Addis Standard Amharic
17.9K subscribers
4.87K photos
123 videos
3 files
3.87K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
#ኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በኢትዮጵያ ወደ ምድር ሲንቀሳቀሱ የታዩት የቁስ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ አስታወቀ

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የታዩት የቁስ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ አስታውቋል።

የታየው ስብስብ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል ሲል ተቋሙ ገልጿል።

የእነዚህ አካላት ስብስብ ክስተት ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችል ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራ እንደሚገኝም አክሎ አስታውቋል።

በቅርቡ በኬንያ በማኩኒ ካውንቲ ሙኩኩ በተባለችው መንደር ክብ ቁስ 2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን 500 ኪሎግራም ክብደት ያለው ግዙፍ ብረት ከሰማይ መወደቁ ይታወቃል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
#አፋር ክልል ጋቢ ዞን በርዕደ መሬት 37 ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ ለሙሉ እና በከፊል ውድመት ደረሰ

በአፋር ክልል ጋቢ ዞን እየተከሰተ ባለው ተከታታይ ርዕደ መሬት በሶስት ወረዳዎች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 16 ትምህርተ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ 21 ትምህርት ቤቶች ደግም ከፊል ጉዳት እንደረሰባቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ያዮ ጉዳቱ የደረሰው በአዋሽ-ፋንታሌ፣ ዱላሳ እና ሓንሩካ ወረዳዎች በሚገኙ 37 ትምህርት ቤቶች እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

አክለውም የክልሉ መንግስት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ በክልል ደረጃ ኮሚቴ በማቋቋም ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በገቢረሱ ዞን ዱለሳ እና አዋሽ ፈንታሌ ወረዳዎች በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከሰም ስኳር ፋብሪካ ላይ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ጉዳቶችን ያስከተሉ ትላልቅ አደጋዎች መደረሳቸውና የድርጅቱ ኃይል ማከፋፈያ ህንጻ መፍረሱ ተገልጿል። የኤሌክትሪካል እና መካኒካል ጉዳቶችም መደርሳቸውን የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አሊ ሁሴን ተናግረዋል፡፡

በወረዳዎቹ ከሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች የተፈናቀሉ 4 ሺህ የከሰም ሱካር ፋብሪካ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ58 ሺህ በላይ ሰዎች ጊዜያዊ መጠለያ ገብተው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑም ክልሉ አስታውቋል።
#በፎቶ፡ በ #ሰሜን_ወሎ ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመ

#አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/2017 ዓ.ም በደረሰው “ምክንያቱ ባልታወቀ” የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ተገልጿል፡፡

የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉየ ረታ 4 ሺህ 560 ኩንታል የሚኾን 152 ክምር ላይ የደረሰው ቃጠሎ ጉዳት ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቁመዋል፡፡

የዋድላ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጽሕፈት ቤት ቡድን መሪ ምትኩ ሞላ በበኩላቸው እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ መኾናቸውን መግለጻቸውን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡

ፎቶ፡ አሚኮ
ዜና: በአምስት ወራት #ከዳያስፖራው ከ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱ ተገለጸ

ባለፉት አምስት ወራት ከዳያስፖራው ከሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ከሬሚታንስ መገኘቱን #የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲመራ መደረጉ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ይገባ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ በባንኮች በኩል እንዲመጣ ማስቻሉ ትልቅ ጥቅም እያስገኘ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ አመልክተዋል።

በተጨማሪ በዶላር አስቀምጦ በዶላር ማውጣት የሚቻልበት ሥርዓት መዘርጋቱም ለውጤቱ አንዱ ማበረታቻ ሆኗል ማለታቸውን ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል ከፍተኛውን የሬሚታንስ ገቢ ያገኘችው #ኬንያ መሆናን የአለም ባንክ ይፋ ያደረገው ሪፖርት ያሳያል፤ አራት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ዶላር በማግኘት።

#ሶማሊያ 1 ነጥብ 73 ቢሊየን ዶላር በ2024 ያገኘች ሲሆን #ኡጋንዳ አንድ ነጥብ 49 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷ ተጠቁሟል፤ #ታንዛንያ#ሩዋንዳ እና #ቡሩንዲ በ2024 ያገኙት የውጭ ምንዛሬ ከ1 ቢሊየን ዶላር በታች መሆኑን አመላክቷል።

ኢትዮጵያ ከዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ከሚላክ ገንዘብ በየዓመቱ በአማካይ ከ4 እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር እያገኘሁ ነው ስትል መግለጿን መዘገባችን ይታወሳል፤ የአለም ባንክ በሪፖርቱ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2024 ከሬሚታንስ ያገኘችው ገቢ 630 ሚሊየን ዶላር ነው ሲል አስቀምጧል።

ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ከሬሚታንስ የምታገኘው ሀገር ግብጽ መሆኗን የጠቆመው የአለም ባንክ ሪፖርት በ2024 ብቻ 22.65 ቢሊየን ዶላር አግኝታለች ብሏል፤ ናይጀሪያ 19.84 ቢሊየን በማግኘት በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።
ዜና: #ሶማሊያ ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አባልነት ለመወዳደር ራሷን ዕጩ አድርጋ ማቅረቧን አስታወቀች

ከሳምንታት በፊት ኢትዮጰያ ራሷን እጩ አድርጋ ባቀረበችበት የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ውድድር ሶማሊያም ራሷን እጩ አድርጋ ማቅረቧን አስታወቀች።

በቀጣይ የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እ.አ.አ 2025 እስከ 2028 የስልጣን ዘመን የህብረቱ የሰላም እና የጸጠታ ምክር ቤት አባል ሀገራት በውድድር የሚመረጡ ይሆናል።

የሶማሊያ መንግስት ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “ሶማሊያ ራሷን እጩ አድርጋ ማቅረቧ ሀገሪቱ ለአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ አጀንዳ የበኩላን አስተዋጽኦ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል” ብሏል።

ሱማሊያ ለ17 ዓመታት የህብረቱን የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ያስተናገደች መሆኗን የጠቀሰው መግለጫው ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማምጣት ለሚደረገው ጥረት ማሳያ ነው ሲል አትቷል።

በቅርቡ ለሶማሊያ የተደረገላት የእዳ ስረዛ፣ በያዝነው ወር ሶማሊያ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን ለሁለት አመታት ለማገልገል መጀመሯ፣ የምስራቅ አፍሪካ ማገበረሰብ አባል ለመሆን ያቀረበቸው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቷን በመጥቀስ መግለጫው ሶማሊያ ለአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ለመመረጥ ያበቋታል ሲል አስታውቋል።

ከ3 ሳምንታት በፊት #ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ልትወዳደር መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0e6Gykk6HJiAf1RJq79sbUynMfTizDPQ3nBxxb5CykptcGtDYUh6mQbnBpVmrDr7ol
ዜና: በህገወጥ አዘዋዋሪዎች እርቃናቸውን ታግተው የነበሩ 26 #ኢትዮጵያውያን መታደጉን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አስታወቀ

የደቡብ #አፍሪካ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ እና ሰነድ አልባ 26 ኢትዮጵያውያንን ከህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እገታ መታደጉን አስታወቀ።

ኢትዮጵያውያኑ #በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው በአንድ ቤት ውስጥ እርቃናቸውን እንደነበሩ የፈረንሳዩ የዜና አውታር ኤኤፍፒ አስታውቋል።

ፖሊስ ኢትዮጵያውያኑ ታግተው ወደነበረበት ቤት በተጠጋበት ወቅት ሌሎች ሰላሳ የሚሆኑ በመስኮት በመዝለል ማምለጣቸውን እና በአከባቢው ተደብቀው ሊሆኑ እንደሚችሉ መገለጹን ዘገባው አመላክቷል።

ፖሊስ ከታደጋቸው ኢትዮጵያውያኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በጆሃንስበር ሰሜናዊ ክፍል ዳርቻ ላይ በሚገኝ መኖሪያ ቤት እርቃናቸውን እና ምንም አይነት ሰነድ ሳይኖራቸው ታግተው እንደነበር የከተማዋ ፖሊስ ሃላፊ ኮሎኔል ፊላኒ ኩዋላሴ መግለጻቸውን ጠቁሟል።

ባሳለፍነው አመት ነሃሴ ወር በተመሳሳይ አከባቢ 80 ኢትዮጵያውያን አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ያለበቂ ምግብ ተቆልፎባቸው ፖሊስ እንደታደጋቸው መዘገቡን ኤኤፍፒ አስታውሷል።

ፖሊስ ኢትዮጵያውያኑ ወዳሉበት ቤት እንደገባ 15 እርቃናቸውን የሆኑ ማግኘቱን እና መያዙን የገለጹት የፖሊስ ሃላፊው 11 የሚሆኑት ደግሞ ለማምለጥ በሞከሩበት ወቅት በደተረሰባቸው ጉዳት ሳቢያ ህክምና እንዲያገኙ በሚል ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ መደረጋቸውን አስታውቀዋል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0kLCSw9eJ5tmLQcuVqD2ETubdXVRC36KqagpUYHztqFKxPFU1WdkFnNT8i4pdwReFl
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ የተከሰተው የቤንዚን እጥረት በ #ሱዳን ካለው ጦርነት ጋር ተያያዥ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳሃረላ አብዱላህ ገለጹ።

የኢትዮጵያ እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ቤንዚን በሱዳን ወደብ የሚገባ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ በሱዳን ጦርነት ምክንያት ሙሉ አቅርቦቱ ለሙሉ ወደ ጅቡቱ መዞሩን ገልጸዋል። በዚህም ጁቡቲ ማስተናገድ ከሚችለው አቅም በላይ በመሆኑ ችግሮች መፈጠራቸውን ገልጸዋል።

“ከፈረንጆቹ 2024 የካቲት ወር ጀምሮ የጅቡቲው ሆራይዘን ተርሚናል ከአቅም በታች ሲያስተናግድ በመቆየቱ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ተከስቷል” ሲሉ ለኢቢሲ ተናግረዋል። ሌላኛው ሰሞኑን የተፈጠረው እጥረት የዋጋ ጭማሪ ይኖራል በሚል ግምት ነዳጅ በመያዝ መከሰቱንም አክለው ገልጸዋል።

ይመልከቱ!
#ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያን ጀመረች

የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ከአመታት ቅድመ ዝግጅት በኋላ ትናንት ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስራው ተጀምሯል።

የአክሲዮን ገበያ ሥራውን በይፋ ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ "ለኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል" ብለዋል።

አክለውም "ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅም እና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይዎን ያፍሱ" ሲሉ አሳስበዋል።

የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያው የሀገር ውስጥም ሆነ የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ መሳቡ ተጠቁሟል።

በዚህም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ዋና ዋና የመንግስት ኢንተርፕራይዞች 25 በመቶ ድርሻ መውሰዳቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም አዋሽ ባንክ እና ግሎባል ባንክን የመሳሰሉ ግንባር ቀደም የግል ባንኮች በገበያው ላይ የኢኩዊቲ ኢንቨስትመንት አድርገዋል።
ዜና፡ በ #ኦሮሚያና #አማራ ክልል ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙና በ #ትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች አለመግባባት እንዲፈታ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ

በኦሮሚያና አማራ ክልል እንዲሁም በሀገሪቱ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች ቆመው ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈቶ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ።

ፓትርያርኩ ትናንት ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ “እስካሁን ድረስ የብዙ ነገሮች ዋጋ ታውቋል፤ የሰላም ተመን ግን አልታወቀም” ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ሰላም ጠብን መግደል፣ ከእኔ ይልቅ ወንድሜ ይድላው ብሎ የልብ ስፋት ማግኘት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች “መበደላችሁን እናውቃለን፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው” ያሉት ፓትርያርኩ አክለውልም፤ “ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ሙሉ ለማንበብ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6440
#አዲስ_አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ካሉት 41 ባቡሮች እየሠሩ ያሉት 16ቱ ብቻ እንደሆኑ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ወደ ስራ ሲገባ 41 ባቡሮች የነበሩት ቢሆንም አሁን አገልግሎት እየተሰጡ ያሉት ባቡሮች ቁጥር 16 ብቻ ነው ሲሉ የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብርሀን አበባው ለጋዜጣ ፕላስ ገልጸዋል፡፡

ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባቡሮች አገልግሎት የማይሰጡት በብልሽት ምክንያት መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

ባቡሮቹ ብልሽት በሚያጋጥማቸው ጊዜ የጥገና ዕቃዎች ገበያ ላይ የሉም ያሉት ኃላፊው፤ ችግሩን ለመፍታት ከአንዱ ባቡር እየተነቀለ ወደ ሌላኛው ሲገጠም መቆየቱ ተናግረዋል።

የባቡሮቹን ሶፍትዌር ለመጠቀም ፍቃድ አለመኖሩም ለባቡሮቹ መቆም ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተበላሽተው የቆሙ ባቡሮችን ወደ ስራ ለማስገባት፣ የተሻለ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ዘርፉ አሁን ካለበት የውጤት መቀዛቀዝ ለማውጣት የሪፎርም ስራዎች መጀመራቸውን አብራርተዋል፡፡

በዚህም እስከ መጪው ሰኔ ድረስ አምሥት ባቡሮች ወደሥስራ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የሁለት ባቡሮች የጥገና ስራ መጠናቀቁን ጠቁመው፤ እነኝህ ባቡሮች በቀጣይ ሶስት ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ አብራርተዋል።

(ኢፕድ)