YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ለወገን_ደራሽ_ወገን_ነው ‼️

ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ለሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ የሚውል #6020_A የተሰኘ አጭር የሞባይል ቁጥር ይፋ #አደረገ፡፡
ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም 40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉንና ይህንንም ለብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማስረከቡን ባወጣው መረጃ አመለክቷል።

#6020_ላይ_A ብሎ በመላክ ህብረተሰቡ በአንድ መልእክት ሁለት ብር ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ያቀረበው ኢትዮ ቴሌኮም አጭር የሞባይል ቁጥሩ መላው ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር የሚያደርጉትን ድጋፍ በተቀናጀ መልኩ ለማካሄድ ይረዳል ብሏል።

መላ ኢትዮጵያውያን በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማገዝ ለሚደረገው አገራዊ እንቅስቃሴ ቀና ምላሽ እንዲሰጥ ኢትዮ ቴሌኮም ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ:- EPA
@YeneTube @FikerAssefa