከብቶቻቸው እና ንብረታቸው ላይ ስጋት ያላቸው የአርብቶአድር ማህበረሰቦች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አይደሉም” ሲል ገልጸ። በተባበሩት…
ፖሊስ የባለሀብቱን በመግደልና በማስገደል ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ፖሊስ አቶ ቢረሳው ምናለ ፈንታ የተባሉት ባለሀብትን በመግደልና በማስገደል ወንጀል የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ።
ፖሊስ ትናንት ባወጣው መግለጫ ባለሀብቱ ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ከስራ መልስ ወደ ቤታቸው በማምራት በራቸው ላይ ቆመው የመኪና ጥሩምባ እያሰሙ በር እስኪከፈትላቸው እየጠበቁ በነበረበት ወቅት ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ሦስት ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል፡፡
ከወንጀሉ ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ማንነትና ምንነት ለመለየትም ከአዲስ አበባ ሐዋሳ እስከ ሞያሌ ጫፍ የደረሰ መረጃና ማስረጃዎችን የማሰባሰብ ተግባር ተከናውኗል ብሏል።
በዚህም ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረውን መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለውን ግለሰብ እና አብዩ አይተነው ፈንታ ጨምሮ ለወንጀሉ መፈፀም አካባቢውን በመቆጣጠር ተሳትፎ የነበረውን አቶ ወርቁ መለሰ ካሴ የተባሉትን ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጌዴዎን ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ላይ በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከወንጀሉ መፈፀም በፊት በተቀነባባረ ሴራ በቂ ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የግድያ ወንጀሉን የፈፀመው መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለው ግለሰብ በህገ-ወጥ መንገድ በታጠቀው ማካሮቭ ሽጉጥ የአቶ አብዩ አይተነው ፈንታ የግል ጠባቂ ሆኖ ሲያገለግል እንደቆየ ተጠቁሟል።
በቀጣይም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚደረጉ የፍትህ ሂደቶች ውሳኔውን ተከታትሎ ለህዝብ እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ዜና: ባለፉት አምስት አመታት #የኢትዮጵያ አጠቃላይ ዕዳ የ25 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ፣ አጠቃላይ ዕዳ 69 ቢሊየን ዶላር ተጠግቷል
የኢትዮጵያ አጠቃላይ የመንግስት የውጭ እና የሀገር ውስጥ የዕዳ መጠን ባለፉት አምስት አመታት ብቻ 25 ነጥብ 3 በመቶ መጨመሩ ተጠቆመ፤ መንግስት ማስተማመኛ የሰጠባቸው (guaranteed debt) እና ማስተማመኛ ያልሰጠባቸው (non-guaranteed debt) ዕዳዎችን ጨምሮ የሀገሪቱ አጠቃላይ የዕዳ መጠን 68 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር መድረሱ ተገልጿል።
የዕዳ መጠኑ የሀገሪቱን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 32 ነጥብ 9 መሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ሪፖርት ያሳያል።
ከአጠቃላይ የዕዳ መጠኑ ውስጥ 59 በመቶ ወይንም 40 ቢሊየን ዶላሩ ከሀገር ውስጥ አበዳሪዎች የተገኘ መሆኑን የጠቆመው የገንዘብ ሚኒስቴሪ ሪፖርት ቀሪው 41 በመቶ ወይንም 28 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ ከውጭ አበዳሪዎች የተገኘ ነው ብሏል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6547

የ #ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ከ #ኢትዮጵያ እና ከ #ጂቡቲ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ቃል ገቡ
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሀመድ አብዱላሂ ኢሮ ከኢትዮጵያ እና ከጂቡቲ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ቃል ገቡ። ፕሬዝዳንቱ ግኙኝነቱ የሶማሊላንድ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ጸጥታ እና ቀጠናዊ ትብብርን በማጎልበት ረገድ ጠቀሜታ እንዳላቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንት ኢሮ እሁድ እለት በሀርጌሳ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ወሳኝ ጎረቤት እና የረጅም ጊዜ አጋር መሆኗን አሞግሰዋል። "ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየ ወዳጅና በኢኮኖሚ ልማት፣ በጸጥታ እና በአፍሪካ ውስጥ ግንኙነታችንን በማጠናከር ረገድ ወሳኝ አጋር ናት" ብለዋል። "ይህንን ግንኙነት እና የጋራ ጥቅሞቹን ማጎልበት ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው" ሲሉም አክለዋል።
በተጨማሪም ሶማሊላንድ ከጂቡቲ ጋር ያላትን የቀዘቀዘ ግንኙነት መልሶ ለመገንባት እና ከአሜሪካ ጋር ትብብርን ለምጠናከር ተስፋ እንዳላት ገልጸዋል። “በሶማሊላንድ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ካሳዩ ሁለት ሀገራት ማለትም ከጂቡቲ እና ከአሜሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት እናጠናክራለን" ማለታቸውን ሂራን ዘግቧል።
ባሳለፍነው አመት በሶማሊላንድ የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና በጠ/ሚ አብይ አህመድ( ዶ/ር) መካከል ለሶማሊላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ ደግሞ የባህር በር የሚያስገኝ የመግባባቢያ ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በስምምነቱ ደስተኛ ካልሆነችው ሶማሊያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት በቅርቡ በአንካራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የመግባቢያ ስምምነቱ ትግበራ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።
ከሶማሊያ ባለሥልጣናት በኩል ይህ የመግባቢያ ስምምነት እንደተሻረ ቢናገሩም ኢትዮጵያ እስካሁን በይፋ ያለችው ነገር የለም።

ዜና: #በአክሱም ትምህርት ቤቶች የተደረገውን የሂጃብ እገዳን በመቃወም #በመቀለ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የታደሙበት ሰልፍ ተካሄደ
ሰልፈኞቹ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲከበር ጠይቀዋል
ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሂጃብ ለመልበስ የሚያስችላቸውን መብት ያረጋግጣሉ የተባሉትን የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ መመሪያዎችን በመተግበር ረገድ እየታዩ ናቸው ያሏቸውን መለሳለስ በመቃወም ሰልፈኞቹ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
በሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ አደም አብዱልቃድር "ከአንድ አመት በፊት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃባቸውን ለብሰው ከህዝባቸው ጋር በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ አሁን ደግሞ ሂጃባቸውን ለብሰው ትምህርታቸውን መማር ይገባቸዋል" ብለዋል።
የክልሉ እስልምና ማህበረሰብ ተወካዮችም ሰልፉን ተከትሎ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፤ ፕሬዝዳንቱ ጉዳዩ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ እንዳሳዘናቸው ገልጸው ሂጃብ የለበሱ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መገለል እንደሌለባቸው የመንግስታቸውን አቋም አረጋግጠዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6551

በአክሱም ትምህርት ቤቶች የተደረገውን የሂጃብ እገዳን በመቃወም በመቀለ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የታደሙበት ሰልፍ ተካሄደ - Addis standard
ሰልፈኞቹ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲከበር ጠይቀዋል አዲስ አበባ፣ ጥር 13/ 2017፦ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የታደሙበት ሰልፍ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀለ ከተማ ተካሄደ። ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ሂጃብ ለመልበስ የሚያስችላቸውን መብት ያረጋግጣሉ…
በ #አዲስ_አበባ ከ88 ሺ በላይ ህገወጥ ማስታወቂያዎችን የለጠፉ ተቋማትና ሌሎች ደምቦችን የተላለፉ ግለሰቦች መቀጣታቸው ተገለጸ
በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት ከ27ሺ በላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች፣ ከ88 ሺ በላይ ህገ ወጥ ማስታወቂያዎችን የለጠፉ ተቋማት እና ከ2400 በላይ ህገወጥ ግንባታዎች ያከናወኑ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገለጸ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በእነዚህና በሌሎች ደንብ ጥሰቶች በተወሰደ እርምጃም ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸው፤ በቀጣይ የደንብ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ላይ ባደረገው ግምገማ ላይ የተገኙት አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው፤ በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ግንባታን የሚመጥን የህግና ህግ ማስከበር የሚችል ተቋም የመገንባት ስራው በትኩረት እየተሰራበት ነው ብለዋል።
ተቋሙ ከጊዜ ወደጊዜ የመፈጸም የማስፈፀም አቅሙ እየጨመረ መምጣቱን ያነሱት ቢሮ ሀላፊዋ፤ የደንብ ጥሰትን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር እያከናወነ ያለው” አበረታችና የከተማዋን የልማት እንቅስቃሴ የሚመጥን ነው” ብለዋል።
አክለውም በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚገኙ የመጠጥ፣ የጫት፣ የሺሻ ቤቶችና ሌሎችንም ህገወጥ ተግባር በማከናወን ላይ የሚገኙ ከ3400 በላይ ደንብ ተላላፊዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል። እየተከናወኑ የሚገኙ ህግ የማስከበር ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉም የቢሮ ሀላፊዋ አመላክተዋል።

ምክር ቤቱ በ #አፋር ክልል በርዕደ መሬት የተጓዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው ጥረት በቂ አለመሆኑን ገለጸ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአፋር ክልል በርዕደ መሬት የተጓዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው ጥረት በቂ አለመሆኑን ገልጿል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት እንዲሁም ከውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተውጣጣ ቡድን ይህን ያለው በአፋር ክልል በርዕደ መሬት የተጎዱ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ መመልከቱን ተከትሎ ነው።
የምክር ቤቱ አባላቱ ከሰብአዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ የመጠለያ፣ የምግብና ውሃ አቅርቦት እንዲሁም የጤና አገልግሎት አሰጣጥ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከተመለከቱ በኋላ፤ በቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች አመላክተዋል ተብሏል።
ለዜጎች የሚደረገው ድጋፍ መጠናከር እንዳለበትና በየደረጃው ያሉ የክልሉ አመራር ለጉዳዮ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የቡድኑ አባላት ማስገንዘባቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው፤ ጉዳቱ ቅፅበታዊ ድርጊት ቢሆንም በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን ለማገዝ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በአፋር ክልል በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ58 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ይታወቃል።

በ #የመን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ የ20 #ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ህይወት ማለፉን የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ገለጸ
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰ የጀልባ በመገልበጥ አደጋ 9 ሴቶች እና 11 ወንዶች ጨምሮ 20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ።
አደጋው የተከሰተው ቅዳሜ ምሽት በጣይዝ አስተዳደር አል-ሀጃጃህ አቅራቢያ ሲሆን በሕይወት የተረፉ ሰዎች ወደ ባህር ዳርቻ ለመድረስ እንደቻሉ ድርጅቱ ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ጀልባው 35 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመን ካፒቴን እና ረዳት ጋር አሳፍሮ ከ #ጅቡቲ ሀማርታ አካባቢ በመነሳት "በጠንካራ ወቅታዊ ነፋስ መካከል" ሲጓዝ እንደነበርም ድርጅቱ ገልጿል። የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በመን ተልዕኮ ኃላፊ የሆኑት አብዱስታቶር ኤሶቭ ክስተቱን "ስደተኞች የሚገጥሟቸውን አሳዛኝ ሁኔታዎች የሚያስታውስ" በማለት የገለጹ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ "የኢ-መደበኛን ፍልሰት ዋና መንስኤዎች" እንዲፈታ እና የስደተኞችን ክብር እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
ከወራት በፊት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከ #የመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸው እና ሌሎች 100 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁ ይታወሳል።
በተጨማሪም ባሳለፍነው አመት ሚያዚያ ወር 77 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳፍራ ከየመን ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ 21 ሰዎች ሞተዋል።

ዜና: ቋሚ ኮሚቴው ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው 13 ቢሊየን ብር ድጎማ ለታለመለት አላማ ማዋሉን ለማረጋገጥ የመስክ ምልከታ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ
#የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስቱ በድጎማ የተሰጠውን 13 ቢሊየን ብር ለታለመለት አላማ ማዋሉን ለማረጋገጥ የመስክ ምልከታ እያደረኩ ነው ሲል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።
የክልሉ የኢኮኖሚ ቢሮ ሃላፊዎች “ለሰሜኑ ጦርነት ለተጎዱ መቋቋሚያ የተመደበው 20 ቢሊዮን ብር እስካሁን አልተለቀቀም” ሲሉ ቅሬታ ማቅረባቸውን ያመላከተው የምክር ቤቱ መረጃ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ በሰጡት ምላሽ “ለሰሜኑ ጦርነት ለተጎዱ መቋቋሚያ የተመደበው 20 ቢሊዮን ብር ሶስት ጊዜ መፅደቁን አስታውሰው ገንዘቡ ተለቆ” የህዝቡን ችግር መፍታት አለበት ማለታቸውንም አካቷል።
በተጨማሪም የ 17 ወራት የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ አለመከፈሉ ሰራተኛውን አስተባብሮ ለማሰራት ፈተና እንደሆነባቸው፣ ከማህበራዊ ዋስትና ጋር በተያያዘ እድሜያቸው ለጡረታ የደረሱ ሰዎች የ 17 ወራት ካልተከፈለ ጡረታ መውጣት አይቻልም በመባሉ ሰዎች ለችግር እየተጋለጡ መሆናቸውን” የክልሉ ሃላፊዎች ተናግረዋል ብሏል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6554

ቋሚ ኮሚቴው ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው 13 ቢሊየን ብር ድጎማ ለታለመለት አላማ ማዋሉን ለማረጋገጥ የመስክ ምልከታ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 14/2017 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስቱ በድጎማ የተሰጠውን 13 ቢሊየን ብር ለታለመለት አላማ ማዋሉን ለማረጋገጥ የመስክ ምልከታ እያደረኩ ነው ሲል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ። ለክልሉ ለ2017 በጀት አመት የተሰጠው ድጎማ የስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ለመመልከት እና ድጎማው ለታለመለት አላማ…