የ #አውሮፓህብረት ለ #ኢትዮጵያ ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱን ገለጸ
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ "ግጭቶች፣ ተደጋጋሚ የአየር ንብረት ለውጦች እና ተላላፊ በሽታዎች" ያሳደሩትን ተፅእኖ በመጥቀ በጎርጎሮሳውያኑ 2025 ዓ.ም 40 ሚሊዮን ዩሮ የመጀመሪያ የሰብአዊ እርዳታ ለመመደብ ማቀዱን አስታውቋል።
ይህ ድጋፍ ከ2020 ጀምሮ ለኢትዮጵያ የተደረገውን አጠቃላይ የሰብዓዊ ድጋፍ 436.5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያደርሰውም ገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት እንደገለፀው ድጋፉ፤ "የጥበቃ፣ የምግብ እርዳታ፣ ንጹህ ውሃ እና ንፅህና፣ መጠለያ እና የተመጣጠነ ምግብ እርዳት" አቅርቦትን በማድረስ ረገድ የበጎ አድራጎት አጋሮችን ይደግፋል። በተጨማሪም በሽታዎችን መከላከል፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ጥበቃ እና በቀውሶች ለተጎዱ ህጻናት ትምህርትም እንደሚውልም ተገልጿል።
እርዳታው ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና በተለይም እንደ ሱዳን ካሉ ጎረቤት ሀገራት አዲስ ለስደተኞች ሰዎች በቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን የገለጸው የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ለማሟላት ያለውን ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥቷል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ “ተገቢ ያልሆነ” ሰልፎችን የሚፈጥሩ ማደያዎችን "በፍጹም እንደማይታገ" እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ “ተገቢ ያልሆነ” ሰልፎችን የሚፈጥሩ ማደያዎችን "በፍጹም እንደማይታገ" ና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ትናንት ጥር 6/2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፤ ነዳጅን በጥሬ ገንዘብ ሽያጭ የሚፈጽሙ፣ የነዳጅ እጥረትን በሚፈጥሩ እና የ24 ሰዓት አገልግሎት በማይሰጡ መሰል ድርጊቶች ላይ በሚሳተፉ ማደያዎች ላይ እርምጃዎች እንደሚወሰድ አሳስበዋል፡፡
ኃላፊዋ ናፍጣ በከተማዋ 125 ማደያዎች ቀርቦ በመሰራጨት ላይ በአማካኝ በቀን 2 ሚሊዮን ሊትር፣ ቤንዚን በአማካኝ በቀን 1.45 ሚሊዮን ሊትር በድምሩ ባለፉት ስድስት ወራት በቀን በአማካኝ 3.45 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ በበቂ መጠን መቅረቡን አመላክተዋል፡፡
“በከተማዋ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ምንም አይነት የነዳጅ እጥረት እንዳልነበር” አክለው ገልጸዋል።
በቁጥጥር ሂደት ህገ-ወጥ ተግባር ውስጥ የገቡ ነዳጅ ማደያዎች ላይም እርምጃ መወሰዱን ያስታወሱት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በዚህም በህገ-ወጥ ሲዘዋወር የተወረሰ 47608.5 ሊትር ነዳጅ ምርት ተሽጦ 2,600,649.94 ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉም አውስተዋል፡፡

አገልግሎቱ በስድስት ወራት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንና ከ13 ሺህ በላይ ዜጎች ላይ እርመጃ መውሰዱን አስታወቀ
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፋት ስድስት ወራት 10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከ16 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በሐሰተኛና በተጭበረበሩ የጉዞ ሰነዶች አገልግሎት ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 13,322 ዜጎች ላይ አሰተዳደራዊ ርምጃ መወሰዱንም ገልጸዋል።
ከ721 ሺህ 623 በላይ ፓስፖርቶችን የማተም ስራ ተሰርቷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ከታተመው 98 በመቶው ለተገልጋዮች ተሰጥቷል ብለዋል።
ለ14 ሺህ 367 ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የመስጠት ስራ መከናወኑንና በዚህም ለ20 ግለሰቦች ዜግነት እንደተሰጣቸውም አብራርተዋል። ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሠው ሀይሉን የማጠናከር፤ አሰራሩን በቴክኖሎጂ የማገዝ ስራ ይሰራልም ብለዋል።
አገልግሎቱ በ2016 በጀት ዓመት የሰበሰበው ገቢ 14 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ሲሆን ለ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ተገልጋዮች ፓስፖርት መሰጠቱም ይታወሳል።

'መስፈርት አላሟሉም' በሚል 400 የሚሆኑ ሠራተኞች ከሥራ ተባረሩ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት "በድልድል እና ምደባ" 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከጥር ጀምሮ ከሥራ ማሰናበቱን ሠራተኞች እና ድርጅቱ ተናገሩ።
በ2015 ዓ.ም. "የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት" በሚል ከ70 ዓመታት በላይ ለአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አንበሳ ባስ እና ሸገር ብዙኃን ትራንስፖርት ተዋህደው የልማት ድርጅት ተመሥርቷል።
ይህን ተከትሎ "ሪፎርም" ማድረግ የጀመረው ድርጅቱ፤ ባከናወነው ድልድል እና ምደባ ሠራተኞች "ያለአግባብ" እና "በዘፈቀደ" ከሥራ ተባረናል ሲሉ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት የብቃት ፈተና እና ውድድር ያላለፉ ሠራተኞችን ከሥራ መቀነሱን በመግለፅ "የሪፎርም ባሕሪ ነው" ሲል ለቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥቷል።
ለሠራተኞቹ መመሪያውን ሲያስተዋውቅ የብቃት ፈተና ሰጥቶ ፈተናውን ባያልፉ እንኳ አንድ የደረጃ እርከን ዝቅ ተደርገው ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ መተማመኛ መስጠቱን ተናግረዋል።
ተቋሙ ይህን ቢልም ፈተናውን ያለፉም ያላለፉም፤ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ያላቸው ሠራተኞችን "ያለምንም ማስጠንቀቂያ" ከሥራቸው እንዳባረረ ስድስት ሠራተኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከሥራ የተሰናበቱት ሠራተኞች ከፅዳት እና የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ በተቋሙ ለአስርት ዓመታት ያገለገሉ እና የጡረታ ዕድሜያቸው የተቃረቡ ሠራተኞችም እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cly5757l54go

ዜና፡ በ #ምስራቅ_ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ሁለት ወጣቶች “በሚሊሻዎች” መገደላቸውን የቤተሰብ አባላት ተናገሩ
በ #ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ/ም ከማያ ከተማ ሞተር ሳይክል ገዝተው ወደ ጉራዋ ወረዳ በመመለስ ላይ የነበሩ ሁለት ወጣቶች “በጸጥታ ኃይሎች” በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
ግድያው የተፈጸመባቸው ወጣቶች ከዲሬ ሹኢቤ እና ጃፋር አብዱራዛቅ የተባሉ የጉራዋ ወረዳ ላፍቶ ቀበሌ ነዋሪ እንደሆኑ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
“ሚሊሻዎቹ በጥይት ካቆሰሏቸው በኋላ እዚያው ተተዋቸው እንደሄዱ” የተናገሩት የቤተሰቡ አባሉ፤ “በኋላም የአካባቢው ማህበረሰብ አምቡላንስ ጠርቶ ወደ ጉራዋ ሆስፒታል ቢወስዳቸውም ሊተርፉ አልቻሉም” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል።
ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6510

Addis standard
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ሁለት ወጣቶች "በሚሊሻዎች" መገደላቸውን የቤተሰብ አባላት ገለፁ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 7/ 2017 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ/ም ከማያ ከተማ ወደ ጉራዋ ወረዳ በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ የነበሩ ሁለት ወጣቶች “በጸጥታ ኃይሎች” በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ቤተሰቦቻቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። ግድያው የተፈጸመባቸው ወጣቶች ከዲሬ ሹኢቤ እና ጃፋር አብዱራዛቅ የተባሉ የጉራዋ ወረዳ ላፍቶ ቀበሌ ነዋሪ እንደሆኑ…
#በፎቶ፡ በ #አፋር ክልል በተለይ በ #አዋሽ እና #ዱለቻ ወረዳ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉ አስገድዷል።
ተፈናቃዮቹ እየተደረገላቸው ያለው የውሃ እና የምግብ እርዳታ በመጠለያ ጣቢያው ካሉ የተፈናቃዮች ብዛት አንጻር በቂ አይደለም አለመሆኑን ይገልጻሉ። የውሃ እጥረት ዋነኛው ችግር ሲሆን በተሽከርካሪዎች የሚቀርብላቸው የውሃ አቅርቦት ከተቋረጠ በኋላ ባልታከመ የወንዝ ውሃ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው በበሽታ የመያዝ ስጋትን ጨምሯል።
በክልሉ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከሰም ስኳር ፋብሪካን ጨምሮ በርካታ መኖሪያ ቤቶችን እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።
በዚህም 4 ሺህ የከሰም ሱካር ፋብሪካ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ58 ሺህ በላይ ሰዎች ጊዜያዊ መጠለያ ገብተው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑም ክልሉ አስታውቋል።
ፎቶ፡ ለአዲስ ስታንዳርድ (ከአሚበራ ወረዳ ዳኢዶ የመጠለያ ጣቢያ)

መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አስመጪዎች ሥራቸውን ከመጀመራቸው በፊት የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን እንዲያዘጋጁ አሳሰበ
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አስመጪዎች እና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ኃይል መሙያ ጣቢያዎችን እንዲያዘጋጁ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መመሪያ አስተላለፈ።
በሚኒስቴሩ መረጃ መሠረት በአሁኑ ሰዓት ከ400 በላይ ኩባንያዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣት እና በማከፋፈል ላይ ይገኛሉ።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ በርኦ ሀሰን ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል አብዛኞቹ ቀድሞውኑ የመሙያ ጣቢያዎችን ማዘጋጀታቸውን ገልጸው “ሁሉም አካላት ተገቢ የሆነ የይል መሙያ መሠረተ ልማት እንዳላቸው ማረጋገጥ አለባቸው” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ ደስታ በበኩላቸው በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም በመዲናዋ የሚገኙ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
በቅርቡ ከነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን ፈቃድ በመውሰድ በተቋም ደረጃ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል መሙያ ማሽን (ቻርጀር) መትከል የሚፈቅድ መመሪያ መጽደቁ ይታወሳል።
መመሪያው በመንገዶች ግራና ቀኝ በየ50 ኪሎሜትር ልዩነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መሙላት የሚችል ፈጣን ቻርጀር ጣቢያ ማቋቋም ይፈቅዳል።

ዜና፡ በ #አፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ተፈናቅለው በተጨናናቀ መጠለያ የሚገኙ ዜጎች በቂ ውሃና ምግብ እየቀረበላቸው አለመሆኑን ገለጹ
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለሳ ወረዳ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተከትሎ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ነዋሪዎች እየቀረበላቸው የሚገኘው እርዳታ በቂ አለመሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
“ያለው የሰው ብዛት እና የሚመጣው እርዳታ ተመጣጣኝ አይደለም። የውሃ ችግር በጣም አለ። የሮቶ ውሃ ነበረ የምንጠቀመው እሱ ካለቀ በኋላ ሰው የወንዝ ውሃ ነው እየተጠቀመ ያለው አሁን ላይ። ይህም ለበሽታ ተጋላጭ እንዳያደርገን ስጋት አለን።" ሲሉ አቶ ፈኪር አህመድ የተባሉ ተፈናቃይ ገልጸዋል።
ተፈናቃዮቹ ከመጠጥ ውሃ በተጨማሪ ለመጠለያ የሚውል ሸራ፣ ፍራሽ፣ የምግብ ማብሰያ ግብዓቶች እና ሌሎች የአቅርቦት ችግር መኖሩን ያስረዳሉ።
ሙሉ ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6516

በአፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ተፈናቅለው በተጨናናቀ መጠለያ የሚገኙ ዜጎች በቂ ውሃና ምግብ እየቀረበላቸው አለመሆኑን ገለጹ - Addis standard
በይስሓቅ እንድሪስ @Yishak_Endris አዲስ አበባ፣ ጥር 8/ 2017 ዓ/ም፦ በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለሳ ወረዳ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተከትሎ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ነዋሪዎች እየቀረበላቸው የሚገኘው እርዳታ በቂ አለመሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። አቶ ፈኪር አህመድ በዱለቻ ወረዳ ሰገንቶ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ በአከባቢው…
ዜና፡ በ #አክሱም ከተማ የሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶች በቀረቡባቸው ክሶች ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዙ
የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅሬታ ማቅረቡን ተከትሎ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የከለከሉትን አምስት ትምህርት ቤቶች በቀረቡባቸው ክሶች ላይ ምላሽ እንዲሰጡ አዘዘ።
የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአክሱም ከተማ 159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሃይማኖታዊ ልብሳቸው ምክንያት ትምህርት ቤት እንዳይገቡ መታገዳቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶቹን ከሷል።
አቤቱታውን የተመለከተው የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የሚከለክለውን መመሪያ በተማሪዎች ላይ "ሊመለስ የማይችል የመብት ጥሰት" ሊያስከትል እንደሚችል ገልጾ ታግዶ እንዲቆይ ወስኗል።
ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6527

በአክሱም ከተማ የሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶች በቀረቡባቸው ክሶች ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዙ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 8/ 2016 ዓ/ም፡- የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የትግራይ ክልል ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የከለከሉ አምስት ትምህርት ቤቶች በቀረቡባቸው ክሶች ላይ ምላሽ እንዲሰጡ አዘዘ። የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ 159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሃይማኖታዊ ልብሳቸው ምክንያት ትምህርት ቤት እንዳይገቡ መታገዳቸውን ተከትሎ ትምህርት…
በ #ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል በታጣቂዎችና ሚሊሻዎች መካከል በተከፈተ ተኩስ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተክል ዞን ቡለን ከተማ፣ በ #ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎችና በክልሉ ሚሊሻዎች መካከል በተከፈተ ተኩስ የሰው ሕይወት መጥፋቱን የከተማው ነዋሪዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ፡፡
የክልሉ ነዋሪዎች "የሸኔ ኃይሎች" በማለት ወደ የጠሯቸው የኦነስ ታጣቂዎች በመተከል ዞን በቡልን ከተማ "ባንክ ለመዝረፍ" ባደረጉት ሙከራ በወረዳው የሚታወቁ የአገር ሽማግሌ መገደላቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ከ200 በላይ የሚደርሱ የሸኔ ታጣቂዎች፣ 34 ኪሎ ሜትር ርቀት በማቋረጥ ቡለን ከተማ ላይ የሚገኘውን የ #ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመዝረፍ ሙከራ አድርገዋል ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የቡለን ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል።
የክልሉ ሚሊሻዎች ካምፕና ባንኩ ጎን ለጎን በመሆኑ፣ ከጥበቃዎች ጋር በመሆን ዝርፊያውን ሊከላከሉት ችለዋል ብለዋል።
በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከታጣቂ ቡድኑ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ፣ በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት አለመድረሱን ጠቁመዋል፡፡
ታጣቂዎቹ በሚመለሱበት ወቅት "የእጅ ስልኮችንና ሌሎች ንብረቶችን እየቀሙ" መሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን ያረጋገጡት የቦሮ ዴሞክራቲክስ ፓርቲ አባልና የሕዝብ ተወካዮች አባል የሆኑት መብራቱ ዓለሙ (ዶ/ር) ታጣቂዎቹ በዞኑ በተለይም ድባጤ ወረዳ አብዛኛዎቹን ቀበሌዎች ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

#አሜሪካ በ #ሱዳን የጦር አዛዥ አአል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ ጣለች
አሜሪካ የሱዳን የጦር አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበትንና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የተፈናቀሉበትን የእርስ በእርስ ጦርነት በማባባስ ከሳለች። የአሜሪካ ግምዣ ቤት፤ የቡርሃን አመራር የሲቪል መሰረተ ልማትን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች፣ በገበያዎች እና በሆስፒታሎች ላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን እንዲሁም ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ግድያ መፈጸማቸውን ገልጿል።
በዚህም ትናልንት በአልቡርሃን ላይ ማዕቀብ የተጣለ ሲሆን ይህም የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ በሆኑት ሞሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ከተወሰደ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።
"የቡርሃን አመራር ሰራዊት ከድርድር ይልቅ ጦርነትን መርጧል" ያለው የአሜሪካ ግምጃ ቤት፤ እርምጃው ከቡርሃን ጋር የተያያዙ የአሜሪካን ንብረቶች በሙሉ እንደሚያግድ እና አሜሪካውያን ከእሳቸው ወይም ከተዛመጅ አካላት ጋር እንዳይገናኙ የሚከለክል መሆኑንም አክሎ ገልጿል።
በተጨማሪም ዋሽንግተን የሱዳን-ዩክሬን ዜግነት ያላቸውን እና በሆንግ ኮንግ የሚገኘውን ኩባንያ ጨምሮ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎችን ለሱዳን ጦር መሳሪያ በሚያቀርቡ አካላት ላይም ትኩረት አድርጋለች።
የቡርሃን በአልጀዚራ በተላለፈው ንግግራቸው “እቺን ሀገር ለማገልገል ማንኛውንም ማዕቀብ እንቀበላለን" ሲሉ ተደምጠዋል። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የአሜሪካን እርምጃ "ግራ የሚያጋባ እና ደካማ የፍትህ ስሜት" ሲል ተችቷል።

#ፌዴራል_ፖሊስ በዋናው መስሪያ ቤቱ ያደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል አስመረቀ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በዋናው መስሪያ ቤቱ ያደራጀውን የድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከል በትናንትናው እለት ስራ አስጀመረ። በተጨማሪም ኮማንድ ኮንትሮል ያለው ዘመናዊ መንገድ የሚዘጋ ተሸከርካሪም ተመርቆ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል ተብሏል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በድሮን ፓይለት ማሰልጠኛ ማዕከሉ አዲስ የገቡት ድሮኖች ከከተማ ፀጥታ ቁጥጥር ባሻገር የቦርደር ሴኪዩሪቲን ጨምሮ የኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችል ዕድል የሚፈጥሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ በሀገሪቱ ፖሊስ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነው የድሮን ቴክኖሎጂ ማዕከል፤ ወጣት የፖሊስ ኦፊሰሮች የቴክኖሎጂ ስልጠና አግኝተው የተሻለ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈጠረ ነው ሲል ጠቅሰው አሁን ላይ በተቋሙ ያለው የድሮን አቅም በፖሊስ የወንጀል መከላከል ሰርቪላንስ እና የምርመራ ስራ ከፍተኛ እገዛ አለው ብለዋል።
በተጨማሪም እንደ አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ያሉ መድረኮች ሲኖሩ ለተወሰነ ጊዜ መንገዶችን ዘግቶ ቪአይፒዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል የራሱ የሆነ ኮማንድ ኮንትሮል ያለው ዘመናዊ ሮድ ብሎክ (መንገድ የሚዘጋ) ተሸከርካሪም ተመርቆ ስራ እንዲጀምር ተደርጓል ተብሏል፡፡
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02zdynN9ckoLC9nzty6Z7BKVzhYzUyNmLLrgGkp55imWx7BrvfJKGJcNLjgR8fAXAzl

ምርጫ ቦርድ የአሰራር ሂደት ላይ ግልፅኝነት ለማስፈን እንዲያግዝ የምርጫ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ እንዲጸድቅ መከረ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርዱ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ማሻሻያ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ቦርዱ አዋጆች ሁሉንም አሳታፊ እና ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት አመቺ እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
“የአዋጁ ማሻሻያም ቦርዱ ይበልጥ ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ፍትሐዊ እና ታማኝ እንዲሆን እንደሚያስችለው” አክለው ገልጸዋል ሲል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።
ቦርዱ “ዓለም ዓቀፍ የአሰራር መለኪያዎችን ያሟሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ አሠራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ” መሆኑንም ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። ይህም የምርጫ ቦርድ የአሰራር ሂደት ላይ ግልፅኝነት ለማስፈን እንደሚያግዝ አመላክተዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2019 የተደነገገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ህወሐትን ጨምሮ የታገዱ ፓርቲዎችን ዳግም ህጋዊ ሆነው እንዲመዘገቡ ለማስቻል ባሳለፍነው አመት ግንቦት ወር መሻሻሉ ይታወቃል።