Addis Standard Amharic
17.9K subscribers
4.88K photos
123 videos
3 files
3.88K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
#በፎቶ፡ በ #አፋር ክልል በተለይ በ #አዋሽ እና #ዱለቻ ወረዳ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉ አስገድዷል።

ተፈናቃዮቹ እየተደረገላቸው ያለው የውሃ እና የምግብ እርዳታ በመጠለያ ጣቢያው ካሉ የተፈናቃዮች ብዛት አንጻር በቂ አይደለም አለመሆኑን ይገልጻሉ። የውሃ እጥረት ዋነኛው ችግር ሲሆን በተሽከርካሪዎች የሚቀርብላቸው የውሃ አቅርቦት ከተቋረጠ በኋላ ባልታከመ የወንዝ ውሃ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው በበሽታ የመያዝ ስጋትን ጨምሯል።

በክልሉ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከሰም ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ በርካታ መኖሪያ ቤቶችን እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በዚህም 4 ሺህ የከሰም ሱካር ፋብሪካ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ58 ሺህ በላይ ሰዎች ጊዜያዊ መጠለያ ገብተው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑም ክልሉ አስታውቋል።

ፎቶ፡ ለአዲስ ስታንዳርድ (ከአሚበራ ወረዳ ዳኢዶ የመጠለያ ጣቢያ)
መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አስመጪዎች ሥራቸውን ከመጀመራቸው በፊት የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን እንዲያዘጋጁ አሳሰበ

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አስመጪዎች እና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ኃይል መሙያ ጣቢያዎችን እንዲያዘጋጁ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መመሪያ አስተላለፈ።

በሚኒስቴሩ መረጃ መሠረት በአሁኑ ሰዓት ከ400 በላይ ኩባንያዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣት እና በማከፋፈል ላይ ይገኛሉ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ በርኦ ሀሰን ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል አብዛኞቹ ቀድሞውኑ የመሙያ ጣቢያዎችን ማዘጋጀታቸውን ገልጸው “ሁሉም አካላት ተገቢ የሆነ የይል መሙያ መሠረተ ልማት እንዳላቸው ማረጋገጥ አለባቸው” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ ደስታ በበኩላቸው በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አክለውም በመዲናዋ የሚገኙ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

በቅርቡ ከነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን ፈቃድ በመውሰድ በተቋም ደረጃ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል መሙያ ማሽን (ቻርጀር) መትከል የሚፈቅድ መመሪያ መጽደቁ ይታወሳል።

መመሪያው በመንገዶች ግራና ቀኝ በየ50 ኪሎሜትር ልዩነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መሙላት የሚችል ፈጣን ቻርጀር ጣቢያ ማቋቋም ይፈቅዳል።
ዜና፡ በ #አፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ተፈናቅለው በተጨናናቀ መጠለያ የሚገኙ ዜጎች በቂ ውሃና ምግብ እየቀረበላቸው አለመሆኑን ገለጹ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለሳ ወረዳ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተከትሎ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ነዋሪዎች እየቀረበላቸው የሚገኘው እርዳታ በቂ አለመሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

“ያለው የሰው ብዛት እና የሚመጣው እርዳታ ተመጣጣኝ አይደለም። የውሃ ችግር በጣም አለ። የሮቶ ውሃ ነበረ የምንጠቀመው እሱ ካለቀ በኋላ ሰው የወንዝ ውሃ ነው እየተጠቀመ ያለው አሁን ላይ። ይህም ለበሽታ ተጋላጭ እንዳያደርገን ስጋት አለን።" ሲሉ አቶ ፈኪር አህመድ የተባሉ ተፈናቃይ ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ ከመጠጥ ውሃ በተጨማሪ ለመጠለያ የሚውል ሸራ፣ ፍራሽ፣ የምግብ ማብሰያ ግብዓቶች እና ሌሎች የአቅርቦት ችግር መኖሩን ያስረዳሉ።

ሙሉ ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6516
ዜና፡ በ #አክሱም ከተማ የሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶች በቀረቡባቸው ክሶች ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዙ

የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅሬታ ማቅረቡን ተከትሎ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የከለከሉትን አምስት ትምህርት ቤቶች በቀረቡባቸው ክሶች ላይ ምላሽ እንዲሰጡ አዘዘ።

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአክሱም ከተማ 159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሃይማኖታዊ ልብሳቸው ምክንያት ትምህርት ቤት እንዳይገቡ መታገዳቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶቹን ከሷል።

አቤቱታውን የተመለከተው የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የሚከለክለውን መመሪያ በተማሪዎች ላይ "ሊመለስ የማይችል የመብት ጥሰት" ሊያስከትል እንደሚችል ገልጾ ታግዶ እንዲቆይ ወስኗል።

ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6527
#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል በታጣቂዎችና ሚሊሻዎች መካከል በተከፈተ ተኩስ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተክል ዞን ቡለን ከተማ፣ በ #ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎችና በክልሉ ሚሊሻዎች መካከል በተከፈተ ተኩስ የሰው ሕይወት መጥፋቱን የከተማው ነዋሪዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ፡፡

የክልሉ ነዋሪዎች "የሸኔ ኃይሎች" በማለት ወደ የጠሯቸው የኦነስ ታጣቂዎች በመተከል ዞን በቡልን ከተማ "ባንክ ለመዝረፍ" ባደረጉት ሙከራ በወረዳው የሚታወቁ የአገር ሽማግሌ መገደላቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ከ200 በላይ የሚደርሱ የሸኔ ታጣቂዎች፣ 34 ኪሎ ሜትር ርቀት በማቋረጥ ቡለን ከተማ ላይ የሚገኘውን የ #ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመዝረፍ ሙከራ አድርገዋል ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የቡለን ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል።

የክልሉ ሚሊሻዎች ካምፕና ባንኩ ጎን ለጎን በመሆኑ፣ ከጥበቃዎች ጋር በመሆን ዝርፊያውን ሊከላከሉት ችለዋል ብለዋል።

በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከታጣቂ ቡድኑ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ፣ በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት አለመድረሱን ጠቁመዋል፡፡

ታጣቂዎቹ በሚመለሱበት ወቅት "የእጅ ስልኮችንና ሌሎች ንብረቶችን እየቀሙ" መሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን ያረጋገጡት የቦሮ ዴሞክራቲክስ ፓርቲ አባልና የሕዝብ ተወካዮች አባል የሆኑት መብራቱ ዓለሙ (ዶ/ር) ታጣቂዎቹ በዞኑ በተለይም ድባጤ ወረዳ አብዛኛዎቹን ቀበሌዎች ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
#አሜሪካ#ሱዳን የጦር አዛዥ አአል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ ጣለች

አሜሪካ የሱዳን የጦር አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትንና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የተፈናቀሉበትን የእርስ በእርስ ጦርነት በማባባስ ከሳለች። የአሜሪካ ግምዣ ቤት፤ የቡርሃን አመራር የሲቪል መሰረተ ልማትን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች፣ በገበያዎች እና በሆስፒታሎች ላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን እንዲሁም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ግድያ መፈጸማቸውን ገልጿል።

በዚህም ትናልንት በአልቡርሃን ላይ ማዕቀብ የተጣለ ሲሆን ይህም የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ በሆኑት ሞሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ከተወሰደ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።

"የቡርሃን አመራር ሰራዊት ከድርድር ይልቅ ጦርነትን መርጧል" ያለው የአሜሪካ ግምጃ ቤት፤ እርምጃው ከቡርሃን ጋር የተያያዙ የአሜሪካን ንብረቶች በሙሉ እንደሚያግድ እና አሜሪካውያን ከእሳቸው ወይም ከተዛመጅ አካላት ጋር እንዳይገናኙ የሚከለክል መሆኑንም አክሎ ገልጿል።

በተጨማሪም ዋሽንግተን የሱዳን-ዩክሬን ዜግነት ያላቸውን እና በሆንግ ኮንግ የሚገኘውን ኩባንያ ጨምሮ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎችን ለሱዳን ጦር መሳሪያ በሚያቀርቡ አካላት ላይም ትኩረት አድርጋለች።

የቡርሃን በአልጀዚራ በተላለፈው ንግግራቸው “እቺን ሀገር ለማገልገል ማንኛውንም ማዕቀብ እንቀበላለን" ሲሉ ተደምጠዋል። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የአሜሪካን እርምጃ "ግራ የሚያጋባ እና ደካማ የፍትህ ስሜት" ሲል ተችቷል።
#ፌዴራል_ፖሊስ በዋናው መስሪያ ቤቱ ያደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል አስመረቀ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በዋናው መስሪያ ቤቱ ያደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል በትናንትናው እለት ስራ አስጀመረ። በተጨማሪም ኮማንድ ኮንትሮል ያለው ዘመናዊ መንገድ የሚዘጋ ተሸከርካሪም ተመርቆ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል ተብሏል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከሉ አዲስ የገቡት ድሮኖች ከከተማ ፀጥታ ቁጥጥር ባሻገር የቦርደር ሴኪዩሪቲን ጨምሮ የኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችል ዕድል የሚፈጥሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ በሀገሪቱ ፖሊስ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነው የድሮን ቴክኖሎጂ ማዕከል፤ ወጣት የፖሊስ ኦፊሰሮች የቴክኖሎጂ ስልጠና አግኝተው የተሻለ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈጠረ ነው ሲል ጠቅሰው አሁን ላይ በተቋሙ ያለው የድሮን አቅም በፖሊስ የወንጀል መከላከል ሰርቪላንስ እና የምርመራ ስራ ከፍተኛ እገዛ አለው ብለዋል።

በተጨማሪም እንደ አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ያሉ መድረኮች ሲኖሩ ለተወሰነ ጊዜ መንገዶችን ዘግቶ ቪአይፒዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል የራሱ የሆነ ኮማንድ ኮንትሮል ያለው ዘመናዊ ሮድ ብሎክ (መንገድ የሚዘጋ) ተሸከርካሪም ተመርቆ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል ተብሏል፡፡

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02zdynN9ckoLC9nzty6Z7BKVzhYzUyNmLLrgGkp55imWx7BrvfJKGJcNLjgR8fAXAzl
ምርጫ ቦርድ የአሰራር ሂደት ላይ ግልፅኝነት ለማስፈን እንዲያግዝ የምርጫ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ እንዲጸድቅ መከረ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርዱ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ማሻሻያ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ቦርዱ አዋጆች ሁሉንም አሳታፊ እና ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት አመቺ እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።


“የአዋጁ ማሻሻያም ቦርዱ ይበልጥ ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ፍትሐዊ እና ታማኝ እንዲሆን እንደሚያስችለው” አክለው ገልጸዋል ሲል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ቦርዱ “ዓለም ዓቀፍ የአሰራር መለኪያዎችን ያሟሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ አሠራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ” መሆኑንም ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። ይህም የምርጫ ቦርድ የአሰራር ሂደት ላይ ግልፅኝነት ለማስፈን እንደሚያግዝ አመላክተዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2019 የተደነገገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ህወሐትን ጨምሮ የታገዱ ፓርቲዎችን ዳግም ህጋዊ ሆነው እንዲመዘገቡ ለማስቻል ባሳለፍነው አመት ግንቦት ወር መሻሻሉ ይታወቃል።
ዜና፡ #ኢትዮጵያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 “አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት” እንዳጋጠማት ሂማን ራይትስ ዎች አስታወቀ

አለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆሪቋሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ኢትዮጵያ “መጠነ ሰፊ ግጭቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት እገዳዎች” ማስተናገዷን በመጥቀስ የሰብዓዊ መብት ሁኔታውን “አስከፊ” ሲል ገልጾታል።

ድርጅቱ አዲስ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፤ ግጭት ባለበት አካባቢዎች እና በሀገሪቱ ሌሎች ስፍራዎች በመንግስት የጸጥታ አካላት፣ በሚሊሻዎች እና በታጣቂ ቡድኖች ከባድ ጥሰቶችን መፈፀማቸውን አመልክቷል። በተለይም በአማራ ክልል ያለው ግጭት አሳሳቢ መሆኑን ገልጾ በመንግስት የጸጥታ አካላት እና በፋኖ ታጣቂዎች “የጦር ወንጀል” ድርጊቶች መፈጸማቸውን ገልጿል።

ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6533
ዜና፡ #ኢትዮጵያ#አፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷን ሲፒጄ ገለጸ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በከፋ ሁኔታ ከሚያስሩ ሀገሮች መካከል መካተቷንና በእስር ላይ ካሉ ስድስት ጋዜጠኞች መካከል አምስቱ የሞት ቅጣት ሊያስከትል የሚችል የ"ሽብርተኝነት" ክስ ተመስርቶባቸዋል ሲል የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ትናንት ሐሙስ ዕለት ይፋ ባደረገው የ2024 የጋዜጠኞች እስር ሪፖርት አስታውቋል።

የእስር እርምጃዎቹ የተወሰዱት በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት ጋር የሚገጣጠም መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ፤ ባለሥልጣናቱ "የጦር መሣሪያ የታጠቁ ቡድኖችን እና ደጋፊዎቻቸውን" ለማጥፋት በሚያደርጉት ዘመቻ "ሲቪሎችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ ምሁራንን እና ጋዜጠኞችን" ዒላማ አድርገዋል ብሏል።

ሲፒጄ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋዜጠኞችን ለማሰር "ብዙውን ጊዜ ግልጽ ያልሆኑ የሽብርተኝነት ወይም የጽንፈኝነት ክሶችን" ይጠቀማሉ።

ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6538
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 250 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እንዲለቀቅ የሚያስችል ግምገማን አጸደቀ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በአራት አመታት የተራዘመ ብድር ለ #ኢትዮጵያ ለመስጠት ከፈቀደው የ3.4 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ሁለተኛው ዙር የ250 ሚሊየን ዶላር ብድር እንዲለቀቅ የሚያስችል ግምገማን አጸደቀ።

ቦርዱ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፋይናንስ ፕሮግራም ሁለተኛ ግምገማ ያደረገ ሲሆን ይህም 250 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እንዲለቀቅ መንገድ ከፋች ነው ተብሏል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሪፎርም ፕሮግራሙ ከታሰበው የተሻለ ውጤት እንዳስመዘገበ መሆኑን እና የዋጋ ግሽበት ጫና እንደሚጨምር የተገመተው እለመከሰቱን ገልጿል።

በተጨማሪም ጠንካራ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከታቀደው በበለጠ ፍጥነት እያደገ እንደሚገኝ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋር 3.4 ቢሊዮን ዶላር ለአራት ዓመታት የሚቆይ የፋይናንስ ድጋፍ ፕሮግራም ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል። የመጀመሪያው 345 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም መለቀቁ ይታወሳል።

ስምምነቱ ላይ የተደረሰው ኢትዮጵያ ገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት መከተልን ጨምሮ ሰፋፊ የሆኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ማድረጓን ተከትሎ ሲሆን የብድር ስምምነቱ የሀገሪቱን የዕዳ አወቃቀር ለማሻሻል እንደሚያግዛት ተመላክቷል።

==
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ዕውቅና ይሰጡኛል በሚል #ሶማሊላንድ አይኗን ወደ #አሜሪካ መለሰች

#ኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ለመስጠት እና በምላሹም ዕውቅና ለማግኘት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈርማ የነበረችው ሶማሊላንድ ወደ አሜሪካ እያማተረች ነው።

በርካታ ሶማሊላንዳውያን ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለባለፉት 33 ዓመታት ሶማሊላንድ ስትናፍቀው የነበረውን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ አገር ዕውቅና የማግኘት ህልሟን እውን ያደርጉታል በሚል ተስፋን ሰንቀዋል።

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በተደረሰው የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና አገኛለሁ የሚል ተስፋ ነበራት። ሆኖም በዚህ የመግባባቢያ ስምምነት ቁርሾ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያና ሶማሊያ በቅርቡ ልዩነታቸውን ለመፍታት በአንካራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የመግባቢያ ስምምነቱ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

ከሶማሊያ ባለሥልጣናት በኩል ይህ የመግባቢያ ስምምነት እንደተሻረ ቢናገሩም ኢትዮጵያ በይፋ ያለችው ነገር የለም።

"ዶናልድ አዳኛችን ነው። ብልህ እና የተግባር ሰው ነው። አምላክ አሜሪካን ይባርክ" ስትል የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነችው አይሻ ኢስማኤል ዕውቅና እናገኛለን በሚል ተስፋ ድምጿ በደስታ ተሞልቶ ለቢቢሲ ተናግራለች።

በሶማሊላንድ መዲና ሐርጌሳ ነዋሪ ለሆነችው አይሻ ይህ ዕውቅና የማግኘት ተስፋ ደስታን የሚያመጣ ቢሆንም በተቃራኒው ለሞቃዲሾ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ትላለች።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cy4mme0j8jmo
#እስራኤል ካቢኔ የጋዛውን ተኩስ አቁም ስምምነት አጸደቀ

የእስራኤል ካቢኔ የጋዛውን ተኩስ አቁም ስምምነት በ24 ድጋፍ በ8 ተቃውሞ አጸደቀ። 15 ወራቱ ያቆጠረውን የእስራኤል እና ሀማስ ታጣቂዎች ጦርነት ያስቆማል የተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት ለ6 ሰአታት ከፈጅ ውይይት በኋላ ጸድቋል።

በእስራኤል ጥምር መንግስት ውስጥ የገንዘብ ሚኒስትሩ እና የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ስምምነቱን አጥበቀው ከተቃወሙ የካቤኔ አባላቶች መካከል ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ታጋቾች የሚመለሱበትን እና የጋዛው ጦርነት የሚቆምበትን የተኩስ አቁም ስምምነት መንግስት አጽድቋል ሲል አስታውቋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰበት ረቡዕ ጀምሮ በጋዛ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ከፍተኛ ጥቃቶችን ማድረሳቸውን ቀጥለዋል መባሉን አላይን ዘግቧል፡፡

ምንም እንኳን ስምምነቱ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢጠበቅም ቅዳሜ ማለዳ የእስራኤል የአየር ጥቃት ከካን ዮኒስ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ማዋሲ አካባቢ በሚገኝ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ አምስት ሰዎችን መግደሉን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
#ህወሓት ጠቅላል ጉባዔ እንዲያካሂድ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ቀነ ገደብ እንደማይቀበልና መንግስት"የ #ፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ እንዳይተገበር እንቅፋት መሆኑን” ገለጸ

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ የ #ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ጠቅላል ጉባዔ እንዲያካሂድ ቀነ ገደብ መሰጠቱን እንደማይቀበል አስታወቀ።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ያደረገው ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ “ ህወሓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔ ዛሬ ይሁን ነገ አይቀበልም" ሲል ገልጿል።

ህወሓት ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም “በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ” መመዝገቡ ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።

ይሁን እንጂ ቦርዱ ፓርቲው ለጠቅላላ ጉባዔው ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ምንም ምልክት እንደሌለው ገልጾ፣ በቦርዱ የተላለፉትን ውሳኔዎች በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ሕጉን መሠረት ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02UWHpn6EVweTnUkLskJMSmz2x4L6QcktuPPMCeRF2xZ8LUV5T7uhzAUkBMGexu9HRl
ካለፈው አመት የመጀመሪያ አጋማሽ ጋር ሲነጻጸር 59 በመቶ ብልጫ ያለው ገቢ ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና ተገኘ

በያዝነው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ለውጭ ገበያ ከቀረበ 204 ሺህ 206 ነጥብ 63 ቶን የቡና ምርት 908 ነጥብ 47 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ ሻፊ ኡመር ዛሬ በሰጡት መግለጫ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገቢ ደረጃ የ337 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 59 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል።

አፈጻጸሙም የ86 ሺህ 251 ነጥብ 17 ቶን ወይም 73 በመቶ ብልጫ አለው ማለታቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ 133 ሺህ 63 ነጥብ 49 ቶን የቡና ምርት በመላክ 714 ነጥብ 99 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ንዑስ ዘርፍ ለማግኘት የታቀደውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ገቢ ለማሳካት ዝርዝር ዓመታዊ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱንም አመላክተዋል፡፡
ዜና: “#በህወሓት አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” - አቡነ ማትያስ

በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል የሚያጨልም ነው ሲሉ #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጻጻስ የሆኑት አቡነ ማትያስ ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና ለግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ገለጹ።

“ሁኔታዎች ከግዜ ወደ ግዜ እየከፋ፤ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል ሊያጠፋ ወደሚችል ሁኔታ እያመራ ይገኛል፤ ይህንን እያየን ዝምታን መምረጥ በሰውና በፈጣሪ የሚያስጠይቅ በመሆኑ ይህንን የምክር ደብዳቤ ለመጻፍ ተገድጃለሁ” ብለዋል።

ፓትርያርኩ በደብዳቤያቸው ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለመወያየት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካላቸው በመጠቆም ደብዳቤውን ለመጻፈ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።

“በእልክ እኔ እሻላለሁ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን፣ እኔ ብቻ ነኝ ለህዝብ የማስበው በሚል በተፈጠረው ውስብስብ ችግር የሚያዝን እንጂ የሚደሰት ህዝብ የለም” ሲሉ ጠቁመዋል።

“በአመራሩ መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዳይበቃ በአንድነት ተስማምቶ ሲኖር በነበረው ህዝብ መካከልም ተጽእኖው እየወረደ ይገኛል” ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6542
ዜና፡ በ#አፋር ክልል አርብቶ አደሮች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አለመሆናቸው ተገለጸ፤ ባለሥልጣናቱ በግዴታ ለማስለቀቅ አቅደዋል ተብሏል

በአፋር እና በ#ኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት፤ "በአዋሽ እና ዱሌቻ ወረዳዎች ያሉ የተወሰኑ ነዋሪዎች በተለይም ከብቶቻቸው እና ንብረታቸው ላይ ስጋት ያላቸው የአርብቶ አድር ማህበረሰቦች ወደ ሌላ ቦታ ለመዘዋወር ፈቃደኞች አይደሉም" ሲል ገልጸ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት መሠረት፤ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አደጋ ካለባቸው አካባቢዎች ለማስወጣት አስገዳጅ እርምጃዎችን ለመውሰድ እያሰበ ነው።

ከአያኤኤሲ ክላስተር አስተባባሪዎች እና አጋሮች ድጋፍ በተዘጋጀው አዲስ መረጃ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት፤ በኦሮሚያ ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰቱ ባሉበት አካባቢዎች የፀጥታ ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6544
ፖሊስ የባለሀብቱን በመግደልና በማስገደል ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ አቶ ቢረሳው ምናለ ፈንታ የተባሉት ባለሀብትን በመግደልና በማስገደል ወንጀል የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ።

ፖሊስ ትናንት ባወጣው መግለጫ ባለሀብቱ ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ከስራ መልስ ወደ ቤታቸው በማምራት በራቸው ላይ ቆመው የመኪና ጥሩምባ እያሰሙ በር እስኪከፈትላቸው እየጠበቁ በነበረበት ወቅት ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ሦስት ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል፡፡

ከወንጀሉ ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ማንነትና ምንነት ለመለየትም ከአዲስ አበባ ሐዋሳ እስከ ሞያሌ ጫፍ የደረሰ መረጃና ማስረጃዎችን የማሰባሰብ ተግባር ተከናውኗል ብሏል።

በዚህም ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረውን መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለውን ግለሰብ እና አብዩ አይተነው ፈንታ ጨምሮ ለወንጀሉ መፈፀም አካባቢውን በመቆጣጠር ተሳትፎ የነበረውን አቶ ወርቁ መለሰ ካሴ የተባሉትን ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጌዴዎን ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ላይ በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከወንጀሉ መፈፀም በፊት በተቀነባባረ ሴራ በቂ ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የግድያ ወንጀሉን የፈፀመው መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለው ግለሰብ በህገ-ወጥ መንገድ በታጠቀው ማካሮቭ ሽጉጥ የአቶ አብዩ አይተነው ፈንታ የግል ጠባቂ ሆኖ ሲያገለግል እንደቆየ ተጠቁሟል።

በቀጣይም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚደረጉ የፍትህ ሂደቶች ውሳኔውን ተከታትሎ ለህዝብ እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡