#በፎቶ፡ በ #ሰሜን_ወሎ ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመ
በ #አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/2017 ዓ.ም በደረሰው “ምክንያቱ ባልታወቀ” የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ተገልጿል፡፡
የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉየ ረታ 4 ሺህ 560 ኩንታል የሚኾን 152 ክምር ላይ የደረሰው ቃጠሎ ጉዳት ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቁመዋል፡፡
የዋድላ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጽሕፈት ቤት ቡድን መሪ ምትኩ ሞላ በበኩላቸው እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ መኾናቸውን መግለጻቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡
ፎቶ፡ አሚኮ

ዜና: በአምስት ወራት #ከዳያስፖራው ከ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱ ተገለጸ
ባለፉት አምስት ወራት ከዳያስፖራው ከሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ከሬሚታንስ መገኘቱን #የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲመራ መደረጉ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ይገባ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ በባንኮች በኩል እንዲመጣ ማስቻሉ ትልቅ ጥቅም እያስገኘ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ አመልክተዋል።
በተጨማሪ በዶላር አስቀምጦ በዶላር ማውጣት የሚቻልበት ሥርዓት መዘርጋቱም ለውጤቱ አንዱ ማበረታቻ ሆኗል ማለታቸውን ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል ከፍተኛውን የሬሚታንስ ገቢ ያገኘችው #ኬንያ መሆናን የአለም ባንክ ይፋ ያደረገው ሪፖርት ያሳያል፤ አራት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ዶላር በማግኘት።
#ሶማሊያ 1 ነጥብ 73 ቢሊየን ዶላር በ2024 ያገኘች ሲሆን #ኡጋንዳ አንድ ነጥብ 49 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷ ተጠቁሟል፤ #ታንዛንያ፣ #ሩዋንዳ እና #ቡሩንዲ በ2024 ያገኙት የውጭ ምንዛሬ ከ1 ቢሊየን ዶላር በታች መሆኑን አመላክቷል።
ኢትዮጵያ ከዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ከሚላክ ገንዘብ በየዓመቱ በአማካይ ከ4 እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር እያገኘሁ ነው ስትል መግለጿን መዘገባችን ይታወሳል፤ የአለም ባንክ በሪፖርቱ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2024 ከሬሚታንስ ያገኘችው ገቢ 630 ሚሊየን ዶላር ነው ሲል አስቀምጧል።
ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ከሬሚታንስ የምታገኘው ሀገር ግብጽ መሆኗን የጠቆመው የአለም ባንክ ሪፖርት በ2024 ብቻ 22.65 ቢሊየን ዶላር አግኝታለች ብሏል፤ ናይጀሪያ 19.84 ቢሊየን በማግኘት በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

ዜና: #ሶማሊያ ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አባልነት ለመወዳደር ራሷን ዕጩ አድርጋ ማቅረቧን አስታወቀች
ከሳምንታት በፊት ኢትዮጰያ ራሷን እጩ አድርጋ ባቀረበችበት የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ውድድር ሶማሊያም ራሷን እጩ አድርጋ ማቅረቧን አስታወቀች።
በቀጣይ የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እ.አ.አ 2025 እስከ 2028 የስልጣን ዘመን የህብረቱ የሰላም እና የጸጠታ ምክር ቤት አባል ሀገራት በውድድር የሚመረጡ ይሆናል።
የሶማሊያ መንግስት ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “ሶማሊያ ራሷን እጩ አድርጋ ማቅረቧ ሀገሪቱ ለአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ አጀንዳ የበኩላን አስተዋጽኦ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል” ብሏል።
ሱማሊያ ለ17 ዓመታት የህብረቱን የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ያስተናገደች መሆኗን የጠቀሰው መግለጫው ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማምጣት ለሚደረገው ጥረት ማሳያ ነው ሲል አትቷል።
በቅርቡ ለሶማሊያ የተደረገላት የእዳ ስረዛ፣ በያዝነው ወር ሶማሊያ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን ለሁለት አመታት ለማገልገል መጀመሯ፣ የምስራቅ አፍሪካ ማገበረሰብ አባል ለመሆን ያቀረበቸው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቷን በመጥቀስ መግለጫው ሶማሊያ ለአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ለመመረጥ ያበቋታል ሲል አስታውቋል።
ከ3 ሳምንታት በፊት #ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ልትወዳደር መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0e6Gykk6HJiAf1RJq79sbUynMfTizDPQ3nBxxb5CykptcGtDYUh6mQbnBpVmrDr7ol

ዜና: በህገወጥ አዘዋዋሪዎች እርቃናቸውን ታግተው የነበሩ 26 #ኢትዮጵያውያን መታደጉን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አስታወቀ
የደቡብ #አፍሪካ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ እና ሰነድ አልባ 26 ኢትዮጵያውያንን ከህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እገታ መታደጉን አስታወቀ።
ኢትዮጵያውያኑ #በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው በአንድ ቤት ውስጥ እርቃናቸውን እንደነበሩ የፈረንሳዩ የዜና አውታር ኤኤፍፒ አስታውቋል።
ፖሊስ ኢትዮጵያውያኑ ታግተው ወደነበረበት ቤት በተጠጋበት ወቅት ሌሎች ሰላሳ የሚሆኑ በመስኮት በመዝለል ማምለጣቸውን እና በአከባቢው ተደብቀው ሊሆኑ እንደሚችሉ መገለጹን ዘገባው አመላክቷል።
ፖሊስ ከታደጋቸው ኢትዮጵያውያኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በጆሃንስበር ሰሜናዊ ክፍል ዳርቻ ላይ በሚገኝ መኖሪያ ቤት እርቃናቸውን እና ምንም አይነት ሰነድ ሳይኖራቸው ታግተው እንደነበር የከተማዋ ፖሊስ ሃላፊ ኮሎኔል ፊላኒ ኩዋላሴ መግለጻቸውን ጠቁሟል።
ባሳለፍነው አመት ነሃሴ ወር በተመሳሳይ አከባቢ 80 ኢትዮጵያውያን አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ያለበቂ ምግብ ተቆልፎባቸው ፖሊስ እንደታደጋቸው መዘገቡን ኤኤፍፒ አስታውሷል።
ፖሊስ ኢትዮጵያውያኑ ወዳሉበት ቤት እንደገባ 15 እርቃናቸውን የሆኑ ማግኘቱን እና መያዙን የገለጹት የፖሊስ ሃላፊው 11 የሚሆኑት ደግሞ ለማምለጥ በሞከሩበት ወቅት በደተረሰባቸው ጉዳት ሳቢያ ህክምና እንዲያገኙ በሚል ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0kLCSw9eJ5tmLQcuVqD2ETubdXVRC36KqagpUYHztqFKxPFU1WdkFnNT8i4pdwReFl

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በ #ኢትዮጵያ የተከሰተው የቤንዚን እጥረት በ #ሱዳን ካለው ጦርነት ጋር ተያያዥ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳሃረላ አብዱላህ ገለጹ።
የኢትዮጵያ እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ቤንዚን በሱዳን ወደብ የሚገባ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ በሱዳን ጦርነት ምክንያት ሙሉ አቅርቦቱ ለሙሉ ወደ ጅቡቱ መዞሩን ገልጸዋል። በዚህም ጁቡቲ ማስተናገድ ከሚችለው አቅም በላይ በመሆኑ ችግሮች መፈጠራቸውን ገልጸዋል።
“ከፈረንጆቹ 2024 የካቲት ወር ጀምሮ የጅቡቲው ሆራይዘን ተርሚናል ከአቅም በታች ሲያስተናግድ በመቆየቱ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ተከስቷል” ሲሉ ለኢቢሲ ተናግረዋል። ሌላኛው ሰሞኑን የተፈጠረው እጥረት የዋጋ ጭማሪ ይኖራል በሚል ግምት ነዳጅ በመያዝ መከሰቱንም አክለው ገልጸዋል።
ይመልከቱ!

#ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያን ጀመረች
የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ከአመታት ቅድመ ዝግጅት በኋላ ትናንት ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስራው ተጀምሯል።
የአክሲዮን ገበያ ሥራውን በይፋ ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ "ለኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል" ብለዋል።
አክለውም "ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅም እና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይዎን ያፍሱ" ሲሉ አሳስበዋል።
የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያው የሀገር ውስጥም ሆነ የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ መሳቡ ተጠቁሟል።
በዚህም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ዋና ዋና የመንግስት ኢንተርፕራይዞች 25 በመቶ ድርሻ መውሰዳቸው ተመላክቷል።
በተጨማሪም አዋሽ ባንክ እና ግሎባል ባንክን የመሳሰሉ ግንባር ቀደም የግል ባንኮች በገበያው ላይ የኢኩዊቲ ኢንቨስትመንት አድርገዋል።

ዜና፡ በ #ኦሮሚያና #አማራ ክልል ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙና በ #ትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች አለመግባባት እንዲፈታ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ
በኦሮሚያና አማራ ክልል እንዲሁም በሀገሪቱ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች ቆመው ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈቶ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ።
ፓትርያርኩ ትናንት ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ “እስካሁን ድረስ የብዙ ነገሮች ዋጋ ታውቋል፤ የሰላም ተመን ግን አልታወቀም” ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ሰላም ጠብን መግደል፣ ከእኔ ይልቅ ወንድሜ ይድላው ብሎ የልብ ስፋት ማግኘት ነው ብለዋል።
በተጨማሪም በትግራይ ክልል የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች “መበደላችሁን እናውቃለን፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው” ያሉት ፓትርያርኩ አክለውልም፤ “ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ” ሲሉ ጠይቀዋል።
ሙሉ ለማንበብ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6440

Addis standard
በኦሮሚያና አማራ ክልል ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙና በትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች አለመግባባት እንዲፈታ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ - Addis standard
አዲስ አበባ ጥር 3/ 2017 ዓ/ም፦ የኦሮሚያና አማራ ክልል እንዲሁም በሀገሪቱ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች ቆመው ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈቶ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ። ፓትርያርኩ ትናንት ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ የሰላም ትርጉሙ…
የ #አዲስ_አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ካሉት 41 ባቡሮች እየሠሩ ያሉት 16ቱ ብቻ እንደሆኑ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ወደ ስራ ሲገባ 41 ባቡሮች የነበሩት ቢሆንም አሁን አገልግሎት እየተሰጡ ያሉት ባቡሮች ቁጥር 16 ብቻ ነው ሲሉ የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብርሀን አበባው ለጋዜጣ ፕላስ ገልጸዋል፡፡
ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባቡሮች አገልግሎት የማይሰጡት በብልሽት ምክንያት መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።
ባቡሮቹ ብልሽት በሚያጋጥማቸው ጊዜ የጥገና ዕቃዎች ገበያ ላይ የሉም ያሉት ኃላፊው፤ ችግሩን ለመፍታት ከአንዱ ባቡር እየተነቀለ ወደ ሌላኛው ሲገጠም መቆየቱ ተናግረዋል።
የባቡሮቹን ሶፍትዌር ለመጠቀም ፍቃድ አለመኖሩም ለባቡሮቹ መቆም ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተበላሽተው የቆሙ ባቡሮችን ወደ ስራ ለማስገባት፣ የተሻለ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ዘርፉ አሁን ካለበት የውጤት መቀዛቀዝ ለማውጣት የሪፎርም ስራዎች መጀመራቸውን አብራርተዋል፡፡
በዚህም እስከ መጪው ሰኔ ድረስ አምሥት ባቡሮች ወደሥስራ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የሁለት ባቡሮች የጥገና ስራ መጠናቀቁን ጠቁመው፤ እነኝህ ባቡሮች በቀጣይ ሶስት ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ አብራርተዋል።
(ኢፕድ)

ዜና፡ በ #አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ በመከልከላቸው የብሔራዊ ፈተና የኦንላይን ምዝገባ እንዳለፋቸው ገለጹ
በ #ትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና የኦንላይን ምዝገባ ለማከናወን "ሂጃብ እንዲያወልቁ" መጠየቃቸው ባለመቀበላቸው ትናንት ጥር 2 ቀን የምዝገባ ቀኑ እንዳለፋቸው ገለጹ።
ተማሪዎቹ “ሂጃባቸውን እስካላወለቁ ድረስ ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ትምህርት ቤቶቹ መከልከላቸውን” ገልጸው ይህም የሃይማኖታዊ እምነትን መጣስ ነው ብለዋል።
ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች አንድ ተማሪ፣ "ሃይማኖታችን ስለሚከለክል ለብሔራዊ ፈተና ለመመዝገብ ብለን ሂጃባችንን ማውለው አንችልም። ሃይማኖታዊ ግዴታችንን ከመተላለፍ ይልቅ ትምህርታችንን መተው እንመርጣለን” ስትል ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጻለች።
ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6450

በአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ በመከልከላቸው የብሔራዊ ፈተና የኦንላይን ምዝገባ እንዳለፋቸው ገለጹ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ጥር 3/ 2017 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ሙስሊም ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና የኦንላይን ምዝገባ ለማከናወን “ሂጃብ እንዲያወልቁ” መጠየቃቸው ባለመቀበላቸው ትናንት ጥር 2 ቀን የምዝገባ ቀኑ እንዳለፋቸው ገለጹ። ተማሪዎቹ “ሂጃባቸውን እስካላወለቁ ድረስ ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ትምህርት ቤቶቹ መከልከላቸውን” ገልጸው ይህም የሃይማኖታዊ እምነትን…
ዜና: በእርዳታ እጦት እና በፖለቲካ ሽኩቻ ሳቢያ #በትግራይ ክልል በሚግኙ የተፈናቃይ ማዕከላት የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው
በ#ህወሓት መካከል እየተካረረ የሚገኘው አለመግባባት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ በክልሉ 99 መጠለያ ማዕከላት በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ የህክምና አገልግሎት አቅርቦት ውስንነት እና በቂ ሰብአዊ እርዳታ እንዳይቀርብ እና ለከፋ ችግሮች እንዲዳረጉ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል።
በሽሬ ከተማ የተፈናቃዮች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ወላይ በርሄ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ባለፉት ሶሰት ወራት ብቻ “ህንፃድ ማዕከል” ከተጠለሉ ተፈናቃዮች መካከል 300 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ይናገራሉ።
አስተባባሪው በየቀኑ ቢያንስ አንድ ሞት እንደሚመዘገብ ጠቁመው አንዳንድ ቀናት ደግሞ ሁለትና ሶስት ግለሰቦች በአንድ ጊዜ ሲቀበሩ ይታያል ብለዋል።
“የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ ሁኔታውን ለመቁጠር፣ ለመመዝገብ ወይም ለመፍታት ምንም ዓይነት ጥረት እየተደረገ አይደለም” ያሉት አስተባባሪው "አመራሩ በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ስለገባ፣ ከተፈናቃዮች አስቸኳይ ፍላጎት ይልቅ ለስልጣን ሩጫ በማስቀደሙ ነው" ችግሩን ያባባሰው ሲሉ አስታውቀዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6441

በእርዳታ እጦት እና በፖለቲካ ሽኩቻ ሳቢያ በትግራይ ክልል በሚግኙ የተፈናቃይ ማዕከላት የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው - Addis standard
በሞላ ምትኩ @MollaAyenew አዲስ አበባ፣ ጥር 3/2017 ዓ.ም፡- የትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ውስጥ በዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በሚመራው ቡድን እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ክልሉ የፖለቲካ ውዥንብር ላይ ይገኛል። ይህ አለመግባባት ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ በክልሉ 99…
የ #ሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
ከአንድ አመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር በኋላ የአንካራውን ስምምነት ተከትሎ የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ በዛሬው ዕለት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሬዝዳንቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ፤ “የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ ሁለቱ ሃገራት የነበራቸው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል፡፡
ሆኖም የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በመካከላቸው የተፈጠረውን አልመግባባት ለመፍታት ያስችላል የተባለ ስምምነት በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም መፈራረማቸው ይታወሳል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና: ከባለስልጣኑ ፈቃድ በመውሰድ በተቋም ደረጃ #ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል መሙያ ማሽን (ቻርጀር) መትከል የሚፈቅድ መመሪያ ጸደቀ
በመንገዶች ግራና ቀኝ በየ50 ኪሎሜትር ልዩነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መሙላት የሚችል ፈጣን ቻርጀር ጣቢያ ማቋቋም ይፈቅዳል
ተቋማት ለሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል ማቅረብ ከፈለጉ ከነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ፈቃድ በመውሰድ ማሽኑን መትከል የሚያስችላቸው መመሪያ መጽደቁ ተጠቆመ።
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል ሙሌት ስርዕትን የተመለከተ ባጸደቀው መመሪያ መሰረት ለራስ አገልግሎት በተለያዩ ተቋማት የሚተከሉ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል መሙያዎች ከባለስልጣኑ ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።
በግል በቤት ውስጥ ከሚተከሉ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል መሙሊያ ማሽኖች ፈቃድ መጠየቅ የማይጠበቅባቸው መሆኑን ያመላከተው የተቋሙ መረጃ ከዚህ ውጭ ግን ማናቸውም የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል ሙሌት የሚሰጡ ማሽኖች መትከል የሚቻለው ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።
መመሪያው ለህዝብ በሽያጭ የኤሌክትሪክ ሃይል ሙሊት አገልግሎት የሚሰጡ ታሪፋቸው በባለስልጣኑ ሲጸድቅላቸው ብቻ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያስገድዳል።
“ከኤሌክትሪክ ታሪፍ ጋር በተገናኘ ከባለስልጣን መ/ቤቱ የሃይል አቅርቦትና ሽያጭ ፈቃድ የወሰዱ ተቋማት ለበለስልጣኑ የታሪፍ ፕሮፖዛላቸውን አቅርበው ሲያፀድቅ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነ መመሪያው ያሳያል፡፡
ለማሽኖቹ መትከያ ቦታዎችን በተመለከተ መመሪያው በየ50 ኪሎ ሜትር በየመንገዶቹ ግራና ቀኝ በኩል እንዲቋቋም መመሪያ የሚፈቅድ ሲሆን በተጨማሪም ለከባድ ተሸከርካሪዎች ማለትም አውቶቢስ እና የጭነት ተሸከርካሪዎች በየ120 ኪሎ ሜትር ቢያንሰ አንድ የሃይል መሙያ እንዲኖር ይፈቅዳል፡፡